በ40 በ60 በሚባለው የቤቶች መርሃግብር የታቀፉ የዲያስፖራ አባላት ከቀጣዩዓመት ምርጫበፊት ቤት
እንዲሰጣቸው የአዲስ አበባ መስተዳድር መመሪያመስጠቱ ታውቋል። ሆኖምየጠቅላላተመዝጋቢውንየቤትፍላጎትለመሸፈንበትንሹከ16 ዓመታትበላይጊዜን
እንደሚወስድ የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ የአዲስ አበባቁጠባቤቶችኢንተርፕራይዝእስካሁን 13ሺህ 800 ቤቶችን በሰንጋተራእና ቃሊቲ ክራውን
ሆቴልበመሳሰሉአካባቢዎችላይእየገነባመሆኑየታወቀሲሆን ፣ እነዚህን ቤቶችእስከሚቀጥለውዓመትአጋማሽድረስለዕድለኞችለማስተላለፍታቅዷል።
የአስተዳደሩምንጮችእንደገለጹትቤቶቹከቀጣይዓመትምርጫበፊትሙሉበሙሉ ተጠናቀውእንዲተላለፉከአስተዳደሩመመሪያተሰጥቷል። ሆኖም
ለ40 በ60 የቤቶች ፕሮግራምየተመዘገበውጠቅላላሕዝብቁጥር 164 ሺህ 779 ያህልሲሆንአስተዳደሩግን በዓመትከ10 ሺህቤቶችበላይቤቶችን
የመገንባትአቅምባለመፍጠሩየተመዘገቡትንብቻ ለማዳረስከ16 ዓመታትበላይጊዜንእንደሚፈልግየአስተዳደሩምንጮችአስታውቀዋል፡፡ ይህደግሞ ከዛሬ
ነገየመኖሪያቤትባለቤትእሆናለሁብሎተስፋላደረገውሕዝብተስፋ አስቆራጭዜናነውብለዋል፡፡ በ20/80 በተለምዶኮንዶሚኒየምፕሮግራምየምርጫ 97
ንመቃረብታሳቢአድርጎ ሲጀመርከ350ሺበላይየአዲስአበባነዋሪመኖሪያቤትእፈልጋለሁብሎመመዝገቡን ያስታወሱትምንጮቹ ፣ ፕሮግራሙ 10 ዓመታት
ያህልቆይቶመመለስየቻለውግን 100 ሺበታችቤትፈላጊዎችንጥያቄነውብለዋል፡፡በዚህመረጃመሠረትየጠቅላላ ተመዝጋቢውንፍላጎትለሟሟላትተጨማሪ
ከ20 ዓመታትበላይጊዜንእንደሚወስድ አፈጻጸሙበራሱየሚናገርነውሲሉአስረድተዋል፡፡ የአስተዳደሩምንጭእንደሚሉትመንግሥትበአዲስ አበባበዓመት
ለቤቶችግንባታብቻ ከ2 እስከ 3 ቢሊየንብርእያወጣመሆኑንአስታውሰውከዚህበላይለማውጣትየፋይናንስ አቅምችግርመኖሩን፣ገንዘቡቢገኝምበግንባታአፈጻጸም
በኩልየአቅምችግርበመኖሩ በአጭርጊዜየመኖሪያቤትፍላጎትንለመመለስየማይችልበትአጣብቂኝውስጥእንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር
ቴዎድሮስ አድሃኖም እንደገለጹት ደግሞ ዲያስፖራው በፈለገበት አካባቢ ቤት ለመስራት ይችል ዘንድ ክልሎች መመሪያ እንዲያወጡ መታዘዙን ገልጸዋል። ሁሉም
ክልሎች ተመሳሳይ የሆነ መመሪያ ባለማውጣታቸው ለዲያስፖራው ቤት ለማደል የታቀደው እቅድ የተፈለገውን ውጤት አለማምጣቱን ገልጸዋል። ይሁን እንጅ ኢሳት
የአዲስ አበባን አዲሱን ካርታ ዝግጅት አስመልክቶ ከወራት በፊት በሰራው ዘገባ፣ የቤት ግንባታ መርሃግብሩ የተሰናከለው በአዲስ አበባ የቤት መስሪያ ባዶ ቦታ
በመጥፋቱ ነው። ቀደም ብሎ የኦሮምያን ልዩ ዞኖች ወደ አዲስ አበባ በመጠቅለል የቤት መስሪያ ቦታዎችን ለማግኘት ታቅዶ የነበረ ቢሆንም፣ የኦሮምያ ክልል አንዳንድ
ባለስልጣናትና አብዛኛው የኦሮሞ ተወላጅ በመቃወሙ እቅዱን በቀላሉ ተግባራዊ ማድረግ አልተቻለም። ዲያስፖራው ከአዲስ አበባ ውጭ ያሉ ቦታዎችን እንዲጠይቅ
ለማግባባት ኢምባሲዎች የስራ መመሪያ ተሰጥቷቸዋል። በሌላ በኩል ደግሞ ለአባይ ግድብ በቦንድ ስም ገንዘብ በውጭ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ገንዘብ ለማሰባሰብ
የታቀደው እቅድ አለመሳካቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አምነዋል። ከፍተኛ ገንዘብ ይገኝበታል የተባለው የአሜሪካ የቦንድ ሽያጭ አምና ጭራሽ አልተካሄደም ብሎ መናገር
እንደሚቻል ሚኒስትሩ ገልጸዋል። በሁሉም አገሮች ያለው የቦንድ ሽያጭ ደካማ መሆኑን የጠቀሱት ሚኒስትሩ ፣ ለድክምቱ ዝርዝር ምክንያቶችን አላቀረቡም።
የዶ/ር ቴዎድሮስ ገለጻ፣ ኢሳት ከዚህ ቀደም የቦንድ ሽያጩ በውጭ አገር አለመሳካቱን ሲዘግብ የቆየውን ያረጋገጠ ሆኗል። በውጭ ያሉ ኢትዮጵያውያን ለአባይ ግድብ
ማሰሪያ ገንዘብ ለመሰብሰብ በገዢው ፓርቲ በኩል የሚዘጋጁትን ዝግጅቶች አጥብቆ ሲቃወም እንደነበር ይታወቃል። አቶ መለስ የአባይን ግድብ እቅድ ይፋ ሲያደርጉ
በውጭ የሚገኘው ኢትዮጵያዊ 1 ቢሊዮን ዶላር ያዋጣል የሚል እምነት ነበራቸው፣ ይሁን እንጅ እስካሁን ባለው መረጃ በውጭ ያለው ኢትዮጵያዊ ከ20 ሚሊዮን
ዶላር በላይ ሊያዋጣ አልቻለም።
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar