- የባህር ዳር፣\ ሰልፍ ተሟሙቆ ዋለ
- የአመራር አባላትን በሆቴል ቤታቸዉ እንገድላችኋለን እየተባሉ ነው
- ከባህር ዳር አካባቢ ያሉ እንቅስቃሴውን እየተቀላቀሉ ነው
- 10 ድርጅቶች ስብስብ የሆነው የትብብር አመራሮች መኢአድ እና አንድነት ተቀላቅለው እየቀሰቀሱ ነው
የባህር ዳር ሰልፍ ነገ የካቲኡት 16 ቀን ከጠዋቱ 3 ሰዓት ጀመሮ ይደረጋል። « ከባዶ ጭንቅላት ባዶ እግር ይሻላል» በሚል የተዘጋጀው ፍላየር ሰልፉ የሰልፉ መነሻ፡- ግሽ አባይ/ ቀበሌ 12 የሚገኘው አንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት ከጠዋቱ 3 ሰዓት ጀምሮ የሰልፉ የጉዞ መስመር፡- ከግሽ አባይ/ ቀበሌ 12 ተነስቶ በድብ አንበሳ ዞሮ ወደ ክልሉ መስተዳድር ጽ/ቤት ነው።
በባህር ዳር አጎራባች ይልማና ዴነሳ ወረዳ፣ የአንድነት ፓርቲ ሰብሳቢና ሁለት አመራሮች ለእሁዱ የተቃውሞ ሰልፍ በማስተባበራቸው ታሰሩ፤ ሌሎቹን አመራሮችም ለማሰር አሰሳ እያደረገ ነው፡፡
ነገ የካቲት 16 በባህር ዳር ከተማ ብአዴንንና አመራሮቹን በመቃወም በሚደረገው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ የባህር ዳር አጎራባች አካባቢ ነዋሪዎችም ለመሳተፍ ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት፣ የአንድነት ፓርቲ የይልማና ዴንሳ ወረዳ አመራሮች ህዝቡን በማስተባበርና አስፈላጊውን መረጃ ሲያደርሱ ሰንብተዋል፡፡
ህዝቡ በብአዴን ላይ እያሳየ የመጣው ቁጣ ያሳሰባቸው የአዴትና የአካባቢው ባለስልጣናትም ሁሉም የወረዳው የአንድነት አመራሮችን በሙሉ ለማሰር እርምጃ ጀምረዋል፤ በዚሁም መሰረት የወረዳው የአንድነት ሰብሳቢ አቶ ይሁኔ ዘለቀ ትላንት ማታ የታሰሩ ሲሆን፣ ዛሬ ደግሞ አቶ ጌታቸው መስፍን እና አቶ ብሩክ ትዕዛዙ ታስረዋል፡፡
እስሩን ከምንም ያልቆጠሩት የአንድነት አመራሮችም ህዝቡን ለሰልፍ ማስተባበራቸውን ቀጥለዋል፤ የባህር ዳር ዙሪያ ወረዳዎች ነዋሪዎችም ለሰልፉ መዘጋጀታቸውን እየገለፁ ነው፡፡
ወደ ባህር ዳር ከተማ ስንመለ፣ የአንድነት፣የመኢአድ እና የትብርር ለዲሞክራሲ አመራሮች ቀስቃሽ ወረቀት በመበተን ላይ ናቸው፤ ህዝቡን አጅቧቸው ቅስቀሳውን አድምቆታል፡፡
የአንድነት ፕሪዝዳንት ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው፣ የመኢአድ ፕሬዝዳንት አቶ አበባው መሃሪ እንዲሁም የትብብር ለዴሞክራሲ ሰብሳቢ አቶ ግርማ በቀለ፣ እንዲሁም የአንድነት ፓርቲ ብሄራዊ ምክር ቤት አባል የሆኑት አንጋፋው ፖለቲከኛ ዶ/ር ኃይሉ አርአያን ጨምሮ ወደ ስፍራው የተንቀሳቀሱ የፓርቲው የስራ አስፈፃሚ አባለት፣ በባህርዳር ጎዳናዎች ላይ የቅስቀሳ ወረቀቶችን በመበተን በዚያ ለበርካታ ቀናት ሲንቀሳቀሱ ከነበሩ አባላትን እና ደጋፊዎች ጎን የቅስቀሳ ተግባራት ላት ተሰማርተዉ ነበር።
የአንድነት ፕሪዝዳንት ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው፣ የመኢአድ ፕሬዝዳንት አቶ አበባው መሃሪ እንዲሁም የትብብር ለዴሞክራሲ ሰብሳቢ አቶ ግርማ በቀለ፣ እንዲሁም የአንድነት ፓርቲ ብሄራዊ ምክር ቤት አባል የሆኑት አንጋፋው ፖለቲከኛ ዶ/ር ኃይሉ አርአያን ጨምሮ ወደ ስፍራው የተንቀሳቀሱ የፓርቲው የስራ አስፈፃሚ አባለት፣ በባህርዳር ጎዳናዎች ላይ የቅስቀሳ ወረቀቶችን በመበተን በዚያ ለበርካታ ቀናት ሲንቀሳቀሱ ከነበሩ አባላትን እና ደጋፊዎች ጎን የቅስቀሳ ተግባራት ላት ተሰማርተዉ ነበር።
ብሕአዴን/ኢሓዴግ ግን የነገዉን ሰልፍ ለማጨናገፍ እያደረገ ያለውን ወከባና እንግልት ግን አላቆመም። በባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 11 በሚገኘው ሰን ራይዝ ሆቴል ያረፉት የአንድነት እና የመኢአድ የቅስቀሳ ቡድን አባላት እና አመራሮች በመንግስት የደህንነት አባላት ወከባ እየደረሰባቸው ሲሆን፣ መሳሪያ የታጠቁ ስድስት የመንግስት ደህንነቶች የታጠቁትን መሳሪያ በማውጣት እንገላችኋለን በማለት የቅስቀሳ ቡድኑን አባላት ለማዋከብና ልከማስፈራራት ትረት አደርገዋል።
የሆቴሉን ሰራተኞችንም፣ አልጋ የያዙ ግለሰቦችን መታወቂያ አምጡ በማለት ግርግር ለማስነሳት ሙከራ ያደረጉ ሲሆን ለፖሊስ በመደወልም «በአንድነት አባላት ተደብድበናል፤ ፎቶም ተነስተናል» በማለት ሀይል እንዲጨመርላቸው ጠይቀዋል።
ትብብር ለዲሞክራሲ አመራሮች ከመኢአድ እና አንድነት ጋር በባህር ዳር እየቀሰቀሱ ናቸው
========================================================================
የአሥር ድርጅቶች ስብስበ የሆነው ትብብር ለዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ አመራር አባላት ከመኢአድ እና አንድነት ጋር በመሆን በባህር ዳር ቅስቀሳ እያደረጉ እንደሆነ የደረሰን ዘገባ ያመልክታል።
የትብብሩ መስራች ድርጅቶች ዉስጥ የሐዲያ ብሔር አንድነት ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ፣የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ፣ የሶዶ ጎርደና ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት፣ የከምባታ ሕዝቦች ኮንግሬስ ፣ የኦሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ኅብረት፣ የመላው ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ፣የመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅት፣ የጌዴኦ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ፣የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ፓርቲ ይገኙበታል።
የባህር ዳሩን ሰልፍ መኢአድ እና አንድነት በጋራ ከመስራታቸውም ባሻገር ፣ ሌሎች ድርጅቶችን ማሳተፋቸው ፣ በራሱ ትልቅ ዉጤት መሆኑን የሚናገሩ ጥቂቶች አይደሉም። በተለይም ድርጅቶች በወረቀት ላይ ሳይሆን፣ በሥራ ትብብራቸውን ማሳየታቸዉ ሕዝብ በተቃዋሚዎች ላይ ያለዉን አመኔታ የበለጠ እንዲጨምር የሚያደርግ ነው።
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar