የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 16ኛ ወንጀል ችሎት ህገመንግስታዊ ስርአቱን በሃይል ለማፍረስ ተንቀሳቅሰዋል
በሚል ከከሰሳቸው አምስት የግል ሚዲያ ተቋማት መካከል የሎሚ መጽሄትን ክስ የተመለከተ ሲሆን፣ ስራ አስኪያጁ አቶ ግዛው ታየ ከጠበቃቸው ጋር ተማክረው
መልስ እስከሚሰጡ ድረስ ሌላ ቀጠሮ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። ፍርድ ቤቱም የምክር ጊዜውን የፈቀደ ሲሆን፣ ተከሳሹ የ50 ሺ ብር ዋስ አስይዘው ለነሃሴ
14 እንዲቀርቡ አዟል። ፍርድ ቤቱ ከዚህ ቀደም የሮዝ አሳታሚ ድርጅትንና ከአገር ጥለው የተሰደዱትን የአዲስ ጉዳይ መጽሄት ስራ አስኪያጅን ክሶች በሌሉበት አይቷል።
ገዢው ፓርቲ በመጪው ምርጫ ላይ ስጋት ይፈጥራሉ ብሎ የሚያስባቸውን የግል መጽሄቶችና አንድ ጋዜጣ ህገመንግስታዊ ስርአቱን በሃይል ለማፍረስ ይንቀሳቀሳሉ በሚል
ወንጀል መክሰሱ ይታወቃል። አለማቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች መንግስት እየወሰደ ያለውን ነጻውን ፕሬስ የማጥፋት ዘመቻ አጥብቀው እየኮነኑት ነው።
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar