የከንቲባ ጽህፈት ቤቱ የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባዎች ኦፊሰር የሆኑት አቶ ማርቆስ ብዙነህ ለፓርቲው በጻፉት ደብዳቤ ” የአዲስ አበባ አስተዳደር የስብሰባና የሰላማዊ ሰልፍ አሰራር ስነስርአት በርካታ ትምህርት ቤቶች ዩኒቨርስቲና የመንግስት ተቋማት በሚገኙበት አካባቢ ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ የማይቻል በመሆኑ የተጠየቀውን የሰላማዊ ሰልፍ እውቅና ጥያቄ” አልተቀበንነውም ብለዋል።
የአንድነት ፓርቲ የአዲስ አበባ ከተማ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ያሬድ አማረ ለኢሳት እንደገለጹት ፓርቲው የመስተዳድሩን ደብዳቤ አልተቀበለውም። መስተዳደሩ በ12 ሰአታት ውስጥ መልስ መስጠት ቢኖርበትም ይህን አለማድረጉን፣ መስተዳድሩ አማራጭ መስመር አቅርቡ ባለማለቱም ፓርቲው ባወጣው መርሃ ግብር መሰረት እንደሚቀጥል ገልጸዋል
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar