tirsdag 3. juni 2014

የትግራይ ህዝብ ዴምክራሲ ንቅናቄ (ትህዴን) ለረጅም ጊዜ ያሰለጠናቸውን ታጋዮች ማስመረቁን ገለጸ።


የትግራይ ህዝብ ዴምክራሲ ንቅናቄ (ትህዴን) ለረጅም ጊዜ ያሰለጠናቸውን ታጋዮች ማስመረቁን ገለጸ።

የትግራይ ህዝብ  ዴሞክራሲ ንቅናቄ (ትህዴን) ለረጅም ጊዜ ያሰለጠናቸውን ታጋዮች ማስመረቁን ገለጸ።

 ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሁሉም አቅጣጫ ወያኔን ለመጣል የሚደረገው ርብርብ በሁሉም መንገድ እያየለ መምጣቱን  የሚያሳይ እንቅስቃሴዎች እየታዩ ናቸው። ከዚህም ውስጥ አንዱ የትግራይ ህዝብ  ዴሞክራሲ ንቅናቄ የሆነው (ትህዴን) ሰሞኑን በርካታ ወጣት ታጋዮችን ማስመረቁ ነው።

 በርካታ ታጋዮች እንዳሉት የሚታወቀው ትህዴን ወያኔን ለመጣል በሃይል ከተነሱት ድርጅቶች አንዱ ነው። አሁንም ረመጽ የተባለውን ቡድን ለበርካታ ወራቶች በማሰልጠን በደማቅ በአል አስመርቆል። በምረቃ ስነ ስርአቱ ላይ ጥሪ የተደረገላቸው የተለያዩ የንቅናቄ መሪዎች መገኘታቸውንም አስታውቀዋል።

ባለፈው ወር የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይልም 4ኛ ዙር የነጻነት ታጋዮችን ማስመረቁን መዘገባችን ይታወሳል። ከውስጥ የደረሰን ዘገባ እንደሚያመላክተው ሁለቱ ንቅናቄዎች በተለያዩ ጉዳዮች ላይ አብረው እንደሚሰሩና የመረጃ ልውውጥ እንደሚያደርጉ ለማወቅ ችለናል።

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar