torsdag 14. august 2014

በአፍሮ ታይም፣ ሎሚ፣ እንቁ እና ጃኖ ላይ ክስ ተመሰረተ (የሁሉም ክስ ቻርጅ ደርሶናል)

ባለፈው ሳምንት በአፍሮ ታይም፣ ሎሚ፣ እንቁ፣ ጃኖ እና አዲስ  ጉዳይ የፕሬስ ውጤቶች ላይ ክስ መመስረቱን በቴሌቪዥን እና ሬድዮ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። በዚህ ክስ ምክንያት የአዲስ ጉዳይ ጋዜጠኞች ወደ ኬንያ ሲሰደዱ የተቀሩት አራቱ የፕሬስ ውጤቶች ግን አሁንም አፈናውን ተቋቁመው ለመስራት እየሞከሩ ናቸው። አዲስ ጉዳይ አዘጋጆች ከአገር ስለወጡ በነሱ ላይ የተመሰረተው የክስ ቻርጅ ዝርዝር የለንም። ሆኖም በቀሩት የፕሬስ ውጤቶች ላይ የተመሰረተውን ክስ በዚህ ዘገባ መጨረሻ ላይ ከዚህ በፎቶ አስቀምጠነዋል።
የአፍሮታይምስ ጋዜጣ ማኔጅንግ ዳይሬክተር
የአፍሮታይምስ ጋዜጣ ማኔጅንግ ዳይሬክተር
በነገርዎ ላይ ይህ “ህዝብን በመንግስት ላይ ማነሳሳት” የሚለው ክስ እኛም ኢትዮጵያ በነበርንበት ወቅት ይደርሱን ከነብሩ የክስ ቻርጆች ውስጥ አንደኛው ነው። አሁንም ድረስ ታድያ ይህ አንቀጽ እየተጠቀሰ ክስ መመስረቱ አልቆመም። የሚገርመው ነገር አቃቤ ህጉ ህዝቡ በመንግስት ላይ ስለመነሳሳቱ ወይም እምነት እንዲያጣ ስለመደረጉ አንድም የሰው ምስክር አቅርቦ አያውቅም። ይልቁንም እኛው ራሳችን ያሳተምነውን ጋዜጣ እና መጽሄት በመረጃነት መልሶ ያቀርበዋል። አሁንም እንደተመለክትነው አቃቤ ህጉ መረጃ ብሎ ያቀረበው የፕሬስ ውጤቶቹ ያሳተሙትን ጋዜጣ እና መጽሄት ነው።
የሎሚ መጽሄት አሳታሚ ግዛው ታዬ
የሎሚ መጽሄት አሳታሚ ግዛው ታዬ
“ህዝብ በመንግስት ላይ እንዲነሳሳ በማሰብ…” ብሎ ሰውን መክሰስ በራሱ ችግር አለው። ምክንያቱም ሰው በማሰቡ ብቻ ሊከሰስ አይገባውም። የኢትዮጵያ አቃቤ ህግ ግን እያንዳንዱን ዜና በራሱ መንግድ በመተርጎም ጋዜጠኛው ይህን የጻፈው ህዝብን ለማነሳሳት አስቦ ነው” በማለት ላለፉት ሃያ አመታት በጋዜጠኞች ላይ ክስ እየመሰረተ ነው የሚገኘው።
የእንቁ መጽሄት ስራ አስኪያጅ አለማየሁ ማህተመወር
የእንቁ መጽሄት ስራ አስኪያጅ አለማየሁ ማህተመወር
ዛሬ የሁሉንም ክስ ቻርጆች አንድ ላይ አንድ ቦታ ለማተም የፈለግነው ወደፊት ይህንን የክስ ቻርጅ ለተለያዩ ጉዳዮች ቢፈልጉት እንኳን በቀላሉ እንዲያገኙት በማሰብ ነው።
የጃኖ መፅሔት አሳታሚና ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋዜጠኛ አስናቀ
የጃኖ መፅሔት አሳታሚና ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋዜጠኛ አስናቀ
የሁሉንም ክስ ቻርጅ በፎቶ መልክ ከዚህ በታች አቅርበነዋል። እያንዳንዱን ፎቶ በማተለቅ ማንበብ ይችላሉ። በፌስ ቡክዎም ላይ ለሌሎች ያካፍሉ።

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar