በአማራ ክልል የክልሉ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የብአዴን ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አለምነው መኮንን በአማራ ህዝብ ላይ የሰነዘሩትን ዘለፋ ተከትሎ የተነሳውን ተቃውሞ ለማብረድ የብአዴን የወጣቶች ሊግ ለአባለቱ የስልጠና እና የግምግማ ስራ በባህር ዳር ፤ ደሴ እና ጎንደር እያከናወነ ነው።
የካቲት 16 አንድነትና መኢአድ በጋራ የጠሩትን ሰልፍ ተከትሎ በባህር ዳር ከተማ ባሉ ዘጠኝ ክፍለ ከተሞች 12 የገጠር ቀበሌዎች ብአዴን አባላቱ እና አባል ያልሆኑ ወጣቶችን በግዳጅ በማስጠራት ባቀረበው የውይይት ሃሳብ እና መመሪያ በማህበራዊ ድረ ገፆች በሚተላለፉ ሃሰተኛ መረጃዎች ማንም ተወናብዶ ሰልፉን መቀላቀል እንደሌለበት አሳስቧል።
የጥፋት ሃይሎች የሚያስወሩት ሴራ ነው የሚለው ብአዴን፣ ሰልፉን ለማጨናገፍ ና ማህበረሰቡ በሰልፉ ላይ እንዳይገኝ ወጣቶች አስፈላጊውን ስራ መስራት እንዳለባቸው መክሯል።
የባህር ዳር ከተማ ወጣቶች ሊግ ጽ/ቤት ሃላፊ ወጣት ጌታቸው ብርሃኑ ባቀረበው ጽሁፍ የተሳሳቱ መረጃዎችን በማምጣት ህዝብ እና መንግስትን የማለያየት ስራ እየሰሩ በማለት ለወጣቶች ተናግሯል፡፡
የብአዴን ጽ/ቤ ሃላፊ የሆኑት አቶ እሱባለው መሰለ በበኩላቸው “የማህበራዊ ድህረ ገጾችን አትመልከቱ ችግር አለባቸው የሚያስተምሩት ጥላቻ እና አመጽን ነው” በማለት ምክራቸውን ለግሰዋል።
“በማህበራዊ ድረ ገፆች በሚተላለፉ ሃሰተኛ መረጃዎች አንታለልም” የሚል መሪ ቃል ይዞ እየተከናወነ ያለው ይህ ስልጠና ፣ ኢሳትንና ተቃዋሚ ፖለቲከኞችን ማእከል አድርጎ የሚካሄድ ነው።
አንዳንድ ተሰብሳቢዎች ” በድምጽ የሰማነውን ጉዳይ አይን ባወጣ ውሸት እንዴት ይክዱናል” ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
የክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የአቶ አለምነውን ንግግር ሳያስተባብሉ ” የብአዴን የወጣት ሊግ እና ታች ያሉ አመራሮች ወጣቱን ለማሳሳት መመኮራቸው ብዙ ተሰብሳቢዎችን አስደምሟል።”
አንዳንድ ወጣቶች ” መረጃውን ለምን ማህበራዊ ሚዲያ እና ኢሳት አቀረበው ብሎ ከመጥላት ለምን አቶ አለምነው ከ22 ሚልየን በላይ የሚሆነውን ህዝብ ተሳደበ ብሎ” ውይይት አይከፈትም ነበር ሲሉ ተደምጠዋል። ብአዴን ከህዝብ ይልቅ ግለሰብ ይበልጥብኛል በማለት ጉዳዩን እየሸፋፈነው ነው በማለት አንዳንድ አባሎቹ ለዘጋቢያችን ነግረዋታል። የጎንደር መሬት ለሱዳን ተቆርሶ መሰጠቱን በተመለከተም ኢህአዴግ ተቃዋሚዎችን በመሳደብ ስታራቴጅ ችግሩን ለማድበስበስ እየሞከረ መሆኑን ወታጦች መናገራቸውን ሪፖርተራችን ከባህርዳር ዘግባለች።
አቶ አለምነው የአማራው ህዝበ የትምክህት ለሃጩን ማራገፍ አለበት በማለት መናገራቸው ይታወቃል
አንድነትና መኢአድ እሁድ ለሚካሄደው ተቃውሞ በባህርዳር ቅስቀሳ በማድረግ ላይ ሲሆኑ፣ ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ ተቃውሞውን እንዲገልጽም ጠይቀዋል።
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar