torsdag 7. februar 2013

ኢቲቪ በኦርቶዶክስ የሃይማኖት አባቶች ላይ እንደ ሙስሊሙ ተመሳሳይ ፊልም ለማሰራጨት ዝግጅት ማጠናቀቁን ታወቀ



 በእስር ላይ የሚገኙ የኢትዮጵያ ሙስሊም የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትንበተመለከተ በዛሬው እለት ዶክመንተሪ ፊልም ለማሰራጨት ያስተዋወቀውየኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ የሃይማኖት አባቶች ላይ ተመሳሳይፊልም ለማሰራጨት ዝግጅት ማጠናቀቁን ውስጥ አዋቂ ምንጮችን የጠቀሱዘገባዎች አመልክተዋል፤ቤተ ክህነት ለፊልሙ የገንዘብ ድጋፍ ማድረጏ የተገለፀሲሆን ፤የሃይማኖት አባቶችም በሂደቱ ተዋናይ መሆናቸው ተመልክቶአል።

ሐራ ተዋህዶ የተባለው የኦርቶዶክሳዊያን ድህረ ገፅ እንደዘገበው በኢትዮጵያቴሌቪዥን የተቀነባበረው ፊልም ፓትሪያርክ አቡነ መርቆሪዎስን ጨምሮ በሶስትአባቶች ላይ አተኩሯል።

ፓትሪያልክ አቡነ መርቆሪዮስን ከቀድሞው ስርአት ጋር ግንኙነት አላቸው የሚልውንጀላ የጨመረው ፊልም ብፁእ አቡነ መልክአ ጻዲቅን ለኢትዮጵያ ሙስሊሞች የመብት ጥያቄ ድጋፍ መስጠታቸውን በአሸባሪነት መፈረጁም ተመልክቶል::

በብጹ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ ፓትሪያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያና በቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሀፊ በብጹ አቡነ መልክአ ጻዲቅ እንዲሁም በብፁዕ አቡነ መቃሪዎስ ላይ የተነጣጠረው ይህ ዶክመንተሪ ፊልም በቅርቡም ይቀርባል ተብሎ እየተጠበቀ ነው::

ብጹ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ ነፍጥ ካነሱ ሀይሎች በተልይም ከግንቦት ሰባትና አርበኞች ግንባር ጋር ይሰራሉ ተብ የተወነጀሉ ሲሆን በአሸባሪነትም ተፈርጀዋል ተብሎል::

በዚህ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ይቀርባል በተባለው ፊልም ላይ ንቡረዕድ ኤሊያስ አብርሀና 3 ሊቃነ ጳጳሳት በአስረጂነት መካተታቸውም ተመልክቶል:: ሌሎች አባቶችም ፍቃደኛ አለመሆናቸውም ከዘገባው ለመረዳት ተችሎል:;

የፊልሙ ርዝማኔ 1 ፡ 30 ሲሆን በሁለት ክፍል ይቀርባል ተብሎ እየተጠበቀ ነው::

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar