የአንድነት ብሔራዊ ምክር ቤትእና የመኢአድ ላዕላይ ምክር ቤት አባላት በጋር ባካሔዱት ስብሰባ ሁለቱ ፓርቲዎች የፊታችን ሐሙስ መጋቢት 11 ቀን 2006 ዓ.ም የቅድመ ውህደት ፊርማ እንዲያደርጉ መመሪያ ማስተላለፋቸውን ስብሰባውን የተከታተለው የፍኖተ ነፃነት ባልደረባ ዘገበ፡፡
የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት አባላት እና የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ላዕላይ ምክር ቤት አባላት ዛሬ መጋቢት 7 ቀን 2006 ዓ.ም በመኢአድ ጽ/ቤት ባደረጉት ስብሰባ የሁለቱ ፓርቲዎች በአስቸኳይ እንዲዋሀዱ መመሪያ ያስተላለፉት ሁለቱን ፓርቲዎች ፓርቲዎች ለማዋሀድ እያሸማገሉ የሚገኙ ምሁራንና ታዋቂ ግለሰቦች የተካተቱበት ኮሚቴ ያቀረባቸው የማስማሚያ ነጥቦች ከቀረቡ በኋላ እና የሁለቱም ፓርቲዎች ፕሬዘዳንቶችና የውህደት ኮሚቴ አባላት ውህደቱ የዘገየበትን ምክንያት ከዘረዘሩ እንዲሁም የሁለቱ ፓርቲዎች ምክር ቤት አባላት ሰፊ ውይይትና የመፍትሔ ሀሳብ ካቀረቡ በኋላ ነው፡፡ የቅድመ ውህደት ፊርማው በሚፈረምበት ዕለት ሁለቱም ፓርቲዎች የውህደቱን ሂደት የሚያመቻቹ ወኪሎቻቸውን እንደሚያሳውቁም የፍኖተ ነፃነት ባልደረባ ዘግቧል፡፡
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar