fredag 28. november 2014

ሰበር ዜና – ከ40 በላይ የአንድነት አባላትና አመራሮች በቃሊቲ እስር ቤት ታገቱ

የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አስራት አብርሃን ጨምሮ ከአርባ በላይ የሚሆኑ የፓርቲው አባላት ቃሊቲ እስር ቤት ውስጥ ታገቱ፡፡
አንድነት ፓርቲ የሚሊዮኖች ድምፅ ለህሊና እስረኞች በሚል መሪ ቃል ከህዳር 14 ጀምሮ እያካሄደያለው የማህበራዊ ሚዲያ ንቅናቄ አካል የሆነውን የህሊና እስረኞችን የመጎብኘት መርሀ-ግብር ለመሳተፍ ወደ ቃሊቲ እስር ቤት ያቀኑት የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አስራት አብርሃ እና የፓርቲው የአዲስ አበባ ሰብሳቢ አቶነገሰ ተፋረደኝን ጨምሮ 40 የአንድነት ፓርቲ አባላት ለግዜው ምክንያቱ ባልታወቀ ሰበብ በእስር ቤቱ ግዜያዊ ማቆያ እንዲገቡ መደረጋቸውን የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ከስፍራው ዘግበዋል፡፡
አንድነት የሚሊዮኖች ድምፅ ለህሊና እስረኞች በሚል መሪቃል በዚህ ሳምንት እያካሄደ ያለው ንቅናቄ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያንን ትኩረት ማግኘቱ ገዢውን ቡድን ማስቆጣቱ መዘገቡ ይታወሳል፡፡
a1a2a3

onsdag 26. november 2014

ሰማያዊ ፓርቲን ያቀፈው የ9 ፓርቲዎች ትብብር በመንግስት አፈና ትግሉን እንደማያቆም አስታወቀ

ትብብሩ ባወጣው መግለጫ ህዳር 21 ለሚደረገው ስብሰባ ለመስተዳድሩ የሰለማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል ደብዳቤ ቢላክለትም ለመቀበል ፈቃደኛ ካለመሆኑም በተጨማሪ፣ ስብሰባውን የሚያስተባብሩት የመኢዴፓ ሊቀመንበርና የትብብሩ ገንዘብ ያዥ የሆኑት አቶ ኑሪ ሙደሲር ላይ የድብደባ ወንጀል እንደተፈጸመባቸው ገልጿል።‹‹ነጻነታችን በእጃችን›› ነው የሚለው ትብብሩ፣  በኢህገመንግሥታዊና ኢዲሞክራሲያዊ እርምጃዎች ወደኋላ እቅዱን በህጋዊ መንገድ ለማስቀጠል እስከ ህይወት መስዋትነት ለመክፈል ያለውን ቁርጠኝነት ገልጿል።
ገዢው ፓርቲ ከአፈና ድርጊቱ እንዲገታና ለቀረበው  ህጋዊ የዕውቅና ጥያቄ በአስቸኳይ መልስ እንዲሰጥ፣  የትግሉ አላማ የመድብለ ፓርቲ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ በመሆኑ በአገር ውስጥም ሆነ ከአገር ውጪ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ለቀጣዩ ሠላማዊ ትግል የሚቀርበውን ጥሪ በንቃት እንዲከታተሉና ከፓርቲዎች ጎን እንዲቆሙ፣ በትብብሩን ያልተቀላቀሉ ፓርቲዎች እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቅርበዋል።
የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር እና የትብብሩ መሪ ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት የትኛውንም ዋጋ ከፍለን ነጻነታችንን ማስመለስ ከሁሉም በላይ ዋጋ የምንሰጠው ነው ብለዋል። እቅዳቸው መስዋትነት ሊያስከፍል እንደሚችል የገለጹት ኢ/ር ይልቃል፣ አስፈላጊውን መስዋትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል። ኢህአዴግ ለመግደልና ለማሰር ቆራጥ የሆነውን ያክል፣ እኛም ለመሞት ቆርጠናል ብለዋል
በሌላ በኩል ደግሞ በእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ የተከሰሱት አራቱ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች እና ስድስት ተከሳሾች  የክስ መቃወሚያ እንዲያቀርቡ ለታህሳስ 9 ቀን 2007 ዓ.ም ከፍተኛው ፍርድ ቤት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
አቶ ሀብታሙ አያሌው፣ የሺዋስ አሰፋ፣ አብርሃ ደስታ እና ዳንኤል ሺበሽ በሚገኙበት የክስ መዝገብ የተከሰሱት አስሩም ተከሳሾች  ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት የቀረቡ ሲሆን፣  የተከሳሽ ጠበቆች በጠየቁት መሰረት የተከሳሾቹን የክስ መቃወሚያ ለመቀበል ፍርድ ቤቱ ለታህሳስ 9/2007 ዓ.ም ቀጠሮ መስጠቱን ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል። ተከሳሾች በሽብርተኝነት ወንጀል መከሰሳቸው የሚታወቅ ነው። አለማቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ክሱ ፖለቲካዊ ነው በማለት ውድቅ ያደርጉታል።

torsdag 20. november 2014

የማንዴላን ጽዋ የተጎነጨው ሃብታሙ አያሌው (በዳዊት ሰለሞን

በ1972 የበጋ ወራት ኔልሰን ማንዴላ ከ27 ዓመት የእስር ፍርዱ 18ቱን ዓመት ወደሚያሳልፍበት ሮቢን ደሴት መጣ፡፡ጠባብ በሆነች ክፍሉ ወለሉ መኝታው፣ መጸዳጃው ደግሞ ቅርጫት ነበረች፡፡ ከባድ ስራ እንዲሰራም ይገደድ ነበር፡፡በዓመት ውስጥ ለ30 ደቂቃ እንዲጎበኘው የሚፈቀድለት ለአንድ ሰው ብቻ ነበር፡፡ በየስድስት ወራቱ አንድ ደብዳቤ እንዲቀበልና እንዲጽፍ ይፈቀድለት ነበር፡፡››

ሐብታሙ አያሌው ደቡብ አፍሪካ ያስተናገደችውን የዓለም ዋንጫ ለመመልከት ወደ አገሪቱ ባቀናበት አጋጣሚ ከልቡ የሚያደንቃቸው ኔልሰን ማንዴላ ለ18 ዓመታት የታሰሩባትን ታሪካዊዋን ክፍል በመጎብኘት የመታሰቢያ ፎቶ ግራፍ ተነስቶ ነበር፡፡

 የጸረ አፓርታይድ ትግል እንዲቀጣጠልና ጥቆሮች በገዛ አገራቸው ባይተዋር የሚሆኑበት የነጮች አገዛዝ እንዲያከትም ኢትዮጵያ ድረስ መጥቶ ወታደራዊ ስልጠና የወሰደው ማንዴላ በሮቢን አይስላንድ ከዓለም ተነጥሎ እንዲቀር ብዙ መከራ ተቀብሏል፡፡

 ወጣቱ ሐብታሙ በአእምሮው ይህንን እያሰላሰለ የነጻነት መንገድ ውጣ ውረድ እየታየው ገጽታውን ለካሜራ ባለሞያ የሰጠ ይመስለኛል፡፡ሐብታሙ በዚያን ወቅት የበሰለ እንጀራ ሌሎች ጋግረው እርሱ እንዲበላ ብቻ የሚጠበቅ ሰው ነበር፡፡

 ልክ ሙሴ በፈርኦን ቤት አድጎ የፈርኦን ልጅ መባልን በመጠየፍ የተራ ሰው ህይወት መምራት እንደጀመረ ሐብታሙም ሮቢንን የጎበኘው ‹‹ኢህአዴግ የጋገረውን እንጀራ ከመብላት ኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኝ የዘመናችን ሮቢን (ማዕከላዊ) መታሰርን እየመረጠ ነበር፡፡

 ሐብታሙ ከደቡብ አፍሪካ መልስ ‹‹አንድነታችን ከልዮነታችን በላይ ነው›› በሚል መሪ ቃል ‹‹አንድነት›› የሚል ቃልና ስም አምርሮ ከሚጠየፈው ኢህአዴግ ጋር ትግል ጀመረ፡፡

 ሮቢንን የጎበኘው ሐብታሙ የማንዴላ መንፈስ ተጠናውቶት የኢትዮጵያ ፖለቲካ መፍትሄ ፍቅር፣መቻቻልና ብሄራዊ እርቅ ማድረግ መሆኑን መስበክ ቀጠለ፡፡

 ይህ ለኢህአዴግ ተንበርካኪነት፣የኒኦ ሊበራሊዝም አቀንቃኝነትና የነፍጠኞች አካሄድ ነው፡፡ ሐብታሙም ጥርስ ውስጥ ገባ፡፡ ‹‹ኢህአዴግ ከታሪክ ይማር›› የሚለው ውትወታው ጆሮ አለማግኘቱ ይታወቅ ዘንድም በአንድ ማለዳ ብሶት የወለዳቸው ነፍጥ አንጋቾች ሐብታሙን መሬት ላይ አስተኝተው እየጎተቱት ማዕከላዊ (ሮቢን) አስገቡት፡፡

 ሐብታሙ በኢትዮጵያው ሮቢን ቅዝቃዜው አጥንት ሰብሮ በሚገባ ክፍል ውስጥ ታስሯል፣ መኝታው ወለሉ ናት፤ ለወራት ቤተሰቦቹን እንዳያገኝ ጠበቃውም እንዳይጎበኙት ተደርጓል፣ ድብደባ ተፈጽሞበታል፣ ህክምና እንዳያገኝ ተደርጓል፣ ያልፈጸመውን ነገር እንደፈጸመ በማድረግ ቃሉን እንዲሰጥ ተገድዷል፣ክፍሉ በጨለማ የተዋጠች ከመሆኗም በላይ ከሌሎች እስረኞች ጋር እንዳይገናኝ ተወስኖበታል፡፡
ሐብታሙ ሮቢንን ሲጎበኝ
ሐብታሙ ሮቢንን ሲጎበኝ

የማንዴላ መንገድ በኢትዮጵያ ተመሳሳዩን ጽዋ እንደሚያስጎነጨው ተገንዝቧል፡፡ እናም ጽዋዋን ለመጠጣት የማንዴላ መንፈስ እንዲረዳው ጸሎት አድርጓል፡፡
But Robben Island became the crucible which transformed him. Through his intelligence, charm and dignified defiance, Mandela eventually bent even the most brutal prison officials to his will, assumed leadership over his jailed comrades and became the master of his own prison. He emerged from it the mature leader who would fight and win the great political battles that would create a new democratic South Africa.
በሮቢን ደሴት የብረት ግግር የተቆለፈበት ማንዴላ በዚያ የሚገኙ አረመኔ የእስር ቤት ሃላፊዎችን ልብ በማሸነፍ በሳል መሪ ሆኖ እንደወጣ ሁሉ ሮቢንን የጎበኘውና በኢትዮጵያው ሮቢን (ማዕከላዊ) የሚገኘው ሐብታሙም በዚሁ መንፈስና ጥንካሬ እንደሚወጣ እምነታችን ጽኑ ነው፡፡

 

“ሃና ናት” ተብሎ የተሳሳተ ፎቶ በመሰራጨት ላይ ነው

በቅርቡ ታፍና ከተወሰደች በኋላ; አስገድዶ መደፈር የደረሰባት እና ህይወቷ ያለፈው ወጣት ሃና ጉዳይ ብዙዎችን እያነጋገረ ነው:: ከዚሁ ጋር ተያይዞ ታዲያ የሷ ያልሆነ ፎቶ በፌስቡክ እና በአንዳንድ ድረ ገጾች ላይ እየወጣ ነው:: ይህንን የተሳሳተ ፎቶ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የሚያሰራጩ ሰዎች አሉ:: ይህ ጉዳይ በአቸኳይ መስተካከል ያለበት ይመስለናል::
hanaአሁን ሆን ተብሎ ወይም በስህተት እየተሰራጨ ያለው ፎቶ ከአመታት በፊት አሜሪካ; በጉዲፈቻ መጥታ በአሳዳጊዎቿ ቸልተኝነት ህይወቷ ያለፈው ሃና ዊልያም ናት:: ትክክለኛውን ፎቶ በዚህ ድረ ገጽ ላይ ያገኙታል::

onsdag 19. november 2014

እንግሊዝ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን በተመለከተ ደብዳቤ መጻፏን ወያኔ አረጋገጠ



የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሮን አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን በተመለከተ ለወያኔዉ ጠቅላይ ሚኒስትር ደብዳቤ መጻፋቸውንና ወያኔም አቋሙን ግልጽ ማድረጓን የወያኔዉ ኮሙዩኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ሚኒስትሩ አቶ ሬድዋን ሁሴን ተናገረ። ሬድዋን በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ባለፈዉ ማክሰኞ በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ዴቪድ ካሜሩን ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደብዳቤ መጻፋቸውን የተለያዩ የውጭ ሚዲያዎች መዘገባቸውን ሰምቻለሁ ካለ በኋለ “ለምን ጻፉ ማለት አይቻልም፤ ጥያቄዉ መሆን ያለበት ምን መለሳችሁ ነው፤” በማለት የተለመደ የማጭበርበሪያ ቃላት ደርድሯል።

የተለያዩ የእንግሊዝ ሚዲያዎች ኢትዮጵያ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ላይ ቀደም ሲል የተፈረደውን የሞት ቅጣት እንዳትተገብር እንዲሁም ኢትዮጵያ ለሚገኘው የእንግሊዝ ኤምባሲ አቶ አንዳርጋቸውን የመጐብኘት ቋሚ ፈቃድ እንዲሰጥ በደብዳቤያቸው መጠየቃቸውንም ሬድዋን ሁሴን ተናግሯል።

ለዴቪድ ካሜሮን ደብዳቤ መልስ መሰጠቱን ያረጋገጠዉ ሬድዋን፣ “በተጨባጭ የተፈረደበትን ግለሰብ ነው የያዝነው፤ እንዲህ ብታደርጉት ባታደርጉት ብሎ ማንሳት ይቻላል። ምክንያቱም እነሱም የሚመለከታቸው በመሆኑ። በዚህ ምክንያት ግን የእኛ መልስ በራሳችን ሕግ መሠረት ዓለም አቀፍ ሕጉም በሚለው መሠረት የምናደርገውን እናደርጋለን፤” ብሏል። ኢትዮጵያ የምትተገብረው የራሷን ሕግ መሆኑን የገለጹት አቶ ሬድዋን፣ “ከነጭም ከጥቁርም የሚመጣን ደብዳቤ ተንተርሰን ምንም አንተገብርም፤” ብሏል። ከዚህ በተጨማሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሮን ደብዳቤ ጽፈው፣ በኢትዮጵያ በኩልም መልስ ተስጥቷል ያለዉ ሬድዋን ሁሴን በደብዳቤው የቀረቡ ጥያቄዎች ቅሬታ እንዳላስነሱ ሁሉ መልሱም ቅሬታ አያስነሳም የሚል ተስፋ በኢትዮጵያ በኩል መኖሩን ተናግረዋል።

“እነሱ ዜጋዬ ነው ብለዋል፤ የእነሱ ዜጋ እንደ ቼ ጉቬራ ነፃ አውጣ ተብሎ ኢትዮጵያ ውስጥ አልተላከም። የእነሱ ዜጋ ከነበረ የእንግሊዝን ዴሞክራሲ ይበልጥ ለመጨመር መታገል ይችል ነበር። ነገር ግን በኢትዮጵያ በቅጥር ነብሰ ገዳይነት ካልተሰማራ በስተቀር ሌላ ሚና አልነበረውም፤” ብለዋል።

ሽመልስ ከማልና ፈትያ የሱፍ በፕሬስ ድርጅት እየተወዛገቡ ነው

‹‹ችግሮች በአስቸኳይ ካልተፈቱ ለበላይ አካል እናሳውቃለን›› ፈትያ የሱፍ
‹‹ችግሮቹ ውጫዊ ናቸው›› አቶ ሽመልስ ከማል
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር







የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሽመልስ ከማል እና በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የባህልና ቱሪዝም ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ፈትያ የሱፍ በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዙሪያ እየተወዛገቡ እንደሚገኙ ምንጮች ገልጸዋል፡፡

አቶ ሽመልስ ከማል የፕሬስ ድርጅት የቦርድ ሰብሳቢ ሲሆኑ፣ ላለፉት አራት አመታት ድርጅቱ በተለያዩ ችግሮች ተዘፍቆ እያለ በቦርድ ሰብሳቢነታቸው ችግሮቹን መፍታት የነበረባቸው ቢሆንም ተደጋጋሚ ማሳሰቢያዎችን ችላ በማለት ድርጅቱ ከእነ ችግሮቹ እንዲዘልቅ አድርገዋል በማለት የባህልና ቱሪዝም ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ፈትያ የሱፍ ተናግረዋል፡፡

 ሰሞኑን የ2007 የበጀት እቅድን ለመገምገም በተገናኙበት ወቅት የፕሬስ ድርጅት ቦርድ እና አስተዳደር በበርካታ ችግሮች ዙሪያ ወቀሳ እንደደረሰበትና ችግሮቹ እንዲፈቱም ማስጠንቀቂያ እንደተሰጠ በራሱ ድርጅት እየታተመ የሚወጣው ኢትዮጵያን ሄራልድ ጋዜጣ በቅዳሜ እትሙ አስነብቧል፡፡

በድርጅቱ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የአስተዳደር ብልሹነት መኖሩን የተናገሩት ፈትያ የሱፍ፣ ‹‹በራሱ ድርጅት በችግር የተተበተበ ጋዜጠኛ እንደምን የሌሎችን ድርጅቶችና ግለሰቦች የአሰራር ችግሮች ሊያጋልጥ ይችላል?›› ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ አክለውም በተደጋጋሚ ችግሮቹ ለድርጅቱ አስተዳደር በሰራተኞች ሲቀርቡለት የዝሆን ጆሮ ይስጠኝ እያለ ማለፉን የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዋ አውስተዋል፡፡


ፈትያ የሱፍ እንደሚሉት የፕሬስ ድርጅት ቦርድ እና አስተዳደር ችግሮቹን በአስቸኳይ የማይፈታ ከሆነ ወደሚመለከተው ከፍተኛ አካል ለማስተላለፍ ከውሳኔ ላይ መደረሱን አስረድተዋል፡፡

የድርጅቱ የቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ሽመልስ ከማል በበኩላቸው የድርጅቱ ችግሮች ውጫዊ መሆናቸውን ይናገራሉ፡፡ ድርጅቱ የበጀት ችግሮች እንዳለበት ያወሱት አቶ ሽመልስ፣ በተጨማሪ ግን በድርጅቱ ላይ መጥፎ እይታ ያላቸው እና መጠቀሚያ ለማድረግ የሚፈልጉ አካላት በሰራተኞች ስም አላማቸውን ለማስፈጸም የሚሯሯጡ ወገኖች አሉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

‹‹የግል እና የመንግስት ሚዲያ ይለያያሉ፤ በአመለካከት፣ በአሰራርና በጥራት ልዩነት አላቸው›› በማለትም ሰራተኞቹ ፕሬስ ድርጅት እንደ ግል ሚዲያ ሊሰራ እንደማይችል ማስጠንቀቂያ አዘል መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ሰብስቤ ከበደ እና አቶ ሽመልስ ከማል ከፍተኛ የሆነ የጥቅም ትስስሮሽ እንዳላቸው የሚገልጹት የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች፣ በዚህ ትስስራቸው የተነሳም የአቶ ሽመልስ ከማል ባለቤት ያለምንም ውድድር በድርጅቱ በጋዜጠኝነት ተቀጥራ ምንም ስራ ሳትሰራ ደመወዝ ትወስድ እንደነበር፣ በኋላ ግን ‹ስራውን አልቻልኩትም› በሚል ከድርጅቱ እንደወረጣች ይናገራሉ፡፡

አቶ ሰብስቤ ከበደ በሰራተኞች ዘንድ ተቀባይነት የሌላቸው እና በተለያዩ ስብሰባዎች በይፋ ‹አልቻልክም ድርጅቱን ልቀቅ› ተብለው በሰራተኞች እንደተነገራቸው ምንጮች ይናገራሉ፡፡ ሆኖም ግን ከአቶ ሽመልስ ከማል ጋር ባለቸው የጥቅም ትስስር በስልጣናቸው እስካሁን እንደሚገኙ፣ ይህም ድርጅቱን እና ሰራተኞችን እየጎዳ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡

mandag 17. november 2014

የአሜሪካ ድምጽ ፒተር ሃይንላይንን ከሃላፊነቱ አነሳ


Peter goes(አዲስ ቮይስ) የአሜሪካን ድምጽ ዳይሬክተር ዴቪድ አንሶር የአፍሪካ ቀንድ የበላይ ሃላፊ የነበረው ፒተር ሃይንላይን ከሃላፊነቱ መነሳቱን አሳወቁ። ዳይሬክተሩ ባለፈው አርብ የክፍሉን ሰራተኞች በድንገት ሰብስብስበው እንዳስታወቁት ሃይንላይን ከሃላፊነቱ ተነስቶ በምትኩ የርሳቸው ከፍተኛ አማካሪ የሆኑት ዊሊያም ማርሽ በግዚያዊነት መሾማቸውን ገልጸዋል።
በቅርቡ በአሱዛ ፓስፊክ ዩኒቨርሲቲ ለአቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ተሰጥቶ የነበረ ክብር መሰረዙ ጋር በተያየዘ ከሄኖክ ሰማእግዜር ጋር በመተባበር የተዛባ ዘጋባ አቅርቧል የሚል ክስ ቀርቦበት የነበረው ፒተር ሃይንላይን የአስተዳደር በደል አቤቱታም በተጨማሪ በስሩ ያስተዳድራቸው ከነበሩ ሰራተኞች ቀርቦበት እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።
የአሜሪካ ድምጽ የበላይ ሃላፊዎች በሃይንላይን ላይ የቀረቡትን አቤቱታዎች መመርመራቸውንና ከፍተኛ የአሰራር ጉድለቶች እንደነበር ማረጋገጣቸው ታውቋል። በጋዜጠኛና አክቲቪስት አበበ ገላው አቤቱታ የቀረበበትን ዘገባ በተመለከተ የአሜሪካን ድምጽ የበላይ አስተዳደር (Board of Broadcasting Governors) ጉዳዩን በጥልቀት መርምሮ ዘገባው ያለተሟላና ከአሜሪካ ድምጽ ደረጃ በታች የወረደ ነበር ሲል መግለጹ ይታወሳል።
ይሁንና የአሜሪካን ድምጽ የአማርኛ ክፍል ግዜውን በጠበቀ መልኩ አግባብ ያለው እርምትና ማስተካከየ ሳያደርግ መቅረቱና ስህትቱን ከማረም ይልቅ መሸፋፈን በመምረጡ ተጨማሪ አቤቱታ ለቪኦኤ የበላይ ሃላፊዎች ቀርቦ እንደነበር አበበ ገላው ገልጿል።
አበበ በተለይ ፒተር ሃይንላይን እንደ ባለስልጣን ሃላፊነት በተሞላበት መልኩ ማስተካከያ ከማድረግ ይልቅ አደናጋሪና የተዛቡ ዘገባዎችን በተደጋጋሚ እንዲቀርቡ ማድረጉ ለእርምጃው መወሰድ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው የውስጥ አዋቂዎችን በመጥቀስ አስረድቷል።
አዲሱ የአፍሪካ ቀንድ ሃላፊ ሆነው የተሾሙት ማርሽ ከዚህ በፊት በተመሳሳይ ሃላፊነት ለሶስት አመታት ማገልገላቸው የታወቀ ሲሆን በሰራተኞች የተከበሩና ለሙያቸው ትልቅ ከበሬታ ያላቸው መሆኑን ለማወቅ ተችላሏል። ፒተር ሃይንላይን ከሃልፊነት ቦታው ወርዶ ያልምንም አስተዳደራዊ ሃላፊንት ወደ አፍሪካ ክፍል መዛወሩ ለመረዳት ተችሏል።

torsdag 13. november 2014

ታሪክ እንደስኳርና ጨው በኪሎ




የአጼ ቴዎድሮስ፤ የአጼ ሚኒሊክ፤ የአጼ ዮሐንስ ደብዳቤዎችን ጨምሮ ሁለት ሺህ ኪሎ የሚመዝኑ ታሪካዊ ፋይዳቸው ከፍተኛ የሆኑ መጽሃፍትና ጋዜጦች ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ መጽሃፍት በኪሎ 20 ብር ተቸበቸቡ።

በሃገር ውስጥ እንዲኖሩ የማድረግ ፍላጎት ያላቸው–በተቻለ ለኢትጵያዊያን ብቻ መጽሃፍ የሚሸጡ ነጋዴዎች በሽያጩ እንዳይሳተፉ ሲታገዱ፤ ከውጭ ሃገር ገዢዎች ጋር ግንኙነት ያላቸውና ጥቅሙን የሚያውቁ አትራፊዎች ግን በሚስጥር ተጋብዘው በርካሹ ገዙት።
የዮብ ሉዶልፍ፤ ጀምስ ብሩስ፤ ሮሲኒ፤ ሂስትሪ ኦፍ አቢሲኒያ፤ የፋሽስት ወረራ ጊዜ በወራሪው ሃይል ይታተሙ የነበሩ ጋዜጦች እንዳሉ፤ የቄሳር መንግሥትና የሮማ ብርሃን የተባሉት ጋዜጦች እና ሌሎችም የማይገኙና አሁን ቢገኙ ደግሞ ዋጋቸው በእጅጉ የናረ የሆኑ ውድ የሃገር ሃብት ጊዜ ያለፈባቸው፤ ጥቅም የሌላቸው፤ ያረጁ፤ ቦታ ያጣበቡ፤ በሚሉና በሌሎችም ሰበብ እንደ ስኳር መጥቅለያ ተራ ወረቀት በኪሎ ተቸበቸቡ።

ሚስጥራዊ ግን ንግዳዊ መሳይ የኢትዮጵያ ታሪክ ለተተኪው ትውልድ ሊተላለፍ የሚቻልበትን መንገድና ማስረጃ ሁሉ ድምጥማጡን ማጥፋት ቀደም ብሎ የታቀደ መሆኑ ሲሰማ ነበር። አሁንማ ሚስጥርነቱም ሳያስፈልግ፤ ምን ይሉናልም ገደል ገብቶ፤ “ላይጠቅሙ ቦታ ይዘው አዳዲስ መጻሕፍት ቦታ አጡ” (አዳዲስ የሚባሉትም ከ1983 ወዲህ በገዢዎቻችን አባላትና ስለጀግንነታቸው፤ ኢትዮጵያ ትላንት የተፈጠረች ሃገር የሚሉ አይነቶቹ ናቸው) በሚል አጉል ሰበብ እየተመረጡና የኢትዮጵያን ምንነት፤ ማንነት፤ ቀደምት ኢትዮጵያዊያን የፈጸሙት መልካም ምግባርና የኢትዮጵያዊነታቸው መገለጫ የሰፈረበት በውጭ ሰዎች የተጻፉት ዘመን ያስቆጠሩት የታሪክ መዛግብት በኪሎ ከስኳርና ጨው ባነሰ ዋጋ መሸጡ ያሳዝናል።

እነዚህ ጥንታዊ፣ ጥናታዊ፣ አብዛኛው በአይን ምስክር ላይ ተመስርተውና ምርምር ተካሂዶባቸው ጉልበት ጊዜ መዋዕለ ንዋይ ፈሶባቸው በምሁራን የተጻፉ፤ ሃገራችንን ጎብኝተው፤ ከማሕበረሰቡ ጋር ተግባብተውና ባሕልና ልምዱን ቀስመው፤ ልምዱን ተላምደው ለታሪክና ለትውልድም እንዲተላለፍ በማለት በዚያ መጓጓዣ እንደአሁኑ አልጋ ባልጋ ባልሆነበት ዘመን፤ ሽያጭ ያዋጣል አያዋጣም የሚለው ጥያቄ ባልታወቀበትና፤ ተጉዘው ያዩትንና የተረዱትን ላላዩትና እድሉ ላልገጠማቸው ሁሉ እንዲሆን ብለው ጽፈው ለሕትመት ያበቋቸው የሃገራችን ታሪካዊ ሰነዶች በኛው በዜጎቻችንን እንዲጠፉና እንዳይነበቡ ከቤተመዘክራችን ወጥተው አንዱን በ16ኛው ክፍል ዘመን የተጻፈውን መጽሐፍ ከአንድ ኪሎ ሽንኩርት ባነሰ ዋጋ በኛ ዘመን መሸጡ ያሳፍራል፤ ያናድዳል፤ ያሰቆጫል።

ሻጩ ብሔራዊ ቤተመዘክር የሀገራችን የታሪክና ሌሎችም መጻሕፍት፤ በኢትዮጵያዊያንም ሆነ በውጭ ደራሲያንና የታሪክ ተመራማሪዎች ያሳተሟቸው በነጻ የተገኙ፤ ዋጋ ተከፍሎባቸው የተሰባሰቡት፤ ተቀምጠው ለሕዝብ ንባብ የሚበቁበት፤ ለምርምር የሚውሉበት፤ ለማስረጃነት የሚጠቀሱበት ባለአደራ ተቋም እንዲሆን ነበር የተቋቋመው። አሁን ባህሪውን ለውጦ አደራ በላነቱን በግላጭ “ባለቤት ያላት በግ ላቷን ውጭ ታሳድራለች” እንዲሉ፤ በዚያ ቤተመዘክርም የተሰየሙት ሃላፊዎች ማን አለብን ባዮችና ማን ነክቷችሀ ተብየዎች በመሆናቸው የጥንቷን ኢትዮጵያ ታሪክ የሚያስተምረንን መጸሐፍ ሁሉ “ድምጥማጡን አጥፉ፤የዚች ሃገር ታሪክ “ሀ” ተብሎ የሚመዘገበው እኛ መግዛት ከጀመርንበት አንስቶ፤ የሚጻፈው ታሪክ ሁሉ እኛን መሰረት ያደረገ መሆን ስላለበት ከዚያ ውጭ ያለው ሁሉ ወደ ቤተመዘክር ጨርሶ እንዳይደርስ” በሚል መመርያ የተሰጠበት በመመስል መልኩ የታሪክ ቅርስ ሽያጩ ተካሄደ።

ሽያጩን የፈቀዱት የወመዘክር ሃላፊ መጪው ምርጫ ሰዉን ሁሉ ጠራርጎ በቀን አበል ሥልጠና ሲያስገባ እሳቸውም ሥልጠና ላይ በመሆናቸው፤ ቀደም ተብሎ ሲወራ የነበረው ሽያጭ በመዘግየቱ ኢትዮጵያዊነት የሚሰማቸውና መጽሃፍቱ በምንም መልኩ ከሃገር መውጣት የለበትም፤ መሸጡም አግባብ አይደለም የሚሉ ነጋዴዎች ሽያጩን አስቀድመው ሰምተው ለመሳተፍ ቢጠይቁም እንዳይሳተፉ ተደረጉ።
የሃላፊው ሥልጠና ላይ መግባት ሽያጩን ሲያዘገየውም ሽያጩ ተሰርዟል ተብሎ ቢታሰብም፤ ባለሥልጣኑ ወዲያው ሰልጥነው የወጡ የዕለቱ ዕለት ቅድሚያ ሰጥተው “ይሸጥ” ብለው በፊርማቸው አዘዙ። ከጠዋቱ በሁለት ሰአት ከ45 ደቂቃ ላይ ከመፈረማቸው በቅጽበት የተዘጋጁት መጫኛዎች ተከታትለው ወደ ወመዘክር ግቢ ገብተው፤ ከፍለው፤ ቅርሳችንን ጭነው ጭልጥ አሉ። ነገሩ አስቀድሞ በእቅድ ተደራጅቶ ያለቀ ሆኖ ነው እንጂ እንዴት ተብሎ እንዲህ ተፋጠነ ይባላል?!
በቃ ንብረትነቱ የገዢዎቹ ሆነና ወዲያው ወሬውን የሰሙ ከገዙት ላይ ለውጭ ሰዎች ከማለፉ በፊት ብለው ተሯሩጠው እጥፍ ከፍለው ለመግዛት ቢሞክሩ ዋጋው የትየለሌ ሆነና በመግዛት ፈንታ ቅስማቸው ተሰብሮ በሃዘን ወደየመጡበት ተመለሱ።
በጣም የሚያሳዝነው በረከት የጻፈው “የሁለት… ወግ” በሃሰትና በትርኪ ምርኪ የተሞላው የክብር ቦታ ተሰጥቶት መጪው ትውልድ የውሸት ታሪክ እንዲማርበት ሲደረግ በታሪክ ላይ ተመስርተው ለመዘገቡትና የኢትዮጵያን ምንነት ማንነት፤እምቢኝ አንገዛም ለጠላት አንንበረከክም፤ ሃገራችንን አሳልፈን ከመስጠት ለሃገራችን ሉአላዊነት፤ ለዳር ድንበሯ መከበር እራሳችንን እናሳልፋለን ስላሉት ቆራጦች የተጻፈው የማንነት ማረጋገጫ የማይረባ ያረጀ ተብሎ በኪሎ መሸጡ የደረስንበትን የታሪክ ዝቅጠት ያሳያል።
መጻሕፍቶቹ ቦታ አጣበቡ ከተባለ ለምን ቤተመጻሕፍታቸው ባዶውን ለሆነውና የመጽሐፍ ያለህ ብለው ለሚጮሁት የየክልሉ መንግሥታዊና የግል ኮሌጆችና ዩኒቨርሲቲዎች በችሮታ አይሆንም ከተባለም ለነጋዴ በተሸጠበት ዋጋ አልተሰጠም?
እነዚህ የሃገርን ታሪክ፤ የሕዝብን ማንነት የሚዘክሩ የታሪክ ቅርሶች እንዲሸጡና ከኢትዮጵያዊያን እንዲርቁ መደረጉ ተተኪው ትውልድ ስለሃገሩ እንዳያውቅና ማንነቱን ጨርሶ እንዲዘነጋ ሆን ተብሎ የሚደረግ ደባ ነው።
“ጥቅም የላቸውም፤ አርጅተዋል፤ቦታ አጣበቡ፤ ከደራሲያን ማሕበርና ከዩኒቨርሲቲ ምሑራን አይተው እንዲሸጡ የወሰኑት ነው፤ ኮሚቴ ተቋቁሞ ረጂም ጥናትና ምርምር አድረጎበት የወሰነው ነው” ተብሎ ለሽያጭ፤ ያውም በኪሎቱ 20 ብር ከተቸበቸቡት የታሪክ ምስክሮቻችን በጥቂቱ እነሆ:

1 A NEW HISTORY OF ETHIOPIA JOB LUDOLF 1682
2 HISTORE DE ETHIOPIA GREEN LOPO 1728
3 JOURNAL OF A VISIT TO SOME PARTS OF ETHIOPIA GEORGE WADDING ESA 1822
4 LIFE IN ABYSSINIA MANSFIELD PARKYNS 1856
5 HISTRE EN ABYSSINIA D’ABADDI 1867
6 NARRATIVE OF THE BIRITISH MISSINO TO THEODROS KING OF ABYSINIA HARMUZD RASSAM 1869
7 CARDINAL MASSAIA 35 ANNI DI MISSIONE IN ALTA ETHIOPIA 1885
8 LE NEGUS MENELIK J.G VANDER HEXNI 1899
9 FIRST FOOT STEPS IN EAST AFRICA –EXPLORATION OF HARRAR CAPT, SIR RICHARD T BURTON 1925
10 VAT CHRONIQUE GEBRESELASI 1930
ኢትዮጵያዊ የሆነ ሁሉ በያለበት ይህን ድርጊት ሊያወግዘውና የብሔራዊ ቤተመዘክር ወመጻሕፍትን ሃላፊ የመጽሃፉን ሽያጭ የፈቀዱትን ባለፊርማ ለሕግ ማቅረብ ቀዳሚ ተግባሩ ሊያደርገው ይገባል።
ከዘመነ ትዝብቱ

onsdag 12. november 2014

ሰበር ዜና – አዲስ አበባ በግድግዳ ላይ መፈክሮች ተጥለቅልቃ አደረች:ደፍሮ መፈክሮቹን የሚያነሳ አልተገኘም:: ከምኒሊክ ሳልሳዊ


ኢወጋን – በአዲስ አበባ ከተማ በተመረጡ ቦታዎች ላይ የቅስቀሳ መልእከቶችን ለህዝብ እይታ አብቅቷል።
‪#‎VIDEO https://www.youtube.com/watch?v=F2jq9pNgmzg
የአትዮጵያ ወጣቶች የጋራ ንቅናቄ (ኢወጋን)አባላት በአዲስ አበባ ዋና ዋና የህዝብ መገናኛ ቦታዎች እና የአውቶብስ መጠበቂያ የገበያ ቦታዎች ላይ የወያኔን ስርአት የሚያወግዙ እና ስርአቱን ለማውረድ ህዝቡ በጋራ እንዲነሳ የሚያደርጉ ጥሪዎችን ያነገኡ መፈክሮችን በመለጠፍ እንዲሁም ለፖሊስ እና ጦር ሰራዊቱ የሚገባውን የአንድነት እና የህዝብህን አድን ጥሪ በማስተላለፍ የተሳካ ስራ መስራታቸውን ከአዲስ አበባ ኢወጋን የደረሰን መረጃ ያመለክታል::
በአዲስ አበባ ከተማ በተመረጡ ቦታዎች ላይ የቅስቀሳ መልእከቶችን ለህዝብ እይታ አብቅቷል።
መላው ኢትዮጵያዊ ወጣት ከኢወጋን ጎን እንዲሰለፍ ጥሪውን በአክብሮት ያስተላልፋል።
በቭድዮ የተደገፈ ዝርዝር ዜናውን በኢትዮጱያ ወጣቶች ድምጽ በኩል ይፋ እናደርጋለን።
ያለ መስዋዕትነት ድል የለም !!!
የኢትዮጵያ ወጣቶች የጋራ ንቅናቄ (ኢወጋን)አዲስ አበባ ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የሰነዘረዉ ክስ

የኢትዮጵያ አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) መንግሥት በፓርቲዉ አመራርና አባላት ላይ የሚሰነዝረዉን ማዋከብ ከምንጊዜዉም በላይ አጠናክሮ ቀጥሎአል ሲል ከሰሰ።

  የፓርቲዉ የብሄራዊ ምክር ቤት አባል እና የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ዘካርያስ የማነ ብርሃን እንደገለፁት በሀገሪቱ ሊደረግ የታቀደዉን ብሔራዊ ምርጫ አስመልክቶ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ላይ የሚሰነዘረዉ ወከባ መንግስት የፖለቲካ እንቅስቃሴዉን ለመቆጣጠር ሆነ ብሎ እያደረገ ያለዉ ተግባር ነዉ።
እንደ ሁልጊዜዉ ሁሉ አሁንም የፓርቲዉ አባላት ላይ እስራት፤ እንግልትና ወከባ ይፈፀምባቸዋል፤ ያሉት የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የብሄራዊ ምክር ቤት አባልና የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ዘካርያስ የማነ ብርሃን ለሀገሪቱ ዘርፈ ብዙ ፖለቲካዊ ችግሮች እስርና ወከባ መፍትሄ አይሆንም የሚል መግለጫ ፓርቲያቸዉ ማዉጣቱን ገልፀዋል። ይህ ደግሞ በመጪዉ ግንቦት በሚደረገዉ ብሄራዊ ምርጫ ላይ ፓርቲዉ እንዳይሳተፍ የተወሰደ ርምጃ ነዉ ያሉት አቶ ዘካርያስ የማነ ብርሃን።

mandag 10. november 2014

Masreja Justice Center launches masreja.com



merejaMasreja Justice Center has been launched with Masreja.com. The center has human rights activists and legal professionals as its members. The main purpose is to collection information, documentation, and material evidence on crimes against humanity, extra judicial killing, illegal detention, and torture that have been committed by government officials, security and police operatives, and military unit commanders.
It puts justice and the rule of law as its primary mission by bringing the perpetrators of human rights violators to the spot light to account for their crimes. And to bring them to face justice in the Western countries. Please read the Masreja’s About US for details.
We are hereby requesting all pro-democracy and freedom web sites to support and promote this noble mission of Masreja by putting its banner at the left or right hand side corner of your web sites permanently, and also on the link section of your website. Doing so will enable for tens of thousands of Ethiopians go to the web site on a regular basis to provide us with the needed information, documentation, evidences without which Masreja’s mission will not possibly succeed. The public’s participation is extremely essential to collect information on human rights violating criminals in Ethiopia at various levels of state power.

lørdag 8. november 2014

fredag 7. november 2014

የሰላም ማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ ፋንታሁን ብርሃኑ ታሰረ

ነገረ ኢትዮጵያ 
10624743_609169355875393_2834013995865368265_nተቃዋሚ ፓርቲዎችን በማስተባበርና በማቀራረብ እርቅ ለማስፈን እንደሚንቀሳቀስ የሚነገርለት የመግባባት፣ አንድነትና ሰላም (ሰላም) ማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ ፋንታሁን ብርሃኑ መታሰሩን ምንጮች ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡

አቶ ፋንታሁን የታሰረው ‹‹የሰላም ጥሪ›› በሚል ነጭ ሰንደቅ አላማ በማውረብለብና የማህበሩን አላማ የሚገልጹ፣ እንዲሁም ማህበሩ በአሁኑ ወቅት ለአገሪቱ ችግር የሚላቸውን ጉዳዮች በዝርዝር የያዘ በራሪ ወረቀት ለህዝብ በመበተን ማህበሩን በማስተዋወቅ ላይ በነበረበት ጊዜ እንደሆነ ታውቋል፡፡

በራሪ ወረቀቱ የህሊና እስረኞች መፈታት እንዳለባቸው፣ መንግስት በሀይማኖቶች ላይ ጣልቃ መግባት እንደሌለበት፣ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ዜጎችን ማፈናቀሉ እንዲቆምና መንግስት በተቋማት ላይ ከሚያደርገው ጣልቃ ገብነት እንዲቆጠብ የሚመክሩ ሀሳቦች እንዳሉበት ለማወቅ ተችሏል፡፡

ነጭ ሰንደቅ አላማ ሲያውረበልብ፣ የማህበሩን አላማና በህዝብ ላይ አሉ ያላቸውን ችግሮች ለህዝብ ሲያስተዋወቅ የተያዘው አቶ ፋንታሁን ህዝብን ለማነሳሳትና አመጽ ለመቀስቀስ ሙከራ በማድረግ በሚል እንደተከሰሰም ምንጮች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

አቶ ፋንታሁን እሁድ ጥቅምት 23 ሽሮ ሜዳ አካባቢ በራሪ ወረቀት ሲበትን ተይዞ ላዛሪስት በሚባለው ፖሊስ ጣቢያ ታስ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡

የአመራር አባሉ የት እንዳሉ መኢአድ አያውቅም



የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት - መኢአድ
የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት - መኢአድ
 
ከመኖሪያ ቤታቸው በፌዴራል ፖሊስ የተወሰዱት የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት - መኢአድ ከፍተኛ አመራር አባል አቶ ተስፋዬ ታሪኩ፤ የደረሱበትን እስካሁን እንደማያውቁ የፓርቲው ፕሬዚደንት ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡
ከባህር ዳርና ከጎንደር የተወሰዱ የፓርቲው አባላትም የት እንዳሉ አይታወቅም ብለዋል የመኢአድ ፕሬዝደንት አቶ አበባው መሃሪ።
የፌደራልና የክልል ባለስልጣናት እስካሁን በጉዳዩ ላይ አስተያየት አልሰጡም።

 

torsdag 6. november 2014

በኢብራሂም መሀመድ መዝገብ ተከሰው ከነበሩት 6 ቱ ላይ የቅጣት ወሳኔ ተላላፈባቸው

(ቢቢኤን. ሐሙስ ጥቅምት 27/2007) ስኔ 27 አሚሩ ድምፃችን ይሰማ ጠርቶት በነበረው ሰላማዊ ተቃውሞ በግፍ ተይዘው ታስረው ከነበሩት ወንድሞች መካከል 5ቱ ጥቅምት 24 በዋለው ችሎት ያቀረቡት የመከላኬያ ምስክር በቂ ነው በማለት በነፃ ተሰናብተው የነበረ ሲሆን በተቀሩት 6 ት ተከሳሾችን ደሞ ጥፋተኞች ናቸው በማለት ለቅጣት ውሳኔ ለዛሬ መቅጠሩ ይታወሳል።
news
ፍርድ ቤቱም ዛሬ በዋለው ችሎ ፍርደ ገምደልነቱን በግልፅ ያሳየ የፍርድ ቤቱን ካንጋሮነት ያረጋገጠ አሳፋሪ የቅጣት ወሳኔ መስጠቱን ለማወቅ ተችሎዋል።የቅጣት ውሳኔ ከተላለፈባቸው 6ቱ ንፁሀን ሙስሊሞች መካከል 10ኛ ተከሳሽ ሲቀር በሌሎቹ ላይ 1 አመት ከ 3 ወር የፈረድ ሲሆን 10ኛ ተከሳሽ ላይ ግን የ1 አመት ከ5 ወር የቅጣት ውሳኔ ማስተላለፋን ለቢቢኤን ምንጮች ገልፀዋል።

በሌላ ዜና የህዝበ ሙስሊሙ መፍቴ አፈላላጊ ኮሚቴዎች የመከላኬያ ምስክር በዛሬው እለትም ተደምጦ መዋሉን ታወቀ::
የሚሊዬን ኢትዬዺያውያን ሙስሊሞች ተወካይ የሆኑትና የሚሊዬን ኢትዬዺያውያንን ጥያቄ አንግበው በግፍ ለእስር የተዳረጉት የሳላም አንባሳደሮች የህዝበ ሙስሊሙ መፍቴ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ችሎት ዛሬ ቀጥሎ የዋለ ሲሆን መኪ
 መሀመድ በጭብጥ 11ና ሐይረዲን ከድር በጭብጥ 7 ለሰላም አንባሳደሮቹ የመከላኬያ ምስክር ሆነው ቀርበዋል።

የችሎቱ ቀዳሚ ምስክር የነበረው ወንድም መኪ መሀመድ በጭብጥ 11 የመሰከረ ሲሆን የመንግስት ታጣቂ ሀይሎች ወረሀ ሐምሌ 8 በአወሊያ ሊደርግ ታስቦ የነበረው የሰደቃና አንድነት ፕሮግራም ለማሰነዳት ሀምሌ 6 ምሽት ለፕሮግራሙ ዝግጅት ሲያደርጉ በነበሩት ንፁሀን ኢትዬዺያውያን ሙስሊሞች ላይ የወሰዱትን አስከፊ እርምጃና የፈፀሙትን መንግስታዊ ሽብር አስመልክቶ ለፍርድ ቤቱ ሰፍ ያለ ማብራሬያ ሰጥተዋል።መንግስት በእለቱ ሊደረግ የነበረው የሰደቃና አንድነት ፕሮግራም ለማደናቀፍ ሆን ብሎ በማሴር ያሰማራቸው የመንግስት ታጣቂ ሀይሎች የተከበረውን የምእመናን መስገጃና ፀሎት ማድረጌያ የሆነውን መስጂድ በመድፍር በንፁሀን ሙስሊሞች ላይ ከባድ የሆነ አካላዊም ስነ ልቦናዊም አደጋ ማድረሳቸውንም ጨምሮ ገልፆዋል በእለቱም በርካቶች የተደበደቡ እንደ ነበሩ በመግለፅ በተለይም በአሁኑ ሳአት ከህዝበ ሙስሊሙ መፍቴ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ጋ በግፍ በሀሰት ተከሰው በእስር ላይ የሚገኙት የቀድሞው የአወሊያ ተማሪና የካውንስል አባል ወንድም ሙባረክ አደምንና ሌላኛውን ወንድማችንን ሀለዲ ኢብራሂምን ከፍተኛ ድብደባ እንዳደረሱባቸውም ለፍርድ ቤቱ የዛሬው ምስክር የነበረው ወንድም መኪ መሀመድ ገልፆዋልዩ።

በአጣቃላይ ሀምሌ 6 ምሽት አወሊያ ላይ የመንግስት ታጣቂ ሀይሎች ሲፈፅሙት የነበረው በደልና ግፍ ከገደብ ያለፈና እጅግ ሰባአዊነት የጎደለው ተግባር ሲፈፅሙ እንደ ነበረ ምስክሩ ጨምሮ ገልፆዋል።

በእለቱ ችሎት ለሰላም አንባሳደሮቹ ሁለተኛ ምስክር ሆኖ የቀረበው ወንድም ሐይረዲን ከድር የነበረ ሲሆን በጭብጥ 7 ላይ መንግስት ሙስሊሙ መሀበረሰብ አንስቶዋቸው በነበሩት 3 ህጋዊና ህገ መንግስታዊ ጥያቄዎች ላይ ምን ያክል ጣልቃ ይገባ እንደነበረና በተለይም መስከረም 27 2004 ሊደረግ በነበረው ምርጫ ላይ መንግስት ሲያደርገው የነበረውን ቀጥተኛ ጣልቃ ገብነት አስመልክቶ ሰፋ ያለ ማብራሬያ ለድርድ ቤቱ ሰጥተዋል።በተለይም የመስከረም ወሩ ምርጫ ከመካሄዱ አስቀድሞ በተለያዩ የአዲስ አበባ ወረዳዎች ላይ ምርጫውን አስነልክቶ ስብሰባዎች ይካሄዱ እንደነበረ የገለፁት ምስክር በስብሰባዎቹ ላይ በሚሊዬን ኢትዬዺያውያን ሙስሊሞች የተመረጡትን የህዝበ ሙስሊሙን መፍቴ አፈለሰላጊ ኮሚቴዎችን ስም የማጥፋት ዘመቻ ማድረግና በተለይም ሙስሊሙ ማሀበረስብ ምርጫው እንዲካሄድ የጠየቀው መስጂድ መሆኑን ተከትሎ መንግስት የራሱን የግል አላማውን ለማሳካት በማሰብ ምርጫው መካሄድ ያለበት በቀበሌ ነው ሲል በተወካዬቹ በወረዳው ስራ አሰፈፃሚዎች በኩል ጫና ያሳድር እንደነበረም ምስክሩ ለፍርድ ቤቱ ጨምሮ ገልፀዋል። የእለቱ ችሎት በዚሁ የተጠናቀቀ ሲሆን የእለቱ ምስክር የነበሩት ወንድሞች ከሁለቱም የህግ ባለሞያዎች ለተነሱላቸው ዋናና መስቀለኛ ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ በመስጠት አሰገራሚ የመከላኬያ ምስክርነት ቃለቸውን ሰጥተዋል::

በእለቱ ከነዚ ሁለቱ ምስክሮቻ ጋ ለመመስከር ፍርድ ቤት ቀርበው የመበሩት ሁሴን ጣሂርና ሀይሪያ ሁሴን እነሱ ሊመሰክሩት የነበረው ጭብጥ ቀደም ሲል በመሰከሩት ምስክሮች ተገቢ በሆነ ሆኔታ በመብራራቱ የተከሳሽ ጠበቆች ገልፀው ቀሪዎቹ እንዲሰናበቱላቸው ጠይቀዋል በጠየቁትም መሰረት ሁለቱ ምስክሮቻችን በበቂ እንዲሰናበቱ ተደርጎዋል።

 ህዝበ ሙስሊም ዛሬም እንደተለመድው ችሎት በመገኝት በመገኝት ለወካላቸው ንፁሀን መሪዎች ያለውን አጋርነት ገልፆዋል ችሎት በዚሁ የተጠናቀቀ ሲሆን ቀሪ የሰላም አንባሳደሮ የመከላኬያ ምስከር ለመስማል ለነገ ለአርብ ለጥቅምት 28/2007. ተቀጥሮዋል::
ነገም በሚኖረው ችሎት ህዝበ ሙስሊሙ የተለመደውን አጋርነቱን ይገልፃል ተብሎም ይጠበቃል

ሰሞኑን በጋምቤላ በተከስተው ግጭት 60 የሞቱ ; 36 የተሰደዱ; 4 የደረሱበት ያልታወቀና 23 የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ዝርዝር

የቀድሞው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች የአሁኑ የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ሰመጉ ባወጣው 132ኛ ልዩ መግለጫ በክልሉ በመንገሽና ጎደሬ ወረዳዎች ተፈጥሮ በነበረው ግጭት የተገደሉ የ60 ሰዎች ስም ዝርዝር ይፋ አድርጓል። ዝርዝሩን ይመልከቱ
gambela
gambela 2
gambela 3

onsdag 5. november 2014

በውጥረት የተጀመረው የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባዔ በሰላም ተጠናቀቀ

በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ2007 የሚደረገው የጥቅምት ወር የቅዱስ ሲኖዶስ ጠቅላላ ጉባዔ በሰላም እና በስምምነት ተጠናቋል። ቀደም ሲል ማህበረ ቅዱሳንን ለማሳጣት እና በአሸባሪነት ለመወንጀል፤ በፓትርያርኩ አማካኝነት በተጠራው ስብሰባ ላይ ክፋት ያለው ንግግር ሲያደርጉ የነበሩ ሰዎች ቤተ ክርስቲያናዊ ቅጣት ደርሶባቸዋል። ፓትርያርኩም ቢሆኑ፤ በመጨረሻ የቅዱስ ሲኖዶሱን ወቀሳ ተቀብለው፤ “እሺ ከናንተ ቃል አልወጣም።” ይበሉ እንጂ፤ ለዚህ ሁሉ የዳረጋቸውና ልዩ ጸሃፊያቸው የነበረው ንቡረ ዕድ ኤልያስ አብርሃ እንዲባረር የሚል ሃሳብ ሲቀርብ “እኔን ብታባርሩኝ ይሻላል፤ በፍጹም አይሆንም።” በማለታቸው ለግዜው የልዩ ጽሃፊያቸውን ጉዳይ ወደጎን በመተው በሌሎቹ የቤተክርስቲያኗ አማሳኞች ላይ ቅጣት አሳልፈው ጉባዔው በሰላም እና በጸሎት ሲከናወን ነበር የሰነበተው።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት

የቅዱስ ሲኖዶሱን የስብሰባ ሂደት በቅርብ ይከታተል የነበረው “ሐራ ዘተዋሕዶ” የተባለው ድረ ገጽም የጉባዔውን የመጨረሻ ውሎ ዘግቧል። በኛ በኩል የመግለጫውን ኮፒ አስቀድመን፤ ከዚያ በመቀጠል ለዝርዝር ዘገባው የ”ሐራ ዘተዋሕዶ”ን ሙሉ ዜና መልሰን ለናንተ አቅርበነዋል።
የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ጋዜጣዊ መግለጫ
የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ጋዜጣዊ መግለጫ

የቅዱስ ሲኖዶስ ዓመታዊ ምልአተ ጉባኤ ተጠናቀቀ

የወያኔ ግፍ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ

         
ዘረኛዉ ወያኔና ባለሟሎቹ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በጋምቤላና በሸኮ መዠንገር አካባቢ የሚያካሄዱትን የማንአለብኝነት የመሬት ዝርፍያና ዜጎችን እርስ በርስ በማጋጨት ተጠቃሚ ለመሆን የሚያደርጉት አራዊታዊ ሩጫ የተነሳ ከፍተኛ ቁጥር ያለዉ ህዝብ ይህ ነዉ ተብሎ ሊነገር የማይችል እልቂት እየተፈጸመበት ነዉ። የመዠንገር ህዝብ የሞትና የህይወትን ያክል የማይወጣዉ ምርጫ ስለቀረበለት ተወልዶ ያደገበትን የአባቶቹንና የአያቶቹን አካባቢ ለቅቆ በመዉጣት እራሱን ለመከላከል ባደረገዉ እንቅስቃሴ የብዙ ንጹሃን ዜጎችና ቁጥራቸዉ ቀላል የማይባል ምስኪን ወታደሮችም ህይወት ማለፉ በይፋ እየተሰማ ነዉ።

 ይህንን ተከትሎ ግፈኞቹ የወያኔ መሪዎች በአካባቢዉ ብዙ ዘመን በቆዩ ብሄሰቦች መካክል ሆን ብለዉ ግጭት እንዲነሳ እያደረጉ በህዝብ መካክል ግጭትትና ዕልቂት የተነሳ በማስመሰል በአካባቢዉ ከፍተኛ ሰቆቃ በመፈፀም ላይ ይገኛሉ።

በዚህ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች እየደረሰ ላለዉ መጠነ ሰፊ ግጭትና ዕልቂት ተጠያቂዉ በአካባቢዉ ለዘመናት አብሮ በመደጋገፍ የኖረዉ ህዝብ ሳይሆን የዚህ አሰቃቂ ዕልቂት ባለቤትና ጠንሳሽ ህወሓትና ዘረኛ መሪዎቹ መሆናቸዉን ለአንድም ደቂቃ ሊዘነጋ አይገባም።

 ይህ ግጭት ሊነሳ የቻለዉ ህወሓት የአካባቢዉን ደሃ ገበሬ ከትዉልድ መሬቱ ላይ እያፈናቀለ መሬቱን ለከፍተኛ የጦር መኮንኖቹና የኔ ለሚላቸዉ ባለሟሎቹ በማከፋፈሉ መሆኑን ይህንን ግፍ የሚሰማ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ልብ ሊለዉ ይገባል። ህወሃት የአማራን ተወላጆች አካባቢዉ የእናንተ አይደለምና ዉጡ እያለና እያፈናቀለ በሌላ በኩል ግን በየክልሉ የአካባቢዉን ነዋሪ እያፈናቀለ የራሱን ሰዎች የመሬት ባለቤት ማድረጉ አዲስ የጀመረዉ ክስተት ሳይሆን ቆየት ያለና ስር የሰደደ የወያኔ አሰራር ነዉ።

ይህ ዛሬ በጋምቤላና በአካባቢዋ እየደረሰ ያለዉ ግፍና መከራ ለአካባቢዉ ህዝብ ብቻ የሚተዉ ነጠላ ችግር ሳይሆን በአጠቃላይ ወያኔ በአገራችን ላይ ሆን ብሎ በማድረስ ላይ ያለዉ ችግርና መከራ አካል ነዉ። በጋምቤላ ዉስጥ የፈሰሰዉና እየፈሰሰ ያለዉ የሴቶች፤ የወጣቶች፤ የአረጋዉያንና የህጸናት ደም ለሁላችንም የነጻነት ጥሪ እያቀረበልን ነዉ። ይህ የነጻነት ጥሪ ሰምተን የምናልፈዉ ወይም ነገ እንደርሳለን በለን በቀጠሮ የምናልፈዉ ጥሪ አይደለም። ጥያቄዉ የአገርና የዜጎች ህልዉና ጥያቄ ነዉና ነገ ዛሬ ሳንል አሁኑኑ ይህንን የነጸነት ጥሪ ሰምተን ምላሽ ልንሰጠዉ ይገባል።

ይህ ወያኔ በደቡብ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ዉስጥ በንጹሃን ዜጎቻችን ህይወት ላይ እየፈጸመ ያለዉ ግፍ በአገራችን ህዝብ ላይ ሲደርስ የመጀመሪያዉ አይደለም፤ ካላቆምነዉ በቀር የመጨረሻዉ እንደማይሆንም አካሄዱ በግልጽ እያሳየን ነዉ። ወያኔ ጋምቤላ ዉስጥ ለምለም መሬት እየፈለገና ነዋሪዉን እያፈናቀለ መሬቱን ለባለሟሎቹ ማደሉን ሳይታቀብ በማንለብኝነት እንደቀጠለበት ነዉ።

መሬቱን የተቀማዉ ደሃዉ የጋምቤላ ገበሬም ጫካ እየገባ ከወያኔ ጋር መተናነቁን ቀጥሏል። ትናንት በኦሮሚያ፤ በጉራፈርዳና በቤንሻንጉል አካባቢዎች በአማራ ተወላጆች ላይ የደረሰዉ ግፍና መከራ ዛሬ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ዉስጥ በተለያዩ ብሄረሰቦች ላይ እየደረሰ ነዉ።

ግንቦት 7 የፍትህ፤ የነጻነትና የዲሞክራሲ እንቅስቃሴ ይህ ለከቱን የለቀቀ የህወሓት ዕብሪት እንዲተነፍስና በወገኖቻችን ላይ የሚደርሰዉ ግፍና ሰቆቃ እንዲቆም እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ነግ በኔ እያለ የነጻነት ትግሉን እንደቀላቀል የትግል ጥሪ ያደርጋል።

 ወያኔ እያደረሰ ያለዉ እስራት፤ ድብደባ፤ ግድያና ስደት የሁላችንንም ቤት እያንኳኳ ነዉና ሁላችንም እንደ አንድ ሰዉ ቆመን ወያኔንና ወያኔ የፈጠረዉን ዘረኛ ስርዐት በትግላችን መደምሰስ አለብን። በጋምቤላና በተለያዩ የአገራችን አካባቢዎች የፈሰሰዉ የንጹሃን ወገኖቻችን ደም ደመከልብ ሆኖ የማይቀረዉ ለመብታችንና ለነጻነታችን ቆመን ወያኔን ካስወገድን ብቻ ነዉ።
በህብረት እንነሳ!!!!

በአንድ አካባቢ ኢትዮጵያዊያን ላይ የሚካሄድ ጥቃት በሁሉም ኢትዮጵያዊ ላይ የሚካሄድ ጥቃት ነው!

ህወሓት/ኢህአዴግ በተለያዩ ኢትዮጵያውያን ላይ ያነጣጠረ የግፍ ተግባር ማካሄድና የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲውን ተግባራዊ ማድረጉን በሰፊው ቀጥሏል::  በዚህ አኳያበሶማሌ፣ በአማራው፣ በኦሮሞ፣ በሲዳማ፣ በአፋር፣….ወዘተ ተወላጆች ላይ የሚያካሂደው እልቂት በቂ መረጃ ነው::
shengoየዚህ ቀጣይ ረገጣ ተከታታይ ዒላማ የሆነው አንዱ የአማራው፡ተወላጅ ነው:: ህወሓት/ኢህአዴግ ከመነሻው የአማራ፡ተወላጁን  በጠላትነት ፈርጆ በተለያየ ደረጃየጥቃት ዒላማ አድርጎታል።

 በዚህም መሠረት በራሱ ትዕዛዝም ሆነ በተለጣፊ ድርጅቶቹ አማካኝነት እጅግ ዘግናኝ ግፍ የተሞላበት ወንጀል ፈጽሟል። ለዘመናት  ከኖረበት ቦታ “ወደ መጣህበት ሂድ” ተብሎ ንብረቱ ተነጥቆ ባዶ እጁን በግዳጅ እንዲባረር ተደርጓል። ይህ አልበቃ ብሎ ህፃናት ልጆች ሳይቀሩ አሰቃቂ በሆነ ግፍ እንዲታረዱ ዜጎች ወደ ገደል እንዲወረወሩና፣ ቤታቸው ውስጥ እንዳሉ እንዲቃጠሉ ተደርጓል። በአርባ ጉጉ፣ በወተር ፣በአርሲ .ወዘተ የተካሄደው ይህንኑ ነው የሚያሳየው።

ለዚህ ጨካኝና ህገወጥ ተግባርም የህወሓት/ኢህአዴግ ባለሥልጣኖች በቀጥታም በተዛዋሪም ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል። በጊዜው ጠቅላይ ሚኒስተር የነበረው ታምራት ላይኔ በአማራው ተወላጅ ላይ የኦጋዴን ህዝብ እርምጃ እንዲወስድ ያካሄደው ግልጽ የሆነ መገፋፋት፣ በአርሲ በተካሄደ እልቂት እነ ኩማ ደመቅሳ ዋና ተዋናን እንደነበሩ፣ መለሰ ዜናዊ ከጉራፈርዳ የተባረሩትንና ለአቤቱታ የመጡን ዜጎች እንኳን አባረሯችሁ የሚል አንድምታ  የሚሰጥ መግለጫ በይፋ መስጠቱ ጥቂቶቹ ማስረጃዎች ናቸው።

ይህ ህወሓት/ኢህአዴግ ሆን ብሎ የሚፈጽመውና የሚያበረታታው ህዝብን እርስ በርስ የማጫረስ ተግባር እጅግ እየሰፋ፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተጠናከር በአደገኛፍጥነትመም በመቀጠል ላይ ነው።

ትላንት ከትላንት በስቲያ በተለያዩ ቦታዎች እንደተደረገው ሁሉ፣ ባለፉት ጥቂት ሳምንታትም ባለማቋረጥ በጋምቤላ አካባቢ በተመሳሳይ ሁኔታ በዋናነት በዚሁ በአማራ ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ የድብደባ፣ የግድያና የማፈናቀል እርምጃ በሰፊው ተካሂዶ በመዠንገር አካባቢ ብቻ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሲሞቱ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ቆስለዋል፣ በሽዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ተፈናቅለዋል።

ይህ ሁሉ ሲሆን፣ የዜጎችን ደህንነት የመጠበቅ ግዴታ ያለበት መንግሥት መንበር ላይ የተቀመጠው ህወሓት/ኢህአዴግ ሁኔታው እንዳይከሰት ቀድሞ ለመከላከልም ሆነ በጊዜ ለማስቆም የወሰደው ምንም እርምጃ የለም። ችግሩ ከተፈጠረ በኋላም ቢሆን የተጎዱትን ለመንከባከብ፣ ህክምና የሚሹትን ለመርዳት፣ መልሶ ለማቋቋምና ወንጀለኞቹን ለህግ ለማቅረብ የሚያደርገው ይህ ነው የሚባል ሙከራ አይታይም።  ይሀ ሁሉ  የሚያመለክተው ያለው ስርዓት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የዚህ ወንጀል አካል እንደሆነ ነው።
ሸንጎው የኢትዮጵያን ህዝብ አንዱን ከአንዱ በማጋጨት ሥልጣኑን ለማራዘም ህወሓት/ኢህአዴግ የሚያካሂደውን ቀጣይ ሀላፊነት የጎደለው ኢ-ሰብአዊ ግፍ አጥብቆ ያወግዛል። በአማራውም ሆነ በሌሎች ኢትዮጵያውያን ላይ በተከታታይ እየተካሄደ ያለውን የማፈናቀል፣የግድያ፣ የጅምላ እሰራትና  ሌሎች  ወንጀሎች ባስቸኳይ እንዲቆም ያሳስባል። እስካሁን የተፈጸመው ግፍ ሁሉ ብቃት ባለው እና  ከሥርዓቱ ባለሟሎች ነፃ በሆነ አካል እንዲጣራ፤ ወንጀለኞቹም ለፍርድ እንዲቀርቡ ያስገነዝባል።

በኦጋዴን፣ በኦሮሚያ፣ በሲዳማ፣ በአፋር፣ በወልቃይት እንዲሁም በሌሎች የሀገራችን ቦታዎች ውስጥ ይህ  ሥርዓት የሚያካሂደውን ማለቂያ የሌለው ግፍ ሸንጎ አጥብቆ ያወግዛል።

ሰዎችን በትውልዳቸው የተነሳ በጅምላ የጥቃት ሰላባ ማድረግ በዓለምአቀፍ ህግም አስጠያቂ እንደሆነ የዚህ ጥፋት ፈጻሚም አስፈጻሚም የሆኑ ሁሉ እንዲገነዘቡት በድጋሚ ለማሳሰብ እንወዳለን።

የዚህን  የግፍ ሥርዓት መጨረሻ ለማፋጠን ሁሉም ኢትዮጵያዊ አንድነቱን አጠናክሮ እንዲነሳ እናሳስባለን፡  በአንድ አካባቢ ኢትዮጳያዊያን ላይ  የሚካሄድ ጥቃት በሁሉም ኢትዮጵያዊ ላይ የሚካሄድ ጥቃት ነው!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

tirsdag 4. november 2014

የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር የ24 ሰዓት የተቃውሞ ሰልፍ ጠራ

የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር የመጀመሪያ ዙር ህዝባዊ ትግል ፕሮግራሙን ይፋ አደረገ
• የ24 ሰዓት (የአዳር) የተቃውሞ ሰልፍ ተጠርቷል
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

ጥቅምት 12 ቀን 2007 ዓ.ም 9 ተቃዋሚ ፓርቲዎች የመሰረቱት ትብብር ‹‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ›› በሚል ለአንድ ወር የሚቆይ የመጀመሪያ ዙር የህዝባዊ ትግል ፕሮግራሙን ዛሬ ጥቅምት 25/2007 ዓ.ም በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት ይፋ አደረገ፡፡
yilikal getenet
‹‹ነጻነት በሌለበት ፍትሃዊ ምርጫ የማይታሰብ በመሆኑ የተዘጋውን በር ለመክፈት የ‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ› በሚል የፕሮግራም መርሃ ግብር ለመክፈት ወስኖ የመጀመሪያው ዙር እንቅስቃሴ በአዲስ አበባ ከተማ ለማድረግ›› እንዳዘጋጀ ያሳወቀው ትብብሩ የትግሉ ዓላማ ፍትሃዊ ምርጫ እንዲኖር የሚያስችል መሆኑን ገልጾአል፡፡

‹‹ምርጫ ቦርድ ለገዥው ፓርቲ ያለውን ወገናዊነትና ጉዳይ አስፈጻሚነት ፍንትው አድርጎ አሳይቷል›› ያለው መግለጫው በመጀመሪያ ዙር የአንድ ወር ፕሮግራሙ 6 ዋና ዋና ተግባራትን ለመፈጸም ዝርዝር እቅዶችን አውጥቶ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አስታውቋል፡፡ በህዳር ወር የሚያከናውናቸው ተግባራትም፡-

1. በቤተ እምነት ጸሎት እንዲደረግና ጥሪ ማቅረብና አማኞች እንደየ እምነታቸው ተሳትፎ እንዲያደርጉ ማድረግ

2. የአደባባይ ህዝባዊ ስብሰባዎችን ማድረግ


3. የተቃውሞ ድምጽ ማሰማት (ሰላማዊ ሰልፍ)

4. ለመንግስት ተቋማት ደብዳቤ ማስገባት

5. በምርጫ ዙሪያ የፓናል ውይይቶችን ማድረግና

6. የህዝብን ተሳትፎ ማበረታታትና ድጋፍ ማሰባሰብ እንደሆኑ በመግለጫው አሳውቋል፡፡

ከእቅዶቹ መካከልም በሶስት ተከታታይ እሁዶች በተለያዩ የአዲስ አበባ ክፍሎች 3 የአደባባይ ስብሰባዎች እንደሚኖሩ፣ በመጨረሻው መርሃ ግብርም ህዳር 27ና 28 በፕሮግራሙ ማጠቃለያነት የ24 ሰዓት (የውሎና የአዳር) የተቃውሞ ሰልፍ እንደሚደረግ የትብብሩ ሊቀመንበር ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ገልጸዋል፡፡

በገዥው ፓርቲና በምርጫ ቦርድ ጥምረት ይፈጸማል ያለውን ህገ ወጥ ተግባር በመታገል ለሰላማዊ ትግሉ አወንታዊ አስተዋጽኦ ለማበርከት እስከመጨረሻው በፅናት ለመቆም መዘጋጀቱን የገለጸው ትብብሩ በአገር ቤትና በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን፣ በትብብሩ ሂደት ቆይተው እስካሁን ያልፈረሙና ሌሎች ፓርቲዎች እና የዓለም አቀፉ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ ከጎኑ እንዲቆሙ ጥሪ አቅርቧል፡፡

mandag 3. november 2014

የሚሊዮኖች ድምጽ – እስሩኝ እንጂ አንድነትን ለቅቄ አልወጣም ያሉት ሴት ታጋይ ታሰሩ !

የወላይታ ዞን ዋና ከተማ ፣ የሶዶ ነዋሪ ናቸው። ዘር ኃይማኖት ሳይጠይቅ ሁሉንም ዜጋ ለማቀፍ በሩን ክፍት ያደረገው፣ ለሁሉም ዜጎች የቆመው የአንድነት ፓርቲ አባል ናችው። ፓርቲው የሚሊዮኖች ንቅናቄ ለነጻነት በሚል መርህ በበርካታ ከተሞች ህዝብባዊ እንቅስቃሴ ባደረገበት ወቅት በሶዶ ለተደረገው እንቅስቃሴ በየመንገዱ ከፍተኛ ቅስቀሳ ማድረጋቸው፣ ህዝቡ ማነጋገራቸዉና ማሳመናቸው በአገዛዙ ካድሬዎች አልተወደደላቸውም። “ለምን ወረቀት አሰራጭሽ?” በሚል ክስ ተመሰረተባቸው።
“የአንድነት ፓርቲ የምትለቂ ከሆነና አርፈሽ የምትቀመጭጪ ከሆነ ችገር አያጋጥምሽን” የሚል መደለያ ቢቀርብላቸው “ ነጻነቴን ስጡኝና ሕይወቴን ዉሰዱ” እንዳለው ፓትሪክ ሄንሪ አይነት የነጻነት ጥማትና ወኔ እንዳላቸው በማሳየት ፣ “እሰሩኝ እንጂ ከአንድነት አልወጣም” የሚል ምላሽ ሰጡ። ወ/ሮ ሃዲያ መሀመድ ይባላሉ።
ገዥው ፓርቲ ኢሕአደግ በሌሎች ቦታዎችም እንደሚያደርገው ፣ የግፍ ዱላውን አንስቶ፣ ምርጫው ሲቃረብ፣ በፈጠራ ክስ፣ ወ/ሮ ሃዲያ መሐመድ ለአመት እንዲታሰሩ ወስኗል። እኝህ እህታችን በአሁኑ ወቅት ለሰላም፣ ለዴሞክራሲና ለነጻነት በወህኒ ተወርዉረው ከፍተኛ ዋጋ እየከፈሉ ይገኛሉ።
እንግዲህ የአንድነት ፓርቲ ማለት ይህ ነው። የአንድነት አባላት እጅግ በጣም ፈታኝ በሆነ ሁኔታ፣ ሕይወታቸውን እየከፈሉ፣ ከስራቸው እየተባረሩ ፣ እየተደበደቡ ሰላማዊ በሆነ መንገድ የሚታገሉ ናቸው። ገዥዊ ፓርቲ እነዚህን ወገኖቻችንን ሲያስር በንዴትና ከወገዛ ባለፍ ተግባራዊ ምላሽ ያስፍልገዋል። ለአገዝዙ አፈና እስር ተግባራዊ ምላሽ ይሆን ዘንድ ደግም፣ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የሚሊዮኖች ንቅናቄን እንዲቀላቀልና አንድነት እንዲደገፍ እንጠይቃለን።
በየክልሉ ያላችሁ ኢትዮጵያዉያን የሚያታግላችሁ ድርጅት አላችሁ፣ የአንድነት ፓርቲ። አባል በመሆን ትግሉን ተቀላቀሉ። በዉጭ ያላችሁ ደግሞ ፣ በዉጭ ብትኖሩም የሕዝቡ አካል ናችሁና አገራዊ ግዴታችሁን በመወጣት፣ በድጋፍ ድርጅቶችም ይሁን በሲቪክ ማህበራት በመደራጀት ትግሉን በሐሳብ፣ በገንዘብ ፣ በዲፕሎማሲ ደግፉ።
ለዉጥ፣ ነጻነት ጥቂቶች ስለደከሙ አይመጣም። ለዉጥ ነጻነት ዋጋ ያስከፍላል። ብዙዎች ዋጋ እየከፈሉ ነው። እኛም የድርሻችንን ለመወጣት እንነሳ።
በኢትዮጵያ ዉስጥ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን በስፋት ለመከታተል የሚከተለውን የፌስ ቡክ ገጽ ላይክ ያደርጉ፡
https://www.facebook.com/MillionsOfVoicesForFreedomUdj
በዉጭ አገር ያላችሁ፣ ፓርቲዉን በጽሁፍ፣ ጠቃሚና ፕሮፌሽናል አስተያየቶች በመስጠት ሆነ በማንኛዉም ገንዝበ ነክ ባልሆኑ ጉዳዮች ለመርዳት ፣ የሚሊዮኖች ንቅናቄ ግብረ ኃይል ወይንም የአንድነት ድጋፍ ድርጅት አካል ሆናችሁ መስራት ለምትፈልጉ በሚከተለው አድራሻ ኢሜል ይላኩልን።
millionsforethiopia@gmail.com
በገንዘብ ለመርዳት http://www.andinet.org/ በመሄድ በስተቀኝ በኩል ከላይ «Donate» የሚለውን ይጫኑ ። የነ ወ/ሮ ሃዲያ መኀመድን ፈለግ እንከተል። ለመብታችንና ለነፃነታችችን እንነሳ!

የአንድነት ፓርቲ አዲስ አመራር መግለጫ ሰጠ

በእነሀብታሙ ላይ የተደረገው ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት እጅግ አሳፋሪ ነው››
‹‹ኢንጂነር ግዛቸው በአንድነት ቤት እንደጀግና መታየት አለባቸው››
‹‹ከመኢአድ እና ሰማያዊ ፓርቲዎች ጋር ተዋህደን መስራት አለብን››
አቶ በላይ ፍቃዱ /የአንድነት ሊቀመንበር/
—————-
‹የጸረ-ሽብርተኝነት አዋጁ አሸባሪ ነው››
‹‹ዘንድሮም አዋጁ ይሰረዝ ብለን መጠየቃችንን እንቀጥላለን››
አቶ ግርማ ሰይፉ /የፓርላማ ተወካይ የአንድነት ም/ፕሬዚዳንት/
——————————–




ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ጥቅምት 20 ቀን 2007 ዓ.ም፣ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) ‹‹በፖለቲካ እስረኞች ላይ እየተፈጸመ ያለው ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ይገኛል!›› በሚል ርዕስ በጽ/ቤቱ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቶ ነበር፡፡ መግለጫውንም የሰጡት የወቅቱ የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ በላይ ፍቃዱ፣ ም/ ፕሬዚዳንት አቶ ግርማ ሰይፉ እና የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ዘካሪያስ የማነ ብርሃን ናቸው፡፡
የኢህአዴግ አገዛዝ ከጊዜ ወደጊዜ ሰብዓዊ መብት በመጣስና ዜጎችን በማሰቃየት ወደር የሌለው መሆኑን የጠቀሰው መግለጫው ‹‹ሥርዓቱ ለአገዛዜ ያሰጉኛል የሚላቸውን ንጹሃን የፖለቲካ አመራሮችን፣ ጦማሪያንና ጋዜጠኞችን ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ ክስ በመመስረት ማሰሩ ሳያንስ እነዚህን ዜጎች ሰብዓዊ ክብራቸውን በመድፈርና ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት እየፈጸመ በማሰቃየት ላይ ይገኛል፡፡›› ብሏል፡፡
ፓርቲው የሥርዓቱ ዱላ ሆኖ እያለገለ ያለው የጸረ-ሽብርተኝነት አወጁ እንዲሰረዝ በህዝባዊ ንቅናቄ መጠየቁን በማውሳት ገዥው ፓርቲ ግን አምባገነንነቱን አጠናክሮ በመቀጠል በዜጎች ስቃይ መደሰትን ለጥያቄው ምላሽ ማድረጉን አስረድቷል፡፡
አቶ አንዷለም አራጌ፣ ናትናኤል መኮንን፣ አንዷለም አያሌው፣ ዳንኤል ሺበሺ፣ ሀብታሙ አያሌውና ሎሎችም በፖለቲካ እምነታቸው የተነሳ ወደማሰቃያ ስፍራ የተወሰዱ የአንድነት የቁርጥ ቀን ልጆች መሆናቸውን የጠቆመው መግለጫው፣፣ በሽብርተኝነት ወንጀል ተጠርጥረው በማዕከላዊ እስር ቤት በሚገኙት ዳንኤል ሺበሺ እና ሀብታሙ አያሌው ላይ የደረሰውን ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት ኮንኗል፡፡
ከመግለጫው በኋላ ከጋዜጠኞች የተለያዩ ጥያቄዎች ተነስተው ምላሽ ተሰጥቶባቸው ነበር፡፡ ‹‹በእነ ሀብታሙ ላይ የተደረገው ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት እጅግ አሳፋሪ ነው›› በማለት ለጥያቄዎች መልስ በመስጠት የጀመሩት አቶ በላይ ‹‹የቀድሞ የፓርቲው ሊቀ-መንበር ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራው በሕገ ደንቡ መሰረት በፈቃዳቸው መልቀቂያ ካስገቡ በኋላ ብሐራዊ ምክር ቤቱ ኃላፊነት በተሞላበት መልኩ የስልጣን ሽግግሩን በሕግ አግባብ ፈጽሟል፡፡ ኢንጂነሩ ውሳኔያቸው ትክክል ነበር፡፡ እሳቸውም ደስተኛ ናቸው፡፡ ኢንጂነር ግዛቸው በአንድነት ቤት እንደጀግና መታየት አለባቸው፡፡ ብዙ ፈተናዎችን አልፈዋል፡፡ በአንድነት ቤት የተለየ ቦታ ሊሰጣቸው ይገባል፡፡›› ብለዋል፡፡
ውህደትን በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄም የፓርቲው አዲሱ ሊቀመንበር ‹‹ከፓርቲዎች ጋር አብሮ የመስራት አቋም አለን፡፡ የአንድነት እና የመኢአድ የውህደት ጉዳይ ቢያልቅም በአሰራር ደረጃ ትንሽ የሚቀር ነገር አለ፡፡ በአንድነት ዕይታ የፖለቲካ ምህዳሩን ማስተካከል አለብን፡፡ ከመኢአድ እና ሰማያዊ ፓርቲዎች ጋር ተዋህደን መስራት አለብን፡፡ በድርጅቶቹ ባህል አኳያ እንጂ ሶስታችንም ከርዕዮተ ዓለም ጀምሮ ብዙ ልዩነት የለንም፡፡ አንድ ነን፡፡ ይህ ውህደት መቼ እንደሚሆን በእርግጠኝነት መናገር ባልችልም አንድ ቀን ግን እውን ይሆናል ብለን እናምናለን›› የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
የፓርላማ ተወካዩ አቶ ግርማ ሰይፉ በበኩላቸው፣ የጸረ-ሽብርተኝነት አዋጁን አስመልክቶ ለቀረበላቸው ጥያቄ ፓርቲያቸው በ‹‹ሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት›› በሚለው ንቅናቄ ‹‹አዋጁ ይዘረዝ!›› በማለት መጠየቃቸውን አስታውሰው፣ ‹‹ዘንድሮም አዋጁ ይሰረዝ ብለን መጠየቃችንን እንቀጥላለን፡፡ የጸረ-ሽብርተኝነት አዋጁ አሸባሪ ነው›› ሲሉ ገልጸዋል፡፡
በመጨረሻም ፓርቲው በመግለጫው፣ የበደልን ዘመን ለማሳጠር እንዲቻል ህዝቡ በቁጭት ለለውጥ እንዲነሳ ጥሪ አቅርቦ በደልን ለማስቆም መታገል ወሳኝና ብቸኛው መፍትሄ መሆኑን አስረድቷል፡፡