ዛሬ አርብ ጁምዓ ነበር። የረመዳን ጾም እንደመሆኑ መጠን፤ ለስግደት በጣም ብዙ ሺህ ህዝብ ወደ ታላቁ አንዋር መስጊድ ሄዷል። ከኢህአዴግ ጋር ተመሳጥረው ሙስሊም ወንድሞቻቸውን አሳልፈው በሰጡ እና የ”ኮሚቴ አባሎች” ይፈቱ በሚሉ ሰላማዊ ሙስሊሞች መካከል የተፈጠረው ውጥረት አሁንም እንዳለ ነው። ኢህአዴግ መራሹ መንግስትም ይህን የመከፋፈል አጋጣሚ በመጠቀም፤ “ድምጻችን ይሰማ” የሚሉ ወገኖችን በመደብደብ እና በማሰር መፍትሄ ለማግኘት የሚያደርገውን ጥረት ቀጥሏል።
ይህ አይነቱ በጨለምተኝነት ላይ የተመሰረተ የኢህአዴግ ድርጊት፤ በህዝብ ላይ የሚተገበር “ጥቁር ሽብር” ከማለት ውጪ ሌላ ትርጉም የሚሰጠው አይደለም። ለዚህም ነው በርእሳችን ላይ “ጁምዓ በፖሊስ ጥቁር ሽብር ተናወጠ” ያልነው። ይህ ሽብር እና ነውጥ ምን ይመስል እንደነበር የበለጠ ለመረዳት በስፍራው ተገኝተው፤ የአይን ምስክር ሆነው ዘገባቸውን ያቀረቡትን የጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ እና የጌታቸው ሽፈራውን ዜና መመልከት በቂ ነው። በቅድሚያ ጋዜጠኛ ኤልያስን ዘገባ እናስቀድማለን።
በብጥብጥ የተቋጨው የጁምዓ ስግደት በአንዋር መስጊድ (ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ)
መጽሐፍ ሳነብ ስለነበር በጣም አምሽቼ የተኛሁት፡፡ ጠዋት አረፍጄ ተነሳሁ፡፡ ቁርሴንም ሳልበላ ወደ አንዋር መስኪድ አመራሁ፡፡ ከፒያሣ ጀምሮ መንገድ የተዘጋጋ ስለነበረ፤ ከሦስት ሙስሊም ወንድሞቼ ጋር አንድ ላዳ ታክሲ ኮንትራት ይዘን አቆራረጥን ታላቁ አንዋር መስኪድ ደረስን፡፡ አካባቢው በሙስሊሙ ማኅበረሰብ ተሞልቷል፡፡ አብዛኛው ምንጣፍ እና ካኪ ወረቀት አንጥፈው ለጁምዓ ጸሎት እና ለስግደት ተቀምጠዋል – አስፋልቱን ጭምር ተጠቅመውበታል፡፡ ለመቀመጫ ቦታ ያላገኙት ቆመው ከመስኪዱ በአረብኛ ቋንቋ የሚነገረውን ምስጋና (ትምህርት) በጥሞና እየተለታተሉ ነው፡፡
በርከት ያሉ ፖሊሶች በመስኪዱ አቅርቢያ የተለያዩ ቦታዎች ላይ ቆመዋል – ረዥም ሽመል ይዘዋል! እኔም እንደ ጋዜጠኛ የሙስሊሞቹን ሰላማዊ ተቃውሞ ለመከታታል በማሰብ ነው አንዋር መስኪድ የተገኘሁት፡፡ ከመስኪዱ ራቅ ብዬ በመቆም ሁኔታውን መከታተል ጀመርኩ፡፡ ነገሮች ሰላማዊ ነበሩ፡፡ ከሥፍራው ከተገኘሁ ከአሥራ አምስት ደቂቃ በኋላ በመስኪዱ ዋና በር አካባቢ ወረቀቶች ወደ ላይ ይበተኑ ጀመር፡፡ ሦስት፣ አራት ቦታም ተመሳሳይ ወረቆች መበተናቸውን ቀጠሉ፡፡
ወዲያው፣ ከርቀት ከመስኪዱ በስተቀኝ በኩል ረብሻ ነገር ተመለከትኩ፡፡ ድንጋይ ሲወረውር እና ፖሊሶች ዱላ እንደያዙ ሲሯራጡም ማየት ችያለሁ፡፡
አፍታም ሳይቆይ አካባቢው በሰዎች ሩጫ፣ በረብሻና በፖሊሶች ማሳደድ ትርምስምሱ ወጣ፡፡ ብዙ ሰው በአካባቢው ወደሚገኙ የመኖሪያ እና የንግድ ቤቶች እየዘለለ መግባት ጀመረ፡፡ ነገሮች ለአፍታ ጋብ ያሉ ቢመስሉም ሁኔታው በድጋሚ ተቀሰቀሰ፡፡ በርካታ ፖሊሶች ወደ መኖሪያ ሰፈሮች እና ግቢዎች ውስጥ ዱላቸውን ይዘው በመግባት ሰዎች ማባረር፣ ማሳደድና በዱላ መማታት ጀመሩ፡፡
እኔም ከሦስት ፖሊሶች ጋር ከአንድ መኖሪያ ግቢ ውስጥ ተፋጥጬ ነበር፡፡ አንድ ዱላ ሲሰነዘርብኝ በእጄ ተንቀሳቃሽ ኮምፕዩተር (ላፕቶፕ) ይዤ ስለነበረ እሱ ከፍ በማድረግ ዱላው የላፕቶፕ ቦርሳዬ ላይ አረፈ፡፡ የቀኝ እጄ ጠቋሚ ጣት ግን ከበትሩ ማምለጥ ሳይቻለው ቀረ፡፡
… ከበሩ ፊት ለፊት የነበሩት ፖሊሶች ጥለውን ሄዱ፡፡ ወደ አሜሪካን ግቢ በጉራንጉር ውስጥ አልፌ ብሄድም ድብደባው እና ወከባው በዚህ አለ፡፡ ብዙ ወጣቶች ተደብድበው፣ ጭንቅላታቸው ተበረቃቅሶ ደም በደም ሆነው ተመልክቻለሁ፡፡
በዛሬው ዕለት ምስቅልቅሏ የወጣውን መርካቶ በቻልኩት አቅም ለማየት ችያለሁ፡፡ ሱቆች ተዘጋግተዋል፡፡ አንዋር መስኪድ በፌዴራል ፖሊስ ባልደረቦች እና መኪኖች ተከብቦ ነበር፡፡ አድማ በታኝ ፖሊሶችም በምዕራብ ሆቴል ቁልቁል በሰልፍ ሲያዘግሙ እና ሰፊዋ መርካቶ በፌዴራል ፖሊሶች ተወርራ ነበር፡፡
በዛሬው ዕለት ምስቅልቅሏ የወጣውን መርካቶ በቻልኩት አቅም ለማየት ችያለሁ፡፡ ሱቆች ተዘጋግተዋል፡፡ አንዋር መስኪድ በፌዴራል ፖሊስ ባልደረቦች እና መኪኖች ተከብቦ ነበር፡፡ አድማ በታኝ ፖሊሶችም በምዕራብ ሆቴል ቁልቁል በሰልፍ ሲያዘግሙ እና ሰፊዋ መርካቶ በፌዴራል ፖሊሶች ተወርራ ነበር፡፡
————————
የጋዘጠኛ ኤልያስ ገብሩ ዘገባ እዚህ ላይ ያበቃል። ከስፍራው ሌላም ዘገባ ደርሶናል።ጌታቸው ሽፈራው በስፍራው ተገኝቶ ያየው እና የታዘበውን እንዲህ አስቀምጦታል።
ጭካኔ በአንዋር መስጊድ!
እነዛ ሰላማዊ ሙስሊም ወጣቶች ያለ ርህራሄ እንደዳጉሳ ሲወቀጡ አየሁ፡፡ ህጻን፣ ሽማግሌ፣ ሴት፣ ርጉዝ ሳይባል
በጭካኔ ተደበደቡ፡፡ ታፈሱ! አንዱ ደብድቦ ያሳለፈውን ሌላኛው በተራው ይቀበለዋል፡፡ ተዝለፍልፎ የወደቀ የወደቀበት ላይ ይወቀጣል፡፡ ወጣቶቹ አገር ሰላም ነው ብለው ለመስገጃ የወሰዷቸው መስገጃ ወረቀቶች ደም
በደም ሆነዋል፡፡
በጭካኔ ተደበደቡ፡፡ ታፈሱ! አንዱ ደብድቦ ያሳለፈውን ሌላኛው በተራው ይቀበለዋል፡፡ ተዝለፍልፎ የወደቀ የወደቀበት ላይ ይወቀጣል፡፡ ወጣቶቹ አገር ሰላም ነው ብለው ለመስገጃ የወሰዷቸው መስገጃ ወረቀቶች ደም
በደም ሆነዋል፡፡
ፖሊስና ደህንነቶች በድብደባው ቢሳተፉም ያለ ርህራሄ ወጣት አዛውንቱን በቆመጥ የተደባደቡት ከየ
ጎዳናው የተለቀሙት ወጣቶች ናቸው፡፡
አንዳንዶቹ የጎዳና ተዳዳሪዎች ለመሆናቸው አለባበሳቸው በግልጽ ያሳያል፡፡ ፖሊስ አትደብድቡ እያላቸው
እንኳን የሚሰሙ አይደለም፡፡ ሽጉጥ ማቀባበል የማይችሉት ሽጉጥ ተሰጥቷቸው ሲያስፈራሩ ካርታው ሲወርድባቸው ተመልክቻለሁ፡፡
ጎዳናው የተለቀሙት ወጣቶች ናቸው፡፡
አንዳንዶቹ የጎዳና ተዳዳሪዎች ለመሆናቸው አለባበሳቸው በግልጽ ያሳያል፡፡ ፖሊስ አትደብድቡ እያላቸው
እንኳን የሚሰሙ አይደለም፡፡ ሽጉጥ ማቀባበል የማይችሉት ሽጉጥ ተሰጥቷቸው ሲያስፈራሩ ካርታው ሲወርድባቸው ተመልክቻለሁ፡፡
በወቅቱ የሰማያዊ ፓርቲ የሰማያዊ ፓርቲ የብሄራዊ ምክር ቤት አባል የሆነችው ወጣት ወይንሸት ሞላ አብራኝ ነበረች፡፡ አንዋር መስጊድ በወንዶች መግቢያ ፊት ለፊት ካለው ህንጻ ላይ ሆነን ሁነቱን ስንከታተል ከአሁን ቀደም የሚያውቃትና ከህንጻ ላይ ሆኖ ሲቀርጽ የነበር ደህንነት ብቻዋን ነጥሎ እየደበደበ ወሰዳት፡፡
‹‹ለምን ተወስዳታለህ!›› ብዬ በጠየኩበት ወቅት ከእነዛ ከመንገድ ተለቃቅመው ለድብደባ የተሰማሩት ወጣቶች መካከል አንዱ ሽጉጥ አወጣብኝ፡፡ ለመሳሪያ ልምድ የሌለው በመሆኑ ካርታው እግሩ ስር ወደቀበት፡፡
ወይንሸትን ይዘውም ወደ ውጭ ከነፉ!
ወይንሸት ከተያዘች በኋላ የእነዛ አረመኔዎች ዱላ እኛም ላይ አረፈ፡፡ ፖሊሶች ደክሟቸውን ይሁን አዝነው
ሲተውን ከየት እንደመጡ የማይታወቁት ወጣቶች ግን እስኪበቃቸው ደብድበውናል፡፡
ሲተውን ከየት እንደመጡ የማይታወቁት ወጣቶች ግን እስኪበቃቸው ደብድበውናል፡፡
በድብደባው መሃል አንድ ፖሊስ ክርስቲያን መሆኔን ገልጾ ከአዛውንቶችና ከህጻናት ጋር ስለቀላቀለኝ እንደነዛ ወጣቶች ተዝለፍልፎ ከመውደቅ ተርፌያለሁ፡፡
እንግዲህ አንድ አገር እስከኖርን ድረስ፣ ጭቆናውም የሁላችን እስከሆነ ድረስ ሁላችንም ነጻ ካልወጣን ማንም ነጻ ሊወጣ አይችልምና እኔም እንደወንድሞቼ በአጠና ተደብድቤ ተለቅቄያለሁ፡፡ ግን አልተሰማኝም፡፡ ከእኔው ይልቅ የማይችሉት ዱላ ያረፈባቸው ህጻናትና አዛውንቶች ጣር ልብ ይሰብራል፡፡ ወይንሸት ላይ ያረፈው በትር ያማል!
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar