Addstuwan Ethiopia Begara Wedefit Enaramde
søndag 11. mai 2014
ነዳጅ የያዘ ቦቴ ተገልብጦ አደጋ ደረሰ (አስደንጋጭ ዜና)
የደረሰው የእሳት አደጋ በጣም የከፋ ነበር (ፎቶ በጽዮን)
ዜናውን ከጎተራ ማሳለጫ ወደ ቄራ በጓዝ ላይ የነበረ ነዳጅ የጫነ የፈሳሽ ማመላለሻ መኪና ከነተሳቢውና ተሳፋሪ ጭኖ ከቄራ በኩል ይጓዝ የነበረ ሚኒባስ ታክሲ ሞሐ ለስላሳ መጠጦች ፋብሪካ(ፔፕሲ) ፊት ለፊት ራሳቸውን ከመጋጨት ለማትረፍ ባደረጉት ጥረት ተሳቢው ታክሲው ላይ ተገልብጦ በደረሰ ከፍተነኛ የእሳት አደጋ ሰዎች ተቃጠሉ።በአሁኑ ሰዓት የተቃጠሉ አስክሬኖች እየተለቀመ ነው።ተጎጂዎች ወደ ሆስፒታል እየተወሰዱ ነው። አደጋው ከደረሰ አንድ ሰዓት ሆኖታል።
የዐይን እማኞች እንደተናገሩት ተሳቢው ታክሲው ላይ በወደቀበት ቅጽበት ሚኒባስ ውስጥ ያሉትን ሰዎች ለማትረፍ ርብርብር የተደረገ ቢሆንም ተሳቢው ውስጥ የነበረው ነዳጅ በመፍሰሱ በድንገት ከፍተኛ እሳት ተነስቷል።በዚህን ጊዜ ሁሉም ራሱን ለማዳን መራወጥ ጀመረ።እንደምንም ከሚኒባሱ ውስጥ የወጡ ሰዎች እሳት እየነደደባቸው ራሳቸውን ለማትረፍ ሲሞክሩ ታይተዋል። አደጋውን ተከትሎም በአካባቢው ወዲያው የደረሱ መኪኖች ተጋጭተዋል። አካባቢው በከፍተኛ ጭስ ታፍኖ ነበር።
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar
Nyere innlegg
Eldre innlegg
Startsiden
Abonner på:
Legg inn kommentarer (Atom)
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar