አሸባሪው መንግስት ነው፣ ፍትሕ ማዳን።
ፍትህ እያሉ ቃሊቲ ገቡ ገደሉት ብለው ድራማ ሰሩ።
የመንግስት ወንጀለኞች ለፍርድይቅረቡ።
አሸባሪአይደለንም።
ኢቲቪ ውሸታም ሌባ።
የገደለው መንግሥት ነው።
ኮሚቴው ይፈታ።
አቡኪ አምባሳደር።
ካሚል ሸምሱ አምባሳደር ።
በድሩ ሁሴን አምባሳደር ።
ለዲናችን እንሞታለን።የሚሉና ሌሎችም ተቃውሞዎች ለ45 ደቂቃዎች ያክል ተስተጋብተዋል።
ኢሳት ያነጋገራቸው ሙስሊሞች እንደገለጹት በአንዋር መስጊድ የተካሄደው ተቃውሞ እስከዛሬ ከታዩት ሁሉ የሚልቅ ነው።
በተመሳሳይ ዜናም በወልድያ ከተማ የሚገኙ ሙስሊሞች ‘ መንግስት ድምጻችን ይስማ፣ በመሀይሞች መመራት በቃን፣ መድረሳችን ይመለስ” የሚሉ መፈክሮችን በማሰማት ተቃውሞአቸውን ሲያሰሙ ውለዋል። በናዝሬት/አዳማ፣ በአሰሳ እና ሻሸመኔም ተመሳሳይ ተቃውሞች ተካሂደዋል።
መንግስት በደሴ በሼክ ኑር ኢማም ግድያ ላይ የሰጠው ትኩረት ብዙ ሙስሊሞችን ማበሳጨቱንና ለዛሬው ከፍተኛ ተቃውሞ መንስኤ መሆኑን ጉዳዩን በቅርብ የታዘቡ ወገኖች ይገልጻሉ።
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar