onsdag 4. juni 2014

በደብረ ዘይት ነዋሪዎች ብሄራቸውንና ሃይማኖታቸውን እንዲያስመዘግቡ መገደዳቸው አስግቶዋቸዋል

በከተማዋ ቀበሌ አንድ የሚገኙ ነዋሪዎች እንደገለጹት ፖሊሶች ከስቪል ሰራተኞች ጋር በመሆን ቤት ለቤት እየዞሩ የነዋሪዎችን ብሄር እና ሃይማኖት ሲመዘግቡ ውለዋል።
“የምዝገባው አላማ ሰዎችን እየመረጡ ለማፈናቀል ሊሆን ይችላል” በማለት ስጋታቸውን የገለጹት ነዋሪዎች፣ብሄርን መመዝገቡ ለምን እንዳስፈለገ ሲጠይቁ ከላይ የተላለፈ መመሪያ ነው በሚል እንደተነገራቸው ገልጸዋል።
በጉዳዩ ዙሪያ የከተማውን ፖሊስ ጽህፈት ቤት ሃላፊዎች ለማግኘት ሙከራ ብናደርግም አልተሳካልንም።
አንዳንድ አስተያየት የጠየቅናቸው ነዋሪዎች በበኩላቸው ምዝገባው  ከመጪው ምርጫ ጋር የተያያዘ ሳይሆን እንደማይቀር አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
በክልሉ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየታየ ያለው አለመረጋጋት እና በገዢው ፓርቲ እንደተቀነባበረ የሚታመኑ አልፎ አልፎ የሚነሱ አካባቢን ማእከል ያደረጉ ግጭቶች በቀበሌው ውስጥ ለሚኖሩ ሰዎች ተጨማሪ የስጋት ምንጭ ሆኗል።
ምዝገባው በመላው የክልሉ ከተሞች ይካሄድ አይካሄድ ለማወቅ አልተቻለም።

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar