onsdag 6. august 2014

የመለስ ፋውንዴሽን የገንዘብ ስብሰባ ህዝቡ እንዳይቆጣ በሚል ላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም ተደረገ

የመለስ ዜናዊን ፋውንዴሽን እንሰራለን በሚል ኢትዮጵያውያን ሰራተኞችና አርሶአደሮች በነፍስ ወከፍ ከ50 ጀምሮ
እንዲያዋጡ መገደዳቸው በቅርቡ ከተደረገው የደሞዝ ጭማሪ ጋር ተያይዞ የህዝቡን ቁጣ ሊያባብሰው ይችላል ተብሎ በመሰጋቱ ፣ የገንዘብ መሰብሰቡ ሂደት ለጊዜው እንዲቋረጥ
መደረጉን የኢህአዴግ ምንጮች ገልጸዋል።
ፋውንዴሽኑን ለማሰራት ከሚፈለገው ገንዘብ 10 እጥፍ እንደተሰበሰበ የሚነገርለት ፋውንዴሽን በወ/ሮ አዜብ መስፍን የሚመራ ሲሆን እስካሁን ድረስ ወጪና ገቢውን በተመለከተ
ለህዝብ ለማሳወቅ ባለመድፈሩ ከድርጅቱ አባሎች ትችቶች እየቀረቡበት ነው።
በአዲስአበባነዋሪዎችዘንድከፍተኛምሬትያስከተለውይህየገቢማሰባሰቢያበለፉትሁለትሳምንትበድርጅቱደጋፊዎችአማካኝነትየገንዘብማሰባሰቢያደረሰኝበመያዝበከተማውሁሉምቀበሌዎችና
በአንዳንድየወረዳየመንግስትመ/ቤቶችሲዘዋወሩየታየቢሆንም፣  በዚህሰሞንደግሞበደመወዝጭማሪውቅርየተሰኘውህዝብብሶትላለማባባስበሚልለጊዜውዘመቻውእንዲረግብተደርጓል፡፡
ዘመቻው የህዝቡ ምሬት “ቀንሷል” ተብሎ ሲታመን ሊቀጥል እንደሚችል መንጮች አክለው ገልጸዋል።

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar