mandag 8. desember 2014

70 ኢትዮጵያውያን ቀይ ባህር ላይ አለቁ

ስደትን የህይወታቸው የመጨረሻ አማራጭ በማድረግ በጅቡቲ በኩል አድርገው ወደ የመን ለመግባት የሞከሩ 70 ኢትዮጵያውያን ቀይ ባህር ላይ ሰጥመው መሞታቸውን የየመን ባለስልጣናት ገልጸዋል።
ታይዝ በምትባለዋ ግዛት የሚገኙ ባለስልጣናት ለአሶሴትድ ፕሬስ እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያውያኑን አሳፍራ ስትጓዝ የነበረችው ጀልባ ባጋጠማት ከባድ አውሎ ንፋስና ማእበል አል ማክታ እየተባለ ከሚጠራው ወደብ ራቅ ብሎ ለመስመጥ ተገዳለች። ባለስልጣናቱ እንዳሉት ጀልባዋ 70 ኢትዮጵያውያንን ጭና የነበረ ሲሆን በደጋው ሁሉም ኢትዮጵያውያን አልቀዋል።
የመን የሚገኘው ጋዜጠኛ ግሩም ተክለሃይማኖት በበኩሉ በጀልባዋ ላይ የነበሩት 81 ሰዎች ሲሆኑ፣ 71 ኢትዮጵያውያንና 9 ሶማሊያዎች አልቀዋል። አይ ኦ ኤም የተባለው የስደተኞች ድርጅት አስከሬን ለመሰብሰብ ሙከራ ቢደረግም እስካሁን ምን ያክል አስከሬን እንደተሰበሰበ ለማወቅ አለመቻሉን ገልጿል
ግሩም እንደሚለው በአንድ ወር ውስጥ ብቻ 8 ሺ ኢትዮጵያውያን የመን ሲገቡ፣ በ7 ወር ውስጥ እስከ 50 ሺ ኢትዮጵያውያን ተሰደዋል።

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar