አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ያሉበትን ቦታ ለማወቅ ጥረት እየተደረገ ቢሆንም፣ እስካሁን ድረስ ትክክለኛ ቦታውን ለማወቅ አልተቻለም። ይሁን
እንጅ በማእከላዊም ሆነ በቃሊ እስር ቤት አለመኖራቸውን ምንጮች ገልጸዋል።
የገዥው ፓርቲ ሰዎች በአቶ አንዳርጋቸው ላይ የፕሮፓጋንዳ ስራ ለመስራት የተለያዩ ሰዎችን እያነጋገሩ መሆኑን ለማወቅ ተችሎአል።
ኤርትራ ውስጥ ነበርን ያሉ እና በአቶ አንዳርጋቸው ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ የሚያካሂዱ ” አዳዲስ ሰልጣኞች ” እየተዘጋጁ ሲሆን፣ ከከመንግስት የመገናኛ ብዙሃን ምንጮች የተገኘው መረጃ
እንደሚያሳየው ደግሞ አጠቃላይ የቴሌቪዥን ፕሮግራሙ ከመንግስት ጋዜጠኞች እውቅና ውጭ በደህንነት ሰዎች ብቻ የሚዘጋጅ ይሆናል።
አቶ አንዳርጋቸው ያሉበትን ሁኔታ ለመከታተል ወደ ኢትዮጵያ ተጉዘው የነበሩት የአቶ አንዳርጋቸው ታላቅ እህት በ24 ሰአት ውስጥ አገር ጥለው እንዲወጡ መታዘዛቸው ይታወቃል።
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar