በዛሬ ጠዋት ዘገባችን ወይንሸት ሞላ, አዚዛ አህመድ እና ኡስታዝ መንሱር እያንዳንዳቸው በ5ሺህ ብር ዋስትና ከ እስር ቤት እንዲወጡ ፍርድ ቤቱ ት እዛዝ ሰጥቶ ነበር:: ሆኖም ይህ ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ ዳኞቹን በማስፈራራት ይሁን በምን ባልታወቀ መንገድ ጉዳዩ በቢሮ ውስጥ እንዲታይ ተብሎ; አቃቤ ህጉ ለፖሊስ ተጨማሪ ሰባት የምርመራ ቀናት እንዲሰጠው በጠየቀው መሰረት; በዋስ እንዲፈቱ ተብለው የነበሩት ወይንሸት, አዚዛ እና ኡስታዝ መንሱር እንደገና እንዲታሰሩ ተብሏል::
ከሁለት ሳምንት በፊት አርብ የጁም ዓ ቀን በስፍራው ተገኝተው ከነበሩት መካከል የሰማያዊ ፓርቲዋ ወይንሸት ሞላ እና የአዲስ ጉዳይ መጽሄት ፎቶ አንሺ አዚዛ አህመድ በማይገባ ሁኔታ ታስረው መክረማቸው ይታወሳል። በተለይም ወይንሸት ሞላ ላይ በደረሰው ድብደባ እጇ እስከመሰበር ደረጃ ደርሶ እንደነበር የሚታወስ ነው። ዛሬ ያገኘነው መረጃ እንዳመለከተው ከሆነ ሁለቱም ሴት እህቶች በ5ሺህ ብር ዋስ ለግዜው ከ እስር እንዲፈቱ ልደታ የሚገኘው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ ከሰጠ በኋላ ውሳኔው ተቀልብሶ, ለሰባት ቀናት እንደገና እንዲታሰሩ ተደርጓል።

Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar