onsdag 24. juli 2013

የፕሮቴስታንት ሀይማኖት ተከታዮች እየተሳደድን ነው አሉ



በሰሜን ወሎ ዞን ከወልድያ ከተማ በ140 ኪሜ ርቅት ላይ በትምገኘዋ መቀት ወረዳ የሚገኙ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ከፍተኛ እንግልት እደረሰባቸውና አካባቢውንም ለቀው እንዲወጡ ግፊት እየተደረገባቸው መሆኑን ገልጸዋል።


እስካሁን በደረሰን መረጃ 10 የሚሆኑ የሀይማኖቱ ተከታዮች አካባቢውን ለቀው የወጡ ሲሆን፣ አንድ ተመስገን የተባለ ወጣት ለተባባሪ ዘጋቢያችን እንደገለጸው አማኞቹ ድንጋይ ይወረወርባቸዋል፣ ቤታቸውም በድንጋይ ይደበደባል። ተመስገን ሀምሌ 1 ከፍተኛ ድብደባ ተፈጽሞበት፣ ሞቷል ተብሎ ተጥሎ መትረፉንም ገልጿል።


የኦሮቶዶክስ ሀይማኖት ተከታይ የሆኑት መርጌታ ሙሴ ከፕሮቴስታንት ጋር ባላቸው ቀረቤታ መደብደባቸውን፣ ወርቁ ገበየሁ የተባለ ሰውም እንዲሁ ድብደባ ተፈጽሞበት እጁን መሰበሩን ተባባሪ ዘጋቢያችን ተናግሯል።



በወረዳው ውስጥ የሚኖሩ ፕሮቴስታንቶች ቤት ለመከራየትና ስራ ለመስራት አለመቻላቸውን በየጊዜውም እንገድላችሁዋለን የሚል ማስተጠንቀቂያ እንደሚደርሳቸው ለመረዳት ተችሎአል።


ጉዳት የደረሰባቸው መርጌታ ሙሴ ተክለብርሀን “በወረዳው ውስጥ ለህዝብ የሚቆረቆር መንግስት ህግ ባለመኖሩ” ከፍተኛ ስቃይ እየደረሰነ ነው  ብለዋል።


የወረዳውን አስተዳዳሪ አቶ ይሄነው በላይን ለማነጋገር በተደጋጋሚ ብንደውልም ስላካቸው አይነሳም።

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar