ከእስከዳር ጋር የሚኖረኝ ቀጠሮ የአሁኑን የአንዳርጋቸው ጽጌን ጉዳይ ለመነጋገር ቢሆንም፤ ሳልወድ በሃሳብ ወደኋላ እንድመለስ መገደዴ አልቀረም። በምርጫ 97 ወቅት (ከዘጠኝ አመታት በፊት) አንዳርጋቸው ጽጌ በየእለቱ ወደ ቅንጅት ቢሮ በማምራት የማደራጀት እና የቅስቀሳ ስራዎችን ያከናውን ነበር። የሰኔ የመጀመሪያ ሳምንት ግን ወጣቶች መንገድ ላይ የሚረሸኑበት፤ የቅንጅት ደጋፊዎች የተባሉ ሰዎች በገፍ እየታፈኑ ወህኒ ያሚጋዙበት ወቅት ሆነ።
አንድ ቀን ለአንዳርጋቸው ጽጌ ስልክ ተደወለለት። ጓደኛው ዶ/ር ስለሺ ነበር። “ተገናኝተን ቡና እንጠጣ” አለውና አንዳርጋቸው ከቤት ወጣ። እንደወጣም ቀረ – አልተመለሰም። መንገድ ላይ የጠበቁት የወያኔ ደህንነት አባላት ዶ/ር ስለሺን ጨምረው ወደ ዝዋይ እስር ቤት ወሰዷቸው። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar