በማህበራዊ የመገናኛ ብዙሀን የተለቀቀ አንድ የድምጽ ማስረጃ እንደሚያሳየው ህጻናትን በጉዲፈቻ ስም ወደ ውጭ አገራት የሚልኩ በተለይም የአሜሪካ ድርጅቶች የኢትዮጵያ መንግስት በቅርቡ ያወጣውን ህግ በመቃወም ዘመቻ ሊጀምሩ መሆኑን ውሳኔ ላይ ደርሰዋል።
የኤጀንሲው ተወካዮች እንደሚገልጹት፣ መንግስት በቅርቡ የጣለው እገዳ በመገናኛ ብዙሀንና በህዝቡ ተጽእኖ የመጣ ነው። አንዳንድ የመንግስት ባለስልጣናት በቂ ገንዘብ እስከተከፈለ ድረስ የጉዲፈቻ ሂደቱ እንዲቀጥል እንደሚፈልጉ ይ አንድ አስተያየት ሰጪ የመቀሌ ባለስልጣናትን በማናገር ለመረዳት መቻሉዋን በውይይቱ ላይ ገልጻለች።
ህዝቡና ጋዜጠኞች ጉዲፈቻን በተመለከተ የያዙትን አቋም ለማስለወጥ ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የአየር ሰአት በመግዛት ውይይት እንደሚከፍቱ በመጨረሻ ባወጡት የአቋም መግለጫ ገልጸዋል።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ” ህጻናትን በጉዲፈቻ ስም” ወደ ውጭ የማውጣቱን አሰራር እንደሚቃወም በውይይቱ ላይ የተነሳ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ መንግስት በቅርቡ በወሰደው እርምጃ በርካታ ድረጅቶች በገንዘብ እጥረት መቸገራቸውም ተገልጿል።
ኢትዮጵያውያን ህጻናት ወደ ውጭ አገር እየተላኩ ከፍተኛ ስቃይ እየደረሰባቸው መሆኑ በተደጋጋሚ ተዘግቧል። ሃና ዊሊያምስ የተባለችው ኢትዮጵያዊት ታዳጊ በአሳዳጊዎቿ ከተገደለች በሁዋላ መንግስት ሂደቱ እንዲቋረጥ ማድረጉ ይታወቃል።
የጉዲፈቻ ኤጀንሲዎች በቂ ገንዘብ በመመደብ ህጻናትን የመውሰዱን ሂደት ለማስጀመር እንደሚጥሩ ቃል ገብተዋል።
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar