በተለምዶ ሸዋ በር መብራት ሃይል ግቢ እየተባለ በሚጠራው የንግድ ማእከል ላይ ምክንያቱ በውል ባልታወቀ ሁኔታ የተነሳው የእሳት ቃጠሎ በብዙ መቶወች የሚቆጠሩ ነጋዴዎችን ንብረት አውድመዋል።
ነጋዴዎች እንደሚሉት እሳቱ ሆን ተብሎ በመስተዳድሩ ባለስልጣናት እንዲነሳ የተደረገ ነው። ነጋዴዎቹ አካባቢውን ለቀው እንዲሄዱ በተደጋጋሚኦ ሲጠየቁ እንደነበር እንዲሁም የእሳት አደጋ መኪኖች ዘግይተው እሳቱን ለማጥፋት መምጣታቸው ቃጠሎው በመስተዳድሩ ሰዎች ለመነሳቱ ምክንያት ነው በማለት ኢሳት ያነጋገራቸው ሰዎች ገልጸዋል። ድርጊቱን ለመቃወም አደባባይ የወጡ ሰዎች በፌደራል ፖሊሶች እንዲበተኑ መደረጉን ነዋሪዎች ተናግረዋል።
ከዚህ ቀድም በዚህ የንግድ ማእከል አካባቢ ከፍተኛ የሆነ የእሳት ቃጠሎ ተነስቶ በርካታ ንብረት ወድሟል።
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar