søndag 21. juli 2013
በአማራ ክልል ከ2001- 2004 ዓ.ም ባሉት ጊዜያት ብቻ 67 በገንዘብ የማይተመኑ ቅርሶች ተዘረፉ ፡፡
የክልሉ ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት አጠናቅሮ ለክልሉ ባለስልጣናት ባቀረበው ሪፖርት ላይ እንተመለከተው የክልሉ ቅርስ ጥበቃ ቢሮ ታሪካዊ ቦታዎችን በመንከባከብና የቅርስ ዘረፋ እንዳይካሄድ በመከላከል በኩል በቂ ጥረት አላደረገም።
በክልሉ ከ3000 በላይ የቅርስ መገኛ ተቋማት ቢኖሩም ሙዝየም በማሰራት ቅርሶቻቸውን በጥንቃቄ ለእይታ የቀረቡት 13 ብቻ መሆናቸውን የኦዲት ሪፖርቱ ጠቁሟል፡፡
በተለያዩ ዞኖች የሚጠፉ ታሪካዊ ቅርሶች ከአመት አመት መጨመርም አሳሳቢ እየሆነ መጥቱዋል፡፡
ከ2001- 2004 ዓ.ም ባለው ጊዜ 67 በርካታ የታሪክ ማስረጃዎችን የያዙ በገንዘብ የማይተመኑ ቅርሶች ተዘርፈዋል፡፡
የቅርስ ጥበቃ ቢሮው በተለያዩ ወረዳዎች ቅርሶች ስለመዘረፋቸው ሪፖርት ሲደርሰው አፋጣኝ እርምጃ ባለመውሰዱ ችግሩ ተባብሶ ቀጥሎአል።
ጥናቱን ያካሄዱት የክልሉ ምክትል ኦዲተር አቶ ስመኝ ካሴ ለኢሳት እንደገለጹት የአማራ ክልል ከፍተኛ የሆነ የቅርስ ሀብት ያለበት በመሆኑ ቅርሶችን መጠበቅ ግድ እንደሚል ተናግረዋል።
Abonner på:
Legg inn kommentarer (Atom)
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar