torsdag 4. juni 2015

ሙዩኒክ፤ የተቃውሞ ሰልፍ


በኢንዱስትሪ የበለጸጉት የ ቡድን 7 አባል ሃገራት መሪዎች የዘንድሮውን ስብስባቸውን በሚያካሂዱባት በደቡብ ጀርመን ፌደራል ክፍለ ሀገር ፤ በባቬሪያ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አደባባይ ወጥተው ተቃውሞአቸውን መግለጻቸው ተነገረ። ጉባዔው ከሚካሄድበት ከጀርመንና ኦስትሪያ የአልፕስ ተራሮች ወሰን፤ 100 ኪሎሜትር  ገደማ ራቅ ብላ በምትገኘው የክፍለ ሀገሩ ርእሰ ከተማ የተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ ለተፈጥሮ አካባቢ ጥበቃ የሚቆረቆሩ፤ የአጽናፋዊውን  የኤኮኖሚ ትሥሥር መርኅ የሚቃወሙ የተሰባሰቡበት  ነው። በጀርመን  የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንም ፤ በትውልድ ሃገራቸው  የሰብአዊ መብት ረገጣን በመቃወም ፤ አብረው አደባባ የወጡ ሲሆን፣ የጠ/ሚንስትር አቶ ኃይለማርያም  ደሳለኝን በቡድን 7 አገሮች ተጋባዥ ከሆኑ አፍሪቃውያን መሪዎች አንዱ መሆናቸውን ነቅፈዋል።
በመራኂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል አስተናጋጂነት በጉባዔው የሚሳተፉት የ 7 ቱ ታላላቅ ባለኢንዱስትሪ ሃገራት፤ የብሪታንያ ፤ ካናዳ ፤ ፈረንሳይ፣  ኢጣልያ፤ ጃፓንና ዩናይትድ ስቴትስ  መሪዎች ናቸው።

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar