የኮንዶምኒየም ቤቶች በወቅቱ ዕጣ ወጥቶ ለሕብረሰቡ ማስተላለፍ ካለመቻሉ ጋር ተያይዞ ቆጣቢዎች
በመሰላቸትና ተስፋ በመቁረጥ ከፕሮግራሙ ራሳቸውን እያገለሉ መሆኑ ተሰምቷል።
የአዲስአበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ዋና ስራአስኪያጅ አቶ መስፍን መንግሥቱ ሰዎች በተለያየ ምክንያት እየለቀቁ መሆኑን አምነው ነገር ግን ከተስፋ መቀረጥ
ጋር እንደማይገናኝ ለመንግሥት መገናኝ ብዙሃን አረጋግጠዋል፡፡ እንደእሳቸው ገለጻ በድጋሚ ከተመዘገቡ 993ሺህ የኮንዶምኒየም ፈላጊዎች መካከል 7ሺ ያህሉ
በገዛ ፈቃዳቸው ፕሮግራሙን በማቋረጥ የንግድ ባንክን የቁጠባ ደብተር መልሰዋል፡፡
የፌዴራል መንግሥት ከቁጠባ የተሻለ ገንዘብ ለመሰብሰብ ከያዛቸው ፕሮግራሞች አንዱ ኮንዶሚኒየም ቤቶች ቁጠባ ሲሆን ይህንኑ ተከትሎም የአዲስአበባ ከተማ
አስተዳደር ከአንድ ዓመት በፊት በድጋሚ ባካሄደው የመኖሪያ ቤት ፈላጊዎች ምዝገባ መሠረት ተመዝጋቢው በየወሩ የተወሰነለትን ገንዘብ በንግድ ባንክ በኩል
እንዲቆጥቡ፣ ይህን መቆጠብ ያልቻሉ የቤት ባለቤት መሆን እንደማይችሉ በደነገገው መሠረት በርካታ ነዋሪዎች ገንዘብ ማስቀመጥ ጀምረው ነበር፡፡ ነገር ግን ቤቶቹ
መቼ እንደሚተላለፉ አለመታወቁ፣ ከዚህም በተጨማሪ መንግሥት ቀድሞ የገባውን ቃል ማለትም ቤቶቹ የሚተላለፉት በዕጣ ብቻ ነው የሚለውን በሚሸረሽር መልኩ
ለፖለቲካ ዓላማው ሲል ቤቶቹን አንዴ ለመንግሥት ሠራተኛች ሌላ ጊዜ ለሹማምንቱ ቅድሚያ እሰጣለሁ በማለት በፈለገው ጊዜ እያነሳ የሚሰጥበት አሰራር መስፈኑ
ቆጥቤ የቤት ባለቤት እሆናለሁ የሚለው ተስፋ እንዲጨልም ማድረጉን ዘጋቢያችን ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘ ብዙ ሰዎች ቤቱን ላላገኝ የመንግሥት ፕሮፖጋንዳ መሳሪያ አልሆንም በሚል ከቁጠባው በመሸሽ ላይ ሲሆኑ የተወሰኑት ደግሞ ጨርሶ ከፕሮግራሙ
ራሳቸውን ማግለል መጀመራቸው ታውቋል፡
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar