የክልሉ ምክር ቤት ሳያቀውቀው በስራ አስፈጻሚው እውቅና ከስልጣን የተነሱትን አቶ አለማየሁ አቶምሳን ማን ይተካቸው የሚለው አጀንዳ የአቶ አባ ዱላ ገመዳንና የአቶ አለማየሁ አቶምሳን ቡድኖች እያወዛገበ ነው። አቶ አለማየሁ አቶምሳ ወደ ስልጣን እንደመጡ የአቶ አባዱላን ቡድኖች በመምታት ከስልጣን ውጭ ያደረጉዋቸው ሲሆን፣ አባ ዱላ ይህን አጋጣሚ በመጠቀም ተመልሰው የእርሳቸውን ሰዎች ለማሾም እየሰሩ ነው።
እስካሁን ድረስ የክልሉ ምክር ቤት ስበሰባ አለመጠራቱም ታውቋል። አንዳንዶች እንደሚናገሩት ህወሃት ለዘብተኛ የሆነ መሪ እንዲመጣ ፍላጎት በሚያሳየው ፍላጎት የሁለቱም ሰዎች ደጋፊዎች ላይሾሙ ይችላሉ ፡፡ አቶ አለማየሁ የመሰረቱት አስተዳደር በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚገኙትን መለስተኛ ከተሞችን ለመስተዳድሩ ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆኑ የ10 በ90 ፕሮጀክት እንዲደናቀፍ ማድረጋቸውን በማንሳት እርሳቸውን የሚተካው ሰው ለዘብተኛ ሆኖ ከፌደራል መንግስቱ ጋር ተግባብቶ የሚሰራ እንዲሆን እንደሚፈለግ እኝሁ ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ሰዎች ይናገራሉ።
በአባ ዱላ ዙሪያ የተሰባሰቡ ሰዎች ከሙስና ጋር በተያያዘ ድርጅቱን አደጋ ውስጥ በመጣላቸው በፌደራሉ መንግስት በዙም አይደገፉም። ከሁለቱም ቡድኖች ወጣ ያለ አዲስ ሰው ለማገኘት ኦህዴድ ፈተና እንደሆነበትና ምናልባትም ሽኩቻው በዚህ ከቀጠለ የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት ስልጣኑን ተረክበው ሊቀጥሉ ይችላሉ የሚለውን ግምት እያጠናከረው መምጣቱን ይገልጻሉ።
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar