በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች የሚገኙ ነዋሪዎች እንደገለጹት መንግስት በህወገወጥ መንገድ ተስረተዋል ያላቸውን ቤቶች ያለምንም ተተኪ ቦታና ቤት በማፍረሱ በርካታ ቤተሰቦች ሜዳ ላይ እየተበተኑ ነው።
ኮልፌ አካባቢ አንፎ ሜዳ እየተባለ በሚጠራው ሰፈር ከ2 ሺ እስከ 3 ሺ ቤቶች መፍረሳቸውን ነዋሪዎች ገልጸዋል።
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የሚኖሩ ከ570 በላይ ቤቶች ይፈርሳሉ በመባሉ ነዋሪዎች አቤቱታዎችን እያሰሙ ነው። ልማት አልሙ ተብለን ለረጅም ጊዜ ገንዘብ በማዋጣት መንገድ ማሰራታቸውን፣ ውሃ እና መብራት የመሳሰሉትን አገልግሎቶችን ማስገባታቸውን ገልጸዋል። መንግስት አሁን በደንገት ቦታው ይፈለጋል በማለቱ የነዋሪዎች ህይወት አደጋ ላይ መውደቁን የህዝቡ ወኪሎች ተናግረዋል።
የአዲስ አበባ መስተዳድር ከ15 አመታት ወዲህ የተገነቡ ቤቶችን በማፍረስ ቦታዎቹን ለባለሃብቶች በመሸጥ ላይ ይገኛል።
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar