mandag 21. juli 2014

በአብርሃ ደስታ ቤተሰብ ላይ እየደረሰ ያለው ግፍ ከልክ አልፏል

ብዙዎች እንደሚያውቁት አብርሃ ደስታ በትግራይ የሚገኘው የአረና ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ነው። አረና ፓርቲ የህወሃት ተፎካካሪ ፓርቲ በመሆኑ፤ ወያኔዎች በአባላቱ ላይ ግፍ እና በደል ሲያደርሱ ቆይተዋል። አብርሃ ደስታም ትግራይ ሆኖ በዚያ የሚደረገውን ስር አት አልበኝነት በማጋለጡ፤ የትግራይን ህዝብ እንደካደ ተደርጎ ከድብደባ ጀምሮ የእስር እንግልት ደርሶበታል።  አሁንም ማዕከላዊ እስር ቤት ውስጥ መኖሩ ይነገራል እንጂ፤ ህዝብ እንዲያየውም ሆነ እንዲጠይቀው አልተፈቀደም። ፍርድ ቤት ያቀረቡትም ሰውነቱ በጣም ደክሞ እና ተጎሳቅሉ ከእኩለ ለሊት በኋላ ነው።
Abraha Desta
Abraha Desta

ይህ በአብርሃ ደስታ ላይ የሚደርሰው ስቃይ እና መከራ እንዳለ ሆኖ፤ እሱ ከታሰረ ጀምሮ ደግሞ በቤተሰቡ ላይ ከፍ ያለ ግፍ እየተፈጸመ መሆኑን ከትግራይ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። እንዲህ ይነበባል።
• የአብርሀ ታናሽ እህትና የጤና ባለሙያ (የጤና መኮንን/ HO) የሆነችው ተኽለ ደስታ የኢህአዴግ አባልም ሁና የአብርሀ እህት ስለሆነች ብቻ ከስራ ተባራለች፣ ቢሮ እንዳትገባም በዘበኞች ተከልክላለች፣ መልቀቂያም ከልክለዋታል፤ ቀጣዩ ውሳኔም ቁጭ ብላ እንድትጠባበቅም ተነግሯታል፡፡
• ሁለቱ አዲስ ምሩቃን ወንድሞቹ ኣረጋዊ ደስታና ገ/ገርግስ ደስታ በከፍተኛ ብልጫ ሰቅለው የተመረቁ ቢሆንም ዩኒቨርሲቲው እነሱን ላለመቅጠርና ከነሱ ያነሰ ነጥብ ያላቸውን መቅጠሩ ተሰምቷል፤ አዋሳ ዩኒቨርሲቲም ተወዳድረው እንዳለፉ ሲነገራቸው ቆይቶ ሌሎች ከነሱ በታች የነበሩ ሲጠሩ እነሱ እስካሁን አልተጠሩም፡፡
• እናቱ ሙሉ ኣለማየሁ “አንቺ የዐረናው እናት፣ እንቺ የከሀዲው እናት ይህ የህ.ወ.ሐ.ት ምድር ነው- ወዴትም ውጪልን” ድረስ የሚደርሱ ከፍተኛ በደሎች፣ ለቃላት የከበዱ ግፎች እየተፈፀሙባት ነው፤
• ሌሎች ዘመድ አዝማዶቹም በተዋረድ በከፍተኛ ጭንቅ ውስጥ ገብተዋል፣ ነገ በነሱ ላይም ምን እንደሚመጣ ስጋት ገብቷቸዋል፤

• ጀግናን መውለድ እዳው ብዙ ነው፤ በተለይም ደግሞ እዚህ በጭቆናዋ ምድር- በትግራይ! — ይላል የዘገባው መጨረሻ።

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar