ከሚዲያ ዝግ በመሆን ለኢህአዴግ ካድሬዎችና ሹሞች በተዘጋጀው ውይይት ላይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ የሆኑት አቶ በረከት ስምኦን በኢትዮጵያ በልማታዊ አጀንዳ የሚወከለው ኢህአዴግ ብቻ ነው ያሉ ሲሆን፣ ሌሎች ፓርቲዎች ወይ ይህንን የሚጻረሩ ናቸው፣ ወይም ትርጉም የሌላቸው ናቸው ብለዋል። ኢህአዴግ ለረጅም ጊዜ በስልጣን ላይ ለማስቀጠል በመድብለ ፓርቲ ስም ይዞ መጓዝ እንደሚጠቅም አቶ በረከት ተናግረዋል።
የመድበለ ፓርቲ ስርአት ለአገራችን ተመራጭ ቢሆንም፣ በኢትዮጵያ ሁኔታ ያለው ግን የአውራ ፓርቲ ስርአት ነው ያሉት አቶ በረከት፣ ይህም ስርአት ሁለተኛው ተመራጭ በመሆኑ በአገራችን ለርጅም ጊዜ ይቀጥላል ብለዋል። የአውራ ፓርቲ ስርአት አንድ ፓርቲ በምርጫ እያሸነፈ ለረጅም ጊዜ የሚቀጥል መሆኑንም አቶ በረከት አክለዋል።
አቶ በረከት ይህን የተናገሩት ህዝቡ ሳይሰለች ኢህአዴግን እንዴት ለ50 አመት ተሸክሞ ሊሄድ እንደሚቻል ባስረዱበት ወቅት ነው።
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar