onsdag 17. juli 2013

በአማራ ክልል በ12 ወረዳዎች ባለፉት 10 አመታት 13 ሺ 64 ሰዎች ከነፍስ ግድያ ወንጀል ጋር በተያያዘ ተገድለዋል



የክልሉ አሰተዳደር እና ፀጥታ ቢሮ ባካሄደው  የዳሰሳ ጥናት በ10 አመታት ውስጥ ከነፍስ ግድያ ጋር በተያያዘ 13 ሺ 64 ሰዎች ሲገደሉ ፣ 11 ሺ 93 ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል።

 በጥናቱ ውስጥ እንደተመለከተው ድብደባ መፈጸም ቀዳሚነቱን ሲይዝ  አካል ማጉደል እና ነፍስ ማጥፋት ወንጀሎች  ተከታታዮችን ደረጃዎች ይዘዋል።


የክልሉ ኗሪዎች በወንጀሎች መበራከት ለእስር ፤ለመበታተን፤ለሽፍትነት ፤ለመሰደድ፤ ለድህነት ፤ለጦም አዳሪነት፣  ለማህበራዊ ፤ኢኮኖሚያው ምስቅልቅሎች መዳረገቸው በጥናቱ ተመልክቷል፡፡


በ2004 ዓ.ም በክልሉ ማረሚያ ቤቶች በነፍስ ግድያ ወንጅል ተጠርጥረው ለገቡ  22 ሺ 26 ታራሚዎች  ሌሎች ወጭዎችን ሳያካትት ለምግብ አገልግሎት ብቻ 73 ሚሊዩን 130 ሺ 40 ብር ወጭ መደረጉም በጥናቱ ተጠቅሷል።


እያንዳንዱ ታራሚ  በትንሹ አምስት አመት ቢታሰር  በ 5 አመት 365 ሚሊየን 650 ሺ 200 ብር ወጪ ይደረጋል።


ጥናቱ በአማራ ክልል ካሉ 11 ዞኖች ውስጥ በተመረጡ 6 ዞኖች 12 ወረዳዎች ብቻ የተካሄደው ነው፡፡

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar