በደቡብ ክልል የሚገኘው የወልቂጤ ዩኒቨርስቲ የቃጠሎ አደጋ ደርሶበታል። ትላንት ለሊት ላይ በወንዶች ማደሪያ በተነሳው ቃጠሎ ምክንያት የትምህርት ሂደቱ ተስተጓጉሏል።
በእሳት አደጋው የሰው ህይወት ስለመጥፋቱ እስካሁን የደረሰን ዘገባ የለም። በተጨማሪም የ እሳት አደጋው እና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ሲደረግ ከነበረው ረብሻ ጋር ተያያዥነት ያለው መሆኑን ለግዜው አላወቅንም። ሆኖም ለሊቱን የጀመረው የ እሳት አደጋ የወልቅጤ ዩኒቨርስቲ እና የአካባቢው ነዋሪ ላይ ስጋት መፍጠሩ አልቀረም። ተጨማሪ መረጃዎችን ካገኘን ይዘንላችሁ እንመለሳለን።
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar