የየመን አገር ውስጥ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ኢትዮጵያውያኑ ሞቻ በሚባለው የወደብ ከተማ አቅራቢያ ሲደርሱ የተሳፈሩበት ጀልባ በመስጠሙ 24ቱም አትዮጵያውያን አልቀዋል።
የሁሉም አስከሬን መገኙቱን ባለስልጣኑ ሲናገሩ፣ የተረፉ ካሉም በማፈላለግ ላይ መሆኑን አስታውቋል።
ባለፈው ወር ከ79 ያላነሱ ኢትዮጵያውያን ባህር ላይ ማለቃቸው ሲታወስ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ባህር ላይ የሞቱ ኢትዮጵያውያንን ቁጥር 100 አድርሶታል።
ስቴት ዲፓርትመንት ባወጣው ዘገባ በየቀኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን አገራቸውን ለቀው ይሰደዳሉ። መንግስት በተደጋጋሚ አገሪቱ 11 በመቶ እንዳደገች ቢግልጽም ስደቱ ግን አሁንም ተጠናክሮ ቀጥሎአል።
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar