በአማራ ሕዝብ ተቋቁሞ ሆኖም ግን የጥቂት ብአዴን ባለስልጣናት ከርስ መሙያ ሆኗል የሚባለው ዳሸን ቢራ ላይ ኢትዮጵያውያን የመጠጣት ማእቀብ (ቦይኮት) እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረበ። ጥሪው የቀረበው ሰሞኑን በተለያዩ የሶሻል ሚድያዎች የክልሉ ባለስልጣን የሆኑት አቶ አለምነህ መኮንን እመራዋለሁ የሚሉትን የአማራ ሕዝብ ለመጻፍ በሚከብዱ ጸያፍ ቃላት ሲሳደቡ የሚያስደምጥ ድምጽ ከተለቀቀ በኋላ በተቆጡ ኢትዮጵያውያን ነው።
የቦይኮት ጥሪው በፌስቡክ እና ትዊተርን በመሳሰሉ ታላላቅ የሶሻል ሚዲያዎች እየተሰራጨ ሲሆን በተለይም አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ ክልሎች በተለይም በአማራ ክልል የዳሽን ቢራን አንጠጣም የሚለው አድማ በሰፊው እንደተሰማ ነው። የቦይኮቱ እንስቃሴ መሪዎች በሶሻል ሚድያ እንደገለጹት ብአዴን የተባለው በአማራው ሕዝብ ስም የተቋቋመው የሕወሓት ተላላኪ ድርጅት እንደ አቶ አለምነህ መኮንን ያሉ ሰዎችን በስሩ ይዞ የሚቀጥል ከሆነ ይህ ዳሸን ቢራን ያለመጠጣት አድማ ይቀጥላል።
አቶ አለምነህ መኮንን ሕዝብን በመናቅ አንድን የተከበረ ሕዝብ በአጸያፊ ቃላት ሲናገሩ ማድመጥ በጣም የሚሰቀጥጥ መሆኑን የሚገልጹት እነዚሁ የቦይኮት ዳሸን ቢራ አስተባባሪዎች ሰውዬው ከስልጣናቸው ወርደው ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠይቀዋል።
በሶሻል ሚድያዎች የተበተነውና ብዙዎች በየገጻቸው ላይ እያባዙት የሚገኘው የቦይኮት ዳሸን ቢራ መልዕክት የሚከተለው ነው፦
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar