lørdag 17. mai 2014

ከዞን-9 ታሣሪዎች ስድስቱ ፍርድ ቤት ቀረቡ

ፖሊስ በሽብር አድራጎት እጠረጥራቸዋለሁ ብሏል፤ ፍርድ ቤት የ28 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
የዞን-9 ብሎገሮች በእጅ ብረት ታስረው ወደ ችሎት ሲወሰዱ
የዞን-9 ብሎገሮች በእጅ ብረት ታስረው ወደ ችሎት ሲወሰዱ

  
የታሠሩት ብሎገሮችና ጋዜጠኞች /የፎቶ ምንጭ - ኢንተርኔት/የታሠሩት ብሎገሮችና ጋዜጠኞች /የፎቶ ምንጭ - ኢንተርኔት/

ላለፉት 23 ቀናት ክሥ ሳይመሠረትባቸው ታስረው ከሚገኙት ዘጠኝ የዞን ዘጠኝ የኢንተርኔት ሚድያ ፀሐፊዎች የሆኑ ጋዜጠኞችና አምደኞች ስድስቱ ዛሬ፤ ቅዳሜ፣ ግንቦት 9/2006 ዓ.ም ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡


የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ስምንተኛ ወንጀል ችሎት የጋዜጠኞቹንና የአምደኞቹን ጉዳይ ያየው በዝግ ሲሆን የቀረቡት ጋዜጠኞቹ አስማማው ኃይለጊዮርጊስ፣ ተስፋዓለም ወልደየስ እና ኤዶም ካሣዬ እንዲሁም ሌሎች ሦስት አምደኞች መሆናቸው ታውቋል፡፡
 
የዞን-9 ጋዜጠኞችና ብሎገሮች አራዳ ፍርድ ቤት ቀረቡየዞን-9 ጋዜጠኞችና ብሎገሮች አራዳ ፍርድ ቤት ቀረቡ
ዛሬ ችሎት ያልቀረቡት አምደኞች መቼ እንደሚቀርቡ ለጊዜው በትክክል ባይታወቅም ሰሞኑን ይቀርባሉ የሚል ጭምጭምታ ተሰምቷል፡፡

የስምንት ታሣሪ ጋዜጠኞችና አምደኞች ተከላካይ ጠበቃ አቶ አምሃ መኮንን  እንደገለፁት ፖሊስ ጋዜጠኞቹንና አምደኞቹን በሽብር አድራጎት እንደሚጠረጥራቸው ለችሎቱ አስታውቆ ተጨማሪ ምርመራ ለማድረግ “ሕጉ በሚፈቅደው መሠረት” ያለውን ከፍተኛ ጊዜ የ28 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ጠይቆባቸዋል፡፡
 
አራዳ ፍርድ ቤትአራዳ ፍርድ ቤት
ፍርድ ቤቱም የፖሊስን ጥያቄ ተቀብሎ የ28 ቀናቱን የጊዜ ቀጠሮ መስጠቱንና ጉዳዩንም ለፊታችን ሰኔ 7/2006 ዓ.ም መቅጠሩን ተከላካይ ጠበቃው አቶ አምሃ መኮንን ገልፀዋል፡፡

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar