1 ሺህ 435ኛው የኢድ አልፈጥር በመላው የእስልምና ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ ነው። በአዲስ አበባ ስታዲየም የነበረው
ክብረበአል በሰላም የተጠናቀቀ ሲሆን፣ ድምጻችን ይሰማ ምንም አይነት ተቃውሞ እንዳይካሄድ ባዘዘው መሰረት፣ በአዲስ አበባ ስታዲዮም ተቃውሞ ሳይካሄድ ቀርቷል።
የኢህአዴግ የጸጥታ ሃይሎች ሰሞኑን በወሰዱት ጠንካራ እርምጃ በርካታ ሙስሊሞች የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን፣ ቁጥራቸው በውል ያልተወቀ ሙስሊም ዜጎች
በእስር ቤት እየማቀቁ ይገኛሉ።
በኢድ አል ፈጥር ላይ ተቃውሞ ከተነሳ የኢህአዴግ ደህንነቶች እርምጃ ለመውሰድ ተዘጋጅተው እንደነበር መዘገቡ ይታወሳል።
ልቁማን የኢትዮጵያ ቤልጂየም የሙስሊም ማህበር ( ልብማ) ለኢሳት በላከው መግለጫ መንግስት ባለፈው አርብ በሙስሊም ኢትዮጵያውያን ላይ የወሰደውን
እርምጃ አውግዟል።
ማህበሩ በመግለጫው ህዝበ ሙስሊሙ ላነሳቸው የመብት ጥያቄዎች የመንግስት ምላሽ ግድያ፣ ድብደባ፣ እስራትና ንቀት መሆኑን አስታውሷል። የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ
አባላትን ጨምሮ በሺዎች የሚቆጠሩ መታሰራቸውን፣ ብዙ ንጹህ ሙስሊሞች መገደላቸውን፣ አንዳንዶች አገር ጥለው መሰደዳቸውን እንዲሁም ሌሎች አካል ጉዳተኞች ቆነው
መቀመጣቸውን ጠቅሷል።
የሙስሊሙ ማህበረሰብ ትግሉን ከመቀጠል ውጭ ሌላ አማራጭ እንደሌለው ልብማ ጠቅሶ፣ ድምጻችን ይስማ በኢትዮ-ቴልኮ ላይ የጣለውን የአንድ ቀን ማእቀብም በማድነቅ ተመሳሳይ
አርምጃዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቋል። በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ከሙስሊሞች ጎን እንዲቆሙ፣ መላው የኢትየጵያ ህዝብም በሚወሰዱት እርምጃዎች ተባባሪ እንዲሆን ማህበሩ ጥሪ አቅርቧል።
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar