søndag 13. juli 2014

አብርሃ ደስታ – ከትግራይ አዲስ አበባ ማዕከላዊ እስር ቤት ገባ

በትግራይ የሚደረጉ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በመጻፍ እና በመተቸት ይታወቃል – አብርሃ ደስታ። በትጋይ የሚገኙት ሰዎች የአብርሃ ደስታን ሃሳብ – በሃሳብ ማሸነፍ ሲያቅታችው አስረውታል። ከታሰረ በኋላ ወዴት እንደተወሰደ ለማወቅ አልተቻለም ነበር። ዛሬ ያገኘነው መረጃ ግን አብርሃ ደስታ ከትግራይ ወደ አዲስ አበባ ማዕከላዊ እስር ቤት ተዛውሮ እንደሚገኝ ለማወቅ ችለናል።\
ይህ በ እንዲህ እንዳለ፤ በሚቀጥለው ሳምንት እሁድ በራያ እና አዘቦ የሚደረገውን የአረና ፓርቲ ስብሰባ፤ “ዘመቻ አብርሃ ደስታ” ማለታቸውውን አሳውቀዋል። አረና የትግራይ ፓርቲ እንደገለጸው ከሆነ፤ ዓረና-መድረክ እሁድ 06 / 11 / 2006 ዓ/ም በራያ ዓዘቦ ወረዳ ሞኾኒ ከተማ “ዘመቻ ኣብረሃ ደስታ” የሚል መፈክር ያለበት ህዝባዊ ስብሰባ ያካሂዳል።
ዓረና-መድረክ ፖሊሲው፣ ስትራተጂውና ኣማራጭ ሃሳቡ ከራያ ዓዘቦና ኣከባቢው ህዝብ ለመወያየትና ለማስተዋወቅ ህዝባዊ ስብሰባ ጠርተዋል።
ዓረና-መድረክ የሃገራችን የፍትህ፣ ዲሞክራሲ፣ መልካም ኣስተዳደር፣ ሁላቀፍ ልማት፣ የሚድያ ነፃነት፣ ወዘተ ተግዳረቶች በማቅረብ ለነዚህ ችግሮች መፍትሄ ኣማራጭ ሃሳቦች በማቅረብ ወደፊት ሃገራችን የምትመራበት ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ምን መምሰል እንዳለበት፣ ሰለማዊ የስልጣን ሽግግር እውን የሚሆንበት ኣግባብ፣ ባለፈው 17 የትጥቅ ትግል የተከፈለ መስዋእትነትና በኣሁኑ ሰዓት የተገኘው ለውጥ ምን እንደሚመስል ከራያ ህዝ ጋብ እንወያያለን።

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar