በአማራ ክልል በሰሜን ጎንደር ዞን በጭልጋ፣ በአርማጭሆና በመተማ ወረዳዎች እና በአካባቢው ያሉ የቅማንት ብሔረሰብ አባላት እያቀረቡ ያለውን የማንነትና ህገመንግስታዊ ጥያቄ ለማፈን ሰሞኑን በድምሩ 29 ያህል የቅማንት ተወላጆች መታሰራቸውንና መታፈናቸውን የቅማንት ብሔረሰብ የማንነት ጥያቄና ራስ አስተዳደር ይፈቀድልኝ አስተባባሪ ኮሚቴ አስታውቋል፡፡
ኮምቴው ከየካቲት 28 ቀን 2006 ዓ.ም ጅምሮ በአዲስ መልክ የቅማንት ብሔረሰብ ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ እስርና አፈና መጀመሩን ይፋ አድርጓል፡፡ በዚሁ መሰረት ከጭልጋ 15 ሰዎች መታፈናቸውን፣ከላይ አርማጮህ 14 ሰዎች መታሰራቸውን በመግለጽ እርምጃው የታሳሪዎችን ደህንነት የጎዳ፣ ቤተሰባቸውን ለችግር ያጋለጠ፣ የብሔረሰቡንም ማህበራዊ ማንነት ያናጋ በመሆኑ ድርጊቱ እንዲቆምና የታሰሩትና የታፈኑት እንዲፈቱ የካቲት 28 ቀን 2006 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ጠይቋል፡፡
የቅማንት ህዝብ በተበታተነ መልኩም ቢሆን በጭልጋ፣ በጎንደር ዙሪያ፣ በደንቢያ፣ በደጋው ቋራ፣ በላይ አርማጭሆና በመተማ የሚኖር ነው።
ገዢው ፓርቲ ከጥያቄው ጀርባ እጁ አለበት እየተባለ አስተያየት ሲሰጥ ቢቆይም፣ አሁን የተወሰደው እርምጃ ይህን የሚያጠናክር ሆኖ አልተገኘም። በቅርቡ በጎንደር ከተማ በ100 ሺዎች የሚቆጠሩ የብሄረሰቡ ተወላጆች የተቃውሞ ሰልፍ አካሂደው ነበር። የፌደሬሽን ምክር ቤትም ጉዳዩን እያጠናው መሆኑን ተናግሯል።
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar