torsdag 7. februar 2013

የባለራእይ ወጣቶች ማህበር የአመራር አባላት ማደኛ ወጣባቸው



ከአመራሩ ለመረዳት እንደቻለው፣ የፍርድ ቤት የእስር ትእዛዝ የወጣባቸው በማህበሩ ሊ/መንበር በወጣት ሀብታሙ አያሌው፣ በምክትሉ ሚኬኤል አለማየሁ እና በህዝብ ግንኙነት ሀላፊው በብርሀኑ ተክለያሬድ ላይ ነው።

ወጣት ብርሀኑ በፖሊስ ተይዞ እስር ቤት የገባ ሲሆን፣ ሊቀመንበሩና ምክትሉ ዜናውን እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ አልተያዙም። ግለሰቦቹን በግንቦት7 ስም ለመክሰስ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ለማወቅ ተችሎአል።


በቅርቡ የመንግስት የደህንነት ሀይሎች የማህበሩ የአመራር አባል የሆነች ወጣትን መርፌ በመውጋት አፍነው ከወሰዱዋት በሁዋላ፣ አመራሮቹ ከግንቦት7 ጋር ይገናኙ ነበር ብለሽ ተናገሪ እየተባለች መደብደቡን መዘገባችን ይታወሳል።

ኢሳት ለማረጋጋጥ እንደቻለው ከብዙ ማንገራገር በሁዋላ ሆስፒታሉ ወጣቷ በመርፌ መወጋቷን የሚያሳይ የህክምና ማስረጃ ሰጥቷታል።

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar