ዘረኛው የትግሬ-ወያኔ ቡድን በሰሜን ጎንደር የዐማራ ሕዝብ ላይ የፈጸመው የዘር ማጽዳት እና የዘር ማጥፋት ወንጀል
የትግሬ-ወያኔ ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት አቅዶ ሲነሳ፣ የግቡ መረማመጃ ያደረገው የኢትዮጵያዊነት መገለጫ የሆኑ ተቋሞችን፣ ኃይማኖቶችን፣ ዕሴቶችን እና በተለይም «ዐማራ» የተሰኘውን ነገድ ተወላጆች ነጥሎ ማጥፋት የሚል ሥልት በመከተል እንደሆነ ይታወቃል። በዚህም መሠረት የጥፋቱ ቅድሚያ ዒላማ ያደረገው ለትግራይ ሕዝብ በችግሩ ጊዜ ደራሽ እና የተራበ አንጀታቸውን ዳሳሽ በሆነው የወልቃይት፣ የጠገዴ፣ የጠለምትና የሠቲት ወረዳዎች ሕዝብ ላይ ነው። ወያኔ በእነዚህ የትግሬ አዋሣኝ ወረዳዎች ሕዝብ ላይ የጥፋት ክንዱን የዘረጋው በሦስት መሠረታዊ ምክንያቶች ነው።
የመጀመሪያውና ታላቁ ምክንያት የእነዚህ ወረዳዎች ሕዝብ ዐማራ በመሆኑ እና የትግራይ አዋሳኝ ስለሆነ የትግራይን ታሪክ ክፉውንም ሆነ ደጉን ጠንቅቆ የሚያውቅ በመሆኑ ነው። በዚህም ምክንያት የዚያ አካባቢ ሕዝብ የትግሬ-ወያኔ ለተነሳለት ፀረ-ኢትዮጵያ እና ፀረ-ዐማራ እንቅስቃሴ የማይተኛ እንደሆነ ስለሚረዳ ይህን ሕዝብ ብቻውን አቁሞ ማጥፋት ለወደፊቱ ግሥጋሴው ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥርላቸው በማመን የችግር ጊዜ ደራሻቸውን ሕዝብ ያለርኅራኄ ጨፍጭፈውታል።
ሁለተኛው ምክንያት «ታላቋን ትግራይ» ለመመሥረት ባላቸው ዕቅድ ለውጭ ግንኙነታቸው መውጫ መግቢያ እንዲሆናቸው ከሱዳን ጋር የሚዋሰኑትን እነዚህን ወረዳዎች ወደ ትግራይ ማጠቃለል ስለነበረባቸው ነው። ሆኖም የአካባቢው ሕዝብ «ነገዳችን ዐማራ፣ ጠቅላይ ግዛታችን ጎንደር ነው።» እያለ እንዳያስቸግራቸው በቅድሚያ ነባር ነዋሪውን ጎንደሬ አጥፍቶ በሠፋሪ ትግሬ ማስያዝ ለዓላማቸው ሥምረት ያገለግላል ብለው በማመናቸው ነው።
ሦስተኛው ምክንያት የሠቲት፣ የወልቃይት፣ የጠገዴ፤ እና የጠለምት ወረዳዎች ለሠፋፊ የእርሻ በተለይም ለጥጥ፣ ለሰሊጥ፣ ለማሽላ፤ ለዱር ሙጫ፣ ወዘተርፈ ምርት የሚያመች የለም እና ሠፊ መሬት ባለቤት በመሆኑ ነው። ስለዚህ የእነዚህ የሚያጓጉ የተፈጥሮ ኃብቶች ተጠቃሚ ለመሆን ተቀናቃኙን የጥንት ነዋሪውን ሕዝብ የግድ ማጥፋት አለብን ብለው በማመናቸው ነው።
ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) በዐማራ ነገድ አባሎች ላይ የተቀነባበረ የዘር ማጽዳት ወንጀል መፈጸም የጀመረው ድርጅቱ ገና «ተጋድሎ ሓርነት ሕዝቢ ትግራይ (ተሓሕት)» ተብሎ ይጠራበት ከነበረበረበት የጨቅላነቱ ዘመን ጀምሮ እንደሆነ የድርጅቱ ታሪክ ያስረዳል። በተለይም የትግራይ አዋሣኝ በሆኑት የሰሜን ጎንደር ታሪካዊ አካሎች በነበሩት ወረዳዎች ነዋሪ የሆኑ ዐማራዎችን ለማጥፋት ተሓሕት-ሕወሓት ፕሮግራም ነድፎ መንቀሳቀስ የጀመረው ከ፲፱፻፷፯ ዓ.ም. ጀምሮ እንደሆነ የድርጅቱ ነባር አባሎች ያስረዳሉ። የሰሜን ጎንደር ለም እና ድንግል ወረዳዎች የሚባሉት፦ ወልቃይት፣ ሠቲት፣ ላይ እና ታች አርማጭሆ፣ ጠገዴ እና ጠለምት ናቸው። በሕወሓት ታሪክ ውስጥ «የዲማ ኮንፈረንስ» በመባል የሚታወቀው እና ከ፻፶ (አንድ መቶ ሃምሣ) ያላነሱ አባላቱ ተካፋይ በሆኑበት በየካቲት ወር ፲፱፻፷፰ ዓ.ም. «ጸደቀ» የተባለው ፕሮግራም ወልቃይትን፣ ሠቲት፣ ጠገዴን እና ጠለምትን ከዐማራ በማጽዳት ወረዳዎቹን ወደ ትግራይ መጠቃለል እንዳለባቸው ያስገነዝባል።
ይህ ፕሮግራም ዐማራውን ከማውገዝ አልፎ፣ በትግሬ ደመኛ ጠላትነት በመፈረጅ በግልፅ ቋንቋ «የትግላችን ዓላማ ፀረ-የዐማራ ብሔራዊ ጭቆና ነው» ይላል። ከዚህ በተጨማሪም ፕሮግራሙ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት፣ ብሔራዊ ጥቅም እና የሕዝቧን አንድነት በእጅጉ የሚጎዳ ብቻ ሳይሆን፣ አገሪቱ እንደአገር እንዳትቀጥል የሚያደርግ ዓላማ ያለው መሆኑ በፕሮግራሙ መሠረት ባለፉት ፳፫(ሃያ ሦሥት) ዓመታት በመፈጸም ላይ ያሉት ተግባሮች ሁነኛ እማኖኞችና ነቃሾች ናቸው።
በ፲፱፻፷፰ ዓ.ም. የጸደቀውን የድርጅቱን ፕሮግራም ተግባራዊ ለማድረግ አርከበ ዕቁባይ «ወደ ታላቋ ትግራይ ረፐብሊክ ሊካተቱ ይገባል» የተባሉትን ከጎንደር ወልቃይትን፣ ጠገዴን፣ ጠለምትን፣ ሠቲት፤ እንዲሁም ከወሎ ክፍለሀገር ደግሞ ራያና ቆቦን፣ አላማጣን፣ ወልድያን፣ ጨምሮ እስከ አሸንጌ ኃይቅ ድረስ ያሉትን ሥፍራዎች የሚያካትት ካርታ አዘጋጀ (ተያያዥ ካርታዎችን ከ፩-፬ ይመልከቱ)። በዚህ ሁኔታ ከኢትዮጵያ ተገንጥላ የምትመሠረተው «የትግራይ ረፐብሊክ» ከሱዳን ጋር የሚያገናኛት የመሬት አካል እንድታገኝ ሆነ። በዚህም መሠረት በ፲፱፻፷፱ ዓ.ም. ተሓሕት-ሕውሓት ያለ የሌለ ኃይሉን ከጎንደር ክፍለ ሀገር ነጥቆ ወደ ትግራይ ባካለላቸው ጥንተ-ነዋሪ የዐማራ ሕዝብ ላይ የጥፋት ክንዱን አነሳ።
ከሁሉ አስቀድሞ መታወቅ ያለበት ጉዳይ የትግሬ-ወያኔ ዐማራን ማጥፋት የጀመረው ኢትዮጵያዊነትን በሁለንተናዊ መልኩ ከትግራይ ሕዝብ አዕምሮ እንዲጠፋ ካደረገ እና የዓላማው ተቃዋሚ የሆኑ የራሱን ነገድ አባሎች ከትግራይ ምድር ካጸዳ በኋላ ነው። ይህ በዚህ እንዳለ በ፲፱፻፷፱ ዓ.ም. የተሓሕት-ሕወሓት አመራር አባላት የሆኑት ስብሐት ነጋ፣ አረጋዊ በርሄ፣ ዐባይ ፀሐዬ፣ ሥዩም መሥፍን፣ ስዬ አብርሃ እና አውአሎም ወልዱ «በትግራይ ክፍለሀገር ውስጥ የሚኖሩ ዐማሮች፣ ኦሮሞዎች እና የሌሎችም የኢትዮጵያ ነገዶች ተወላጆች ከትግራይ መሬት ለቀው ይውጡ፤ ትግራይ የትግሬዎች ብቻ ናት!» ብለው ሲወስኑ በወቅቱ ይህን ውሣኔ ተቃውመው የቆሙት ግደይ ዘርዓፅዮን እና ዶክተር አታክልቲ ቀጸላ ብቻ እንደነበሩ ስለሁኔታው የሚያውቁት አቶ ገብረመድህን አርአያ በተለያዩ አጋጣሚዎች አሣውቀዋል። ያ ውሳኔ ተግባራዊ ሆኖ፣ ዛሬ ትግሬዎች ትግራይን በብቸኝነት፣ ቀሪዋን ኢትዮጵያ ደግሞ በገዥነት ተቆጣጥረው ይገኛሉ።

Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar