mandag 28. juli 2014

ሕወሓት አቶ አንዳርጋቸውን በቲቪ ስታቀርብ ራሷን በራሷ ያጋለጠችባቸው 4 ቅጥፈቶች

ስንታየሁ ከሚኒሶታ
እንደተጠበቀው በሕወሓት መንግስት በሚመራው የኢትዮጵያ ፖሊስ ፕሮግራም ላይ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እንዲቀርቡ ተደርጓል። የአቶ አንዳርጋቸው በቲቪ መቅረብ ከዚህ ቀደም በአንዷለም አራጌ፣ በብርቱካን ሚደቅሳ፣ በደበበ እሸቱ፣ በአቡበከር አህመድ ላይ የተለመደ በመሆኑ ብዙም አስገራሚ አልሆነም። ሆኖም ግን ቪድዮውን ልብ ብሎ ለተመለከተው ወያኔ እንዳሰበው ትርፍ ሳይሆን የበለጠ ኪሳራ እንዳገኘበት ለመረዳት ችያለሁ። ለዚህም ነው ወያኔ አቶ አንዳርጋቸውን በቲቪ ስታቀርብ የረሳቻቸው 4 ቅጥፈቶች ስል ለዚህ አስተያየቴ ር ዕስ የሰጠሁት።
ወያኔ አቶ አንዳርጋቸውን በቲቪ ስታቀርብ ራሷን በራሷ ያጋለጠችባቸው 4 ቅጥፈቶች1ኛ. ቪድዮው በጣም ኤዲት እንደተደረገ ያስታውቃል
ሕወሓት ያዘጋጀው የቪድዮ ካሜራ ማንና አቀናባሪው ደንጋጣ እንደሆነ ቪድዮው ያስታውቅበታል። በጣም ተቆራርጦ መቀጣጠሉ ከማስታወቁም በላይ ቢያንስ ከዚህ የተሻለ ኤዲቲንግ ሥራ መሥራት ይችል የነበረ ቢሆንም ይህን ባለማድረጉ ለፕሮፓጋንዳ ሥራ የተዘጋጀውን ቪድዮ ኪሳራ ላይ ጥሎታል። ቪድዮ አቀናባሪው ሆን ብሎ ሕዝብ መቆራረጡን እንዲያውቅ ያደረገ ከሆነ ልናደንቀው የሚገባ ሲሆን፤ ሆኖም ግን ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ከሆነ ይህ ቪድዮ ቅንብሩ አይመጥንም።
2ኛ. ቪድዮው በተደጋጋሚ የተቀረጸ መሆኑ ያስታውቃል።
ቪድዮውን ልብ ብላችሁ ከተመለከታችሁት በተለያየ ጊዜ የተቀረጸ መሆኑ ያስታውቃል። ይህም የሚፈልጉትን ለማግኘት ብዙ ማይል እንደተጓዙ ያሳያል። ምንም እንኳ ተመሳሳይ ቀን የተቀረጸ ለማስመሰል አንድ ዓይነት ቱታ ቢያስለብሱትም 3 የተለያዩ የውስጥ ቲሸርቶች ይታያሉ። አንዱ ነጭ፣ ሌላኛው ሰማያዊና 3ኛው ቀይ ቲሸርቶች። በሌላ በኩል ቪድዮው ሊያልቅ ሲል የምታዩት ቱታ ደግሞ የተለየ ነው።
3ኛ. ውሃዋ የለችም።
እንግዲህ ወያኔ ሌላው የረሳችው አቶ አንዳርጋቸውን በጥሩ ሁኔታ እንዳሉ ለስመሰልና ንጹህና የተገዛ ውሃ አጠገባቸው አስቀምጣ ነበር። ቪድዮው ግን በተለያየ ጊዜ የተቀረጸ ለመሆኑ የሚያስታውቀው በሌላኛው የቪድዮ ክፍል ውስጥ ውሃዋ የለችም።
4ኛ. ቶርች የሚደረግ ሰው እንዳለ ይሰማል
ይሄ ትልቁ ወያኔን ራሱን በራሱ ያጋለጠበት ክፍል ነው። ቪድዮው ተጀምሮ ከ1 ደቂቃ በኋላ ያለውን ስትመለከቱት አንዳርጋቸው በሚናገርበት ወቅት ከጀርባው የድብደባና የሲቃ ድምጽ ይሰማል። ይህም ምን ያህን በወያኔ እስር ቤቶች የሚደረጉትን ቶርቸሮች የሚያሳይ ነው። ይህ ለወያኔ ትልቁ ኪሳራ ሊባል የሚችል ደካማው የፕሮፓጋንዳ ቪድዮው ሊባል ይችላል። ራሱን በራሱ ቶርቸር አድራጊ መሆኑን መስክሯልና ይህንን የሚመለከታቸው አካላት ለዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቶች ማሳየት ይኖርባቸዋል፤ አንዳርጋቸውም እንዲህ ያለው ቶርቸር እንደደረሰበት ማሳያ ሊሆነን ይችላል እላለሁ።
ቪድዮውን ተመልከቱትና ፍረዱ። በመጨረሻም ለወያኔ የማስተላልፈው መል ዕክት አለኝ – እንደሁልጊዜው ለዛሬውም አልተሳካም!

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar