
የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አለምነው መኮንን በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ቀርበው ለማስተባበል የሞከሩት ህዝቡን ይበልጥ ማስቆጣቱንም አቶ ሽፈራው ተናግረዋል። በሌላ በኩል መንግስት በእለቱ ተመሳሳይ ተቃውሞ ለማድረግ ማሰቡ ታውቋል። ተቃዋሚዎችን የሚያውግዙ መፈክሮችን በማስጻፍ የከተማው ነዋሪ በእለቱ እንዲወጣ እና ተቃውሞውን በተቃዋሚዎች ላይ እንዲያሰማ ስራ እየሰራ መሆኑን የኢሳት የባህርዳር ወኪል ገልጻለች።
የብአዴን ሹሞች የባጃጅ መኪኖች ሾፌሮችን በመሰብሰብ በተቃውሞው ቀን ድጋፋቸውን እንዳይገልጹ ለማግባባት ሞክረዋል።
አቶ አለምነው መኮንን የአማራውን ህዝብ የሚያንቋሽሽ ዘለፋ የብአዴን ካድሬዎች በተሰባሰቡበት መድረክ ላይ መናገራቸው ይታወሳል። ም/ል ፕሬዚዳንቱ ትናንት በሰጡት መግለጫ ንግግሬ ተቆራርጦ ቀርቦብኛል በማለት ለማስተባበል ሞክረዋል።
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar