የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለሰራተኞቹ በላከው ማስጠንቀቂያ ላይ በሶማሊ ክልል ባሪ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ 33 የኢትዮጵያ ሚሊሺያዎች በአልሸባብ ታጣቂዎች መገደላቸውን ገልጾ ሰራተኞቹ አስፈላጊውን ጥንቃቄና ጥበቃ እንዲያደርጉ መክሯል።
የኢትዮጵያ የብሄራዊ የደህንነት ጥበቃ መስሪያ ቤት አልሸባብ በኢትዮጵያ ላይ ጥቃት ሊፈጽም ይችላል የሚለውን ስጋት እንደሚጋራ የገለጸው ድርጅቱ ፣ ትምህርት ቤቶች እና ሌሎች ቦታዎች በጥንቃቄ እንዲጠበቁ አዟል።
አልሸባብ ይህን ያክል ቁጥር ያለውን የኢትዮጵያ ወታደር በአንድ ጊዜ ሲገድል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አልተሰማም። የኢትዮጵያ መንግስት ስለሞቱት ወታደሮች የሰጠው አስተያየት የለም።
ኢትዮጵያ ጦሩዋን ወደ ሶማሊያ በማስገባት አልሸባብን ለማዳከም ሙከራ ብታደርግም አልሸባብ ግን አሁንም ጥቃት ከመፈጸም አልተቆጠበም።
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar