torsdag 10. juli 2014

ታዋቂዎቹ ፖለቲከኞች በማእከላዊ እስር ቤት መታሰራቸው ታወቀ

በፌደራል ፖሊሶች እየተደበደበ ወደ አልታወቀ ስፍራ ተወስዶ የነበረው ታዋቂው ፖለቲከኛና ጸሃፊ አብርሃ ደስታ ማእከላዊ እስር ቤት መታሰሩ ታውቋል። የአብረሃ መኖረያ ቤት በፖሊሶች እንደተፈተሸም ለማወቅ ተችሎአል።
የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ወጣት ሃብታሙ አያሌው፣ የፓርቲው ምክትል የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ ዳንኤል ሽበሺ እንዲሁም የሰማያዊ ፓርቲ ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ አቶ የሽዋስ አሰፋ ዛሬ ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ ሲገለጽ፣ ዜናውን እስካቀረብንበት ጊዜ ስለተከፈተባቸው ክስ ለማወቅ የተደረገው ጥረት አልተሳካም።
በኢትዮጵያ ሃሳባቸውን በነጻነት በመግለጻቸው እንዲሁም የተቃውሞ የፖለቲካ ድርጅቶችን በመቀላቀላቸው የሚታሰሩ ኢትዮጵያውያን ቁጥር ከመቼም ጊዜ በላይ ጨምሯል።

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar