onsdag 21. mai 2014

በጣሊያን የኢትዮጵያ ኢምባሲ ባለስልጣን መሞታቸው ታወቀ

የአባታቸው ስም ለጊዜው ያልታወቀውና በተጠባባቂ አምባሳደር ማእረግ ደረጃ ሲሰሩ የቆዩት አቶ ፍስሃ ጧት ስራ ከገቡ በሁዋላ መሞታቸው ታውቋል።
ኢሳት ስለ አሟሟታቸው ዝርዝር መረጃ ባያገኝም አንዳንድ ጣሊያን ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ግለሰቡ የሞቱት ከ3ኛ ፎቅ ላይ ራሳቸውን ወርውረው ነው ይላሉ።
ፖሊስ ወደ አካባቢው ደርሶ ምርመራ ካደረገ በሁዋላ ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውንና መሞታቸውን ነዋሪዎች አክለው ተናግረዋል።
ስለ አሟሟታቸው መንስኤ እስካሁን ይህ ነው የተባለ መረጃ አልተገኘም።
ባለቤታቸው ወደ ሮም መምጣታቸውን፣ ሮም የሚገኘው ኢትዮጵያ ኢምባሲ ዝግ ሆኖ መዋሉን ኢሳት አረጋግጧል። ተጨማሪ መረጃ እንደደረሰን ለህዝብ እናቀርባለን።

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar