የተለያዩ ፓርቲዎች ስብስብ የሆነው የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ባወጣው
መግለጫ በቡርጅ ብሄረሰብና በቦረና ህዝብ መካከል ለዘመናት ሰፍኖ የኖረው መልካም ግንኙነት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በጸረ-ሰላም ሃይሎች እየደፈረሰ
እንደሚገኝ ገልጿል። ከ2 ሺ በላይ የሆኑ የቡርጅ ብሄረሰብ አባላት ከታህሳስ ወር 2006 ኣም ጀምሮ ከአካባቢው ተፈናቅለው ወደ ደቡብ ብሄር
ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የሰገን ዞን በመሰደድ አስቸጋሪ ህይወት በመምራት ላይ ይገኛሉ ብሎአል። በስደተኞቹ ላይ የሚደርሰው ጥቃት
እንደጨመረ መሆኑን የገለጸው መድረክ ሃምሌ 21 ቀን 2006 ዓም በተፈጸመ ጥቃት ወ/ሮ መቹ ዳዊ፣ ህጻን መቹ ቦሩ በጥይት ሲገደሉ፣ ወ/ሮ ቃበሌ
ዳዊ የተባሉ ሴት ደግሞ ከፍተኛ የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል። የብሄረሰቡ አባላት ለብዙ ትውልዶች በኖሩበት መሬት ላይ አርሰውና ከብቶቻቸውን
አርብተው እንዳይጠቀሙ እየተፈጸመባቸው ያለው ጥቃትና ተጽእኖ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባበሰ ሲሆን መንግስት ለችግሩ ተገቢውን በወቅቱ አለማስገኘቱ
በኑሮዋቸው ላይ አስቸጋሪ ሁኔታን ደቅኖባቸዋል። መንግስት በእነዚህ ወንድማማች ህዝቦች መካከል ግጭትና መቃቃር ለመፍጠር በሚራወጡ
ጸረሰላም ሃይሎች ላይ ተገቢውን ህጋዊ እርምጃ በስቸኳይ በመውሰድ ህዝቡ በሰላም አብሮ የሚኖሩበትን ሁኔታ እንዲያመቻች መድረክ ጠይቋል።
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar