በጁምዓው ተቃውሞ የተያዙ ንፁሀን ሙስሊሞች ወደ ቂሊንጦ ማረሜያ እየተዘዋወሩ ነው። በማረሜያ ቤቱም ከፍተኛ የሆነ የቦታ እጥረት ተከስቷል።
(ሃይደር አሊ እንደዘገበው)
ጁምዓ በ11/11/2006 በህዝበ ሙስሊሙ ላይ በአንዋር መስጂድ የመንግስት ሀይሎች በወሰዱት ኢ-ሰብዓዊነት የተሞላበት እርምጃ ታስረው ከነበሩ ሙስሊሞች አብዛኛዎቹ ጁምዓ ሌሊቱን ተደብድበውና የተወሰኑት በገንዘብ ዋስ እየተለቀቁ ሲሆን በዕለቱ ተይዘው ከነበረው ሰላማዊ ሙስሊሞች ውስጥ የተወሰኑት ተመርጠው ወደ ቂሊንጦ ማረሜያ ቤት እየተዘዋወሩ እንደሆነና ለእነዚሁ ንፁሀን ወንድምና እህቶቻችን የሚሆን በቂ ቦታ ማረሜያ ቤቱ ስለሌለው የቦታ እጥረት መከሰቱ ታውቋል።

ወደ ቂሊንጦ ማረሜያ ቤት ከተዘዋወሩት ንፁሀን እህትና ወንድሞቻችን መሀከል 40 የሚሆኑት ዞን 2 ውስጥ የገቡ ሲሆን በዞኑ ውስጥ ለገቡት በቂ ቦታ ባለመኖሩ በዞኑ ውስጥ ለአንድ ታራሚ በተዘጋጀው ቦታ ለሁለት እየተኙም ቦታው ሊበቃ ባለመቻሉ መሬት ላይም ጭምር ለመተኛት እየተገደዱና በማረሜያ ቤቱ ውስጥ ያሉ ታራሚዎችን ጨምሮ ለከፍተኛ እንግለት እየተዳረጉ እንደሆነ ታውቋል።
ወደ ዞን ሶስትና አንድ የገቡት ታራሚዎች ቁጥር ለጊዜው ያልታወቀ ሲሆን በዞን ሶስትም ውስጥ ለታራሚ የተዘጋጀው ቦታ ባለመብቃቱ በአንድ መኝታ ላይ ለሁለት እየተኙ እንደሆነ የታወቀ ሲሆን በዞኑ ያሉ ታራሚዎችም ለእንግልት እየተዳረጉ እንደሆነ ታውቋል።
ንፁሀንን ያለ ጥፋታቸው አስሮ ማንገላታቱ ይቁም!
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar