søndag 3. august 2014

የኢትዮጵያ መንግሥት የታሠሩትን ጋዜጠኞችና ብሎገሮችን እንዲለቅቅ ተጠየቀ



የአውሮፓ ኅብረት


የኢትዮጵያ መንግሥት በሽብር ሕጉ የከሰሳቸውን ጋዜጠኞችና የኢንተርኔት አምደኞች /ብሎገሮች/ ጉዳይ በጥልቅ እያሳሰበው መሆኑን አዲስ አበባ የሚገኘው የአውሮፓ ኅብረት ልዑክ አስታውቋል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ የኢትዮጵያ ፖሊስ አንድ የፎቶ ግራፍ ጋዜጠኛ አሥሮ ላለፉት ሁለት ሣምንታት ክሥ ሳይመሠርት መያዙ ተገልጿል፡፡
አርቲክል 19 እና አምነስቲ ኢንተርናሽናል
የታሠሩት ጋዜጠኞችና ብሎገሮች እንዲለቅቁ የሚያሣድሩትን ጫና እንደሚቀጥሉና በዓለም አቀፍ ተቋማት ዘንድ አቤት ማለት ድረስ እንደሚሄዱ ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ ግልፅ ደብዳቤ “ይድረስ” ያሉት ዓለምአቀፍና ብሔራዊ የመብቶች ተሟጋች ድርጅቶች አስታውቀዋል፡፡

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar