ጥናቱ ኤክስፖርት በማያደርጉ ድርጅቶች ላይ እርምጃ ያለመውሰድ፣ በንግድ ፈቃድ ላይ የተጠናከረ ቁጥጥር ያለማድረግ እና በሕገወጥ የቡና ምርት ዝውውርና ግብይት ላይ የሚመለከታቸው አካላት ተቀናጅተው ያለመስራት በዘርፉ የሚታዩ ችግሮች መሆናቸውን ማመላከቱን ኮምሽኑ በድረገጹ ላይ ባሰፈረው ዜና ገልጿል፡፡
ኢትዮጵያ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ከምታገኝባቸው የግብርና ምርቶች መካከል በቀዳሚነት የሚጠቀሰው የቡና ኤክስፖርት ሒደት ለሙስናና ብልሹ አሠራር ያለውን ተጋላጭነት አስመልክቶ በኮሚሽኑ የተካሔደው ጥናት ይፋ የሆነው ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት ሰሞኑን በግዮን ሆቴል ጥናቱን ለማዳበር በተከናወነ የምክክር ስብሰባ ላይ ነው፡፡
የውይይት መድረኩ የተዘጋጀበት ዓላማ በዘርፉ ስለሚስተዋሉ የአሠራር ጉድለቶች ለሚመለከታቸው ክፍሎች ግልጽ ግንዛቤ ለማስያዝና ችግሮቹን በመቅረፍ ረገድ የተሻለ አሠራር በማመላከት የመፍትሔው አካል ሆነው የድርሻቸውን እንዲወጡ ለማስቻል እንዲሁም በክፍተቶቹ ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ በመያዝ ለመፍትሔው በጋራ ለመንቀሳቀስ ነው ተብሎአል፡፡
አገሪቱ ከቡና ኤክስፖርት የምታገኘው ገቢ በተለይ ባለፉት ሶስት ዓመታት ማሽቆልቆሉ የሚታወቅ ሲሆን ችግሩ ከዚህ ዓይነቱ ሙስናና ብልሹ አሰራር ጋር በቀጥታ ይያያዝ ፣አይያዝ የተገለጸ ነገር የለም፡፡
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar