የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ አርበኞችና ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት በተካሄደው የበዓሉ አከባበር ስነ ስርዓት ላይ ለሃገራቸው የተዋደቁ አርበኞች የሚያገኙት የጡረታ ገንዘብ እንዲሻሻል ተጠይቋል ።
ኢትዮጵያ በፋሺሽት ኢጣልያ ላይ ድል የተቀዳጀችበት 73 ተኛ ዓመት በዓል በመላው ኢትዮጵያ ዛሬ ተከብሮ ዋለ ። በዓሉ በተለይም በአዲስ አበባ በተለምዶ አራት ኪሎ ተብሎ በሚጠራው የድል አደባባባይ በሚገኝበት ስፍራ በድምቀት ተከብሯል ። የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ አርበኞችና ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት በተካሄደው የበዓሉ አከባበር ስነ ስርዓት ላይ ለሃገራቸው የተዋደቁ አርበኞች የሚያገኙት የጡረታ ገንዘብ እንዲሻሻል ተጠይቋል ።
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar