mandag 12. mai 2014

የእንግሊዝ ፍርድ ቤት ታሪካዊ የተባለ ውሳኔ አሳለፈ

ፕራይቬሲ ኢንተርናሽናል የተባለው ዜጎችን ከመንግስታዊ ስለላ ለመታደግ የተቋቋመው ድርጅት የእንግሊዝ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣንን ከሶ አስደሳች የፍርድ ውሳኔ ማግኘቱን ገልጿል።
ጋማ ኩባንያን ፊን ፊሸር እየተባለ የሚጠራውን የኮምፒዩተርና የስልክ የመረጃ መጥለፊያ ሶፍት ዌር እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ሰብአዊ መብቶችን ለሚጥሱ አገሮች መሸጡ በካናዳው ሲትዝን ላብ ላብራቶሪ መረጋጋጡን ተከትሎ ፕራይቬሲ ኢንተርናሽናል በአገር ውስጥ ገቢና ጉምሩክ መስሪያ ቤት ላይ ክስ መመስረቱ ይታወቃል።
እንግሊዝ የአገር ውስጥ ገቢ መስሪያ ቤት ከአገሪቱ የሚወጡ ምርቶች በቂ ቁጥጥር ሳይደረግባቸው እንዲወጣ ፈቃድ ሰጥቷል በሚል ነው ክስ የተመሰረተበት።
ፍርድ ቤቱ የአገር ውስጥና የጉምሩክ መስሪያ ቤት አስፈላጊውን መረጃ እንዲሰጥ ውሳኔ አስተላልፏል። ኮምፒተራቸው የተሰለለባቸው ዶ/ር ታደሰ ብሩ ውሳኔው  አስደሳች  ነው ብለዋል።

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar